У нас вы можете посмотреть бесплатно ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ሶምሶን /መስፍነ እስራኤል # ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ# @ selam@ የድንግል ማርያም ልጅ is live! или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ሶምሶን [ መስፍነ እስራኤል ] ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ] † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † ቅዱስ ገብርኤል † 🕊 † ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል:- ከ፯ [ 7 ] ቱ ሊቃናት አንዱ:: በራማ አርባብ በሚባሉ ፲ [10] ነገደ መላእክት ላይ የተሾመ:: በመጀመሪያዋ የፍጥረት ቀን መላእክትን ያጸና:: ቅዱሳንን ሁሉ የሚረዳ:: ሠለስቱ ደቂቅን : ዳንኤልን : ሶስናን ከሞት የታደገ ታላቅ መልዐክ ነው:: ከምንም በላይ ግን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቅዱሱን መልዐክ "መጋቤ-ሐዲስ" ብላ ታከብረዋለች:: ቅዱስ ገብርኤል የስሙ ትርጉዋሜ "አምላክ ወሰብእ - እግዚእ ወገብር" ነውና ለሥነ ፍጥረት ሁሉ የሚሆን ሐዲስ ዜናን ወደ እመቤታችን ድንግል ማርያም አምጥቷል:: መልዐኩ እመቤታችንን ከመጸነሷ ጀምሮ ባይለያትም መጋቢት ፳፱ [ 29 ] ቀን ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ አብስሯታል:: ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በማግስቱ በድምቀት እንዲከበር በወሰኑት መሠረት ዛሬ ፴ [ በ30 ] ይከበራል:: † ሶምሶን ረዓይታዊ † 🕊 † እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን: ሀያ ሁለቱን ሥነ ፍጥረትን ፈጥሮ አዳምን ገዢ አደረገው:: አክሎም በነፍስ ሕያው አድርጐ: በመንፈስ ቅዱስ አክብሮ: ነቢይና ካህን አድርጐ: ካንዲት ዕፀ በለስ በቀር በፍጥረት ሁሉ ላይ አሰለጠነው:: አባታችን አዳም ግን ስህተት አግኝቶት ከገነት ወጣ:: መከራና ፍዳም አገኘው:: በኋላም ለ፻ [100] ዓመት አልቅሶ ንስሃ ገባ:: ጌታም ንስሃውን ተቀብሎ "ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" የሚል ተስፋ ድህነትን ሰጠው:: ስለዚህም ምክንያት ለ፶፻፭፻ [5,500] ዓመታት ትንቢት ሲነገር: ሱባኤ ወደ ታች ሲቆጠር: ምሳሌም ሲመሰል ኖረ:: ከደግ ፍጥረት አዳም እስከ ኖኅ ድረስ: የሴት ልጆች እግዚአብሔርን በንጽሕና ሁነው በደብር ቅዱስ አመለኩ:: ትንሽ ቆይተው ግን ስለተቀላቀሉ ከቃየን ልጆች ጋር በማየ ድምሳሴ ጠፉ:: በጻድቅ ሰው ኖኅ የተጀመረው ትውልድም እግዚአብሔርን ለመዘንጋት ጊዜ አልፈጀበትም:: ነገር ግን ከሴም ዘር ቅንና ጻድቅ ሰው አብርሃም ተገኘ:: ከእርሱም ይስሐቅ: ከዚያም ያዕቆብ [ደጋጉ] ተገኙ:: ያዕቆብም "እሥራኤል" ተብሎ: በልጆቹ "ሕዝበ እግዚአብሔር" የተባለ ነገድ ተመሠረተ:: በተስፋይቱ ምድር በከነዓን እንዳይኖሩም ርሃብ ምድረ ግብጽ አወረዳቸው:: በዚያም ለ፪፻፲፭ [215] ዓመታት በጭንቅ የባርነትን ሕይወትን አሳለፉ:: እግዚአብሔርም ስለ ወዳጁ አብርሃም ሲል እሥራኤልን አሰባቸው:: የዋሕና ጻድቅ ሰው ሙሴን አስነስቶ እሥራኤልን ከግብጽ ባርነት አዳናቸው:: ይኸውም በጸናች እጅ: በበረታችም ክንድ: በ፱ [9] መቅሰፍት: በ፲ [10] ኛ ሞተ በኩር: በ፲፩ [11] ኛ ስጥመት ግብጻውያንን አጥፍቶ ነው:: በየመንገዱም ጠላቶቻቸውን እየተበቀለላቸው ነው:: ከዚህ ዘመን ጀምሮም እሥራኤል በመሳፍንትና በካህናት የሚተዳደሩ ሆኑ:: አስቀድሞ ሙሴ በምስፍና: አሮን በክህነት መሯቸው:: ቀጥሎም በቅዱስ ሙሴ ኢያሱ: በአሮን አልዓዛር ተተኩ:: እንዲህ እንዲህ እያለም ከኃያል ሰው ሶምሶን ረዓይታዊ ደረሱ:: ይኸውም ከዓለም ፍጥረት ፬፻፪፻ [4,200] ዓመታት በኋላ መሆኑ ነው:: በጊዜው እሥራኤል ጣዖትን እያመለኩ እግዚአብሔርን ስላሳዘኑት ለጠላቶቻቸው አሳልፎ ይሰጣቸው ነበር:: የአካባቢው መንግስታት እነ አሞን: አማሌቅ: ኢሎፍሊ ስንኳ ያኔ ዛሬም ቢሆን እንደምትመለከቱት ዶሮና ጥሬ ናቸው:: በጊዜውም የእሥራኤል ኃጢአት ስለ በዛ ኢሎፍላውያን [ፍልስጤማውያን ፵ [40] ዓመት በባርነት ገዟቸው:: ንስሃ ሲገቡ ደግሞ ልጅ በማጣት ያዘኑ ማኑሄ እና ሚስቱ [እንትኩይ] : በቅዱስ ሚካኤል ተበሥረው ኃያሉን ሶምሶንን ወለዱላቸው:: እርሱም ናዝራዊ [ከእናቱ ማኅጸን ለጌታ የተለየ] ነበርና ፍልስጤማውያንን ቀጥቶ ወገኖቹን እስራኤልን ከባርነት : በአምላኩ ኃይል ታደገ:: ከኃይሉ ብዛት የተነሳም :- ¤ አንበሳን እንደ ጠቦት ይገድል [መሣ.፲፬፥፭] ¤ ፫፻ ቀበሮዎችን አባሮ ይይዝ (መሣ.፲፭፥፫] ¤ በብርቱ ገመዶች ሲያስሩት እንደ ፈትል ይበጣጥሰው (መሣ.፲፭፥፲፬] ¤ በአህያ መንጋጋ ሽህ ሰው ይገድል [መሣ.፲፭፥፲፭] ¤ ጠባቂዎችን ከነ መቃናቸው ተሸክሞ ይወረውር ነበር:: [መሣ.፲፮፥፫] ውኃ ሲጠማውም ከአህያ መንጋጋ ላይ ፈልቆለት ጠጥቷል:: [መሣ.፲፭፥፲፰] በፍጻሜው ግን ደሊላ በምትባል ሴት ተታልሎ ምሥጢሩን በመግለጡና ጸጉሩ በመላጨቱ ኃይሉን አጥቷል:: ጠላቶቹም ዐይኑን አውጥተው መዘባበቻ አድርገውታል:: በፍጻሜው ግን ኃይሉ እንዲመለስለት ፈጣሪውን ለምኖ : አሕዛብ ለጣኦት በዓል እንደተሰበሰቡ የአዳራሹን ምሰሶ አፍርሶ አጥፍቷቸው ዐርፏል:: [መሣ.፲፫፥፲፮] ቅዱስ ሶምሶን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥላ [ምሳሌ] ነው:: † "ክፉ ናችሁ: ኃጢአታችሁ በዝቷል" የማይል ጌታ በመከራችን ሁሉ ተራዳኢ መልዐክን [ቅዱስ ገብርኤልን] ይዘዝልን:: ወርኀ መጋቢትን በሰላም እንዳስፈጸመ ወርኀ ሚያዝያን በምሕረቱ ይባርክልን:: [ † መጋቢት ፴ [ 30 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት [እመቤታችንን ያበሠረበት መታሠቢያ] ፪. ቅዱስ ሶምሶን [መስፍነ እስራኤል] ፫. ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ [ፍልሠቱ] ፬. ቅዱስ ዮሐንስ ዘአክሱም [ድርሳነ ሚካኤልን መጻፉ የሚነገርለት አባት] ፭. እግዚአብሔር ውሃን ከ፫ ከፈለው [ጠፈርን ፈጠረ] [ † ወርኀዊ በዓላት ] ፩. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት ፪. ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ [ሐዋርያ] ፫. አባ ሣሉሲ ክቡር ፬. ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት ፭. ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት † . በአምላኬም በእግዚአብሔር ፊት ስለ ተቀደሰው ስለ አምላኬ ተራራ ስለምን : ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ:: በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ:: አስተማረኝም . . . " † [ዳን.፱፥፳] † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር †