У нас вы можете посмотреть бесплатно ያየልኝ አለ | Apostolic Church of Ethiopia, Goro | Yadah Choir или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
አልመለስም ወደኋላዬ አልቆምም አልል በሰልፉ ላይ በህይወት እስካለሁ የሚገጥመኝን ጥሼ እጓዛለሁ እየሱስ ስላለኝ ያየልኝ አለ እርሱ ያሰበልኝ ኢየሱስ በሰማይ ያዘጋጀልኝ ዳግም ይመጣል በመላዕክት ታጅቦ በቅድስና በክብሩ ተውቦ 1. ሰልፉ ረጅም ቢሆን ቢበዛ መከራ ስጋዬን በጥርሴ ይዜ እጓዛለሁ ከአምላኬ ጋራ ይመጣል ሊወስደኝ እርሱን እጠብቃለሁ ያየልኝ ክብር አንድ ቀን አያለሁ መንገዴን ከፊቴ አስተካክሎልኛል በምህረት እጆቹ ላይተወኝ ይዞኛል እርሱ ያደርሰኛል ካሰበልኝ ቦታ ቃሉን የሚጠብቅ ታማኝ ነው የኔ ጌታ 2. አብዝቼ ስናፍቅ ያየልኝን ክብር ጠላቴ በቁጣ ሊያዝለኝ ቢጣጣር እኔ ግን በአምላኬ ሀይል እበረታለሁ የማርፍባትን ቤት ሀገሬን አያለሁ በእምነት ልዘርጋ ትቼ የኋላዬን እየተከተልኩኝ የህይወት መንገዴን መንግስቱን ለመውረስ ዘውትር እየተጋሁ እጓዛለሁ ወደፊት እየሱስን እያየሁ 3. በምድር እንግድነት በስደትም ብኖር ርስቴ ግን በሰማይ ከአባቴ ዙፋን ስር የመፃተኛ ህይወት ቢሆን አኗኗሬ አርፋለሁ አንድ ቀን በሰማይ ሀገሬ ይመጣል ኢየሱስ እኔን ሊወስደኝ ከአለም መከራ እርፍ ሊያደርገኝ አክሊል ሊሸልመኝ በቅዱሳኑ ፊት በእቅፉ ሊያኖረኝ ዘላለም ሊሆነኝ እረፍት