У нас вы можете посмотреть бесплатно ለድህረ-ክፍያ የኤሌክትሪክ ቆጣሪ ተጠቃሚ ደንበኞቻችን በሙሉ или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
ለድህረ-ክፍያ የኤሌክትሪክ ቆጣሪ ተጠቃሚ ደንበኞቻችን በሙሉ ተቋማችን የድህረ-ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞቹ ወርሃዊ የፍጆታ ሂሳባቸውን ያለምንም መንገላታት በዘመናዊ የክፍያ አማራጮች እንዲከፍሉ ማመቻቸቱ ይታወቃል፡፡ በዚሁ መሰረት አብዛኞቹ ደንበኞቻችን ይህንን ተጠቅመው ክፍያቸውን በወቅቱ እየፈፀሙ በመሆናቸው እያመሰገንን፤ የተወሰኑ ደንበኞች ግን አሁንም የሚጠበቅባቸውን የፍጆታ ሂሳብ በወቅቱ እየከፈሉ አይደለም፡፡ ሆኖም ተቋማችን ባለው አሰራር መሠረት በወቅቱ ግዴታቸውን በማይወጡ ደንበኞቹ ላይ አገልግሎት የማቋረጥ ሥራ እያከናወነ የሚገኝ ቢሆንም፤ ይህንን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም አንዳንድ አጭበርባሪዎች የእኛን ተቋም ሠራተኛ በመምሰል ቆጣሪ ልናነብ ነው፣ ሂሳብ ባለመክፈላችሁ አገልግሎቱን እናቋርጣለን እያሉ ደንበኞችን እያንገላቱና እያጭበረበሩ መሆኑን ደርሰንበታል፡፡ ስለሆነም እየተወሰደ ያለው አገልግሎት የማቋረጥ እርምጃ የሚከናወነው ህጋዊና የታደሰ መታወቂያ እንዲሁም የሥራ ትዕዛዝ በያዙ የተቋማችን ሠራተኞች ብቻ መሆኑን እያሳወቅን፣ ለመሰል ሥራ የሚመጣ ባለሞያ ሲኖር ደንበኛው ይህንን አረጋግጦ እንዲያስፈፅም እናሳውቃለን፡፡ እርሶም መሰል እርምጃ ከመወሰዱ በፊት የሚጠበቅብዎትን የፍጆታ ሂሳብ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በዘመናዊ የክፍያ አማራጮች በወቅቱ እንዲፈፅሙ በዚህ አጋጣሚ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡ #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት