У нас вы можете посмотреть бесплатно ፀጉርን በፍጥነት የሚያሳድጉ 10 ምግቦች | Foods help for hair to grow или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
ለፀጉር እድገት ትልቅ ጠቀሜታ ያላቸው ምግቦች፦ 1. እንቁላል እንቁላል ትልቅ የፕሮቲን እና የባዮቲን ምንጭ ነው። እነዚህ ሁለት ንጥረ ነገሮች ለፀጉር እድገት አስፈላጊ ናቸው። በቂ ፕሮቲን መመገብ ለፀጉር እድገት ጠቃሚ ነው። ምክንያቱም የፀጉር ስሮች በአብዛኛው ከፕሮቲን የተሠሩ ናቸው። ባዮቲን ኬራቲን የተባለ የፀጉር ፕሮቲን ለማምረት በጣም አስፈላጊ ነው። ባዮቲንን በብዛት መጠቀም የባዮቲን እጥረት ባለባቸው ሰዎች ላይ የፀጉር እድገትን ለማሻሻል እንደሚረዳም ጥናቶች አረጋግጠዋል። 2 ኢንጆሪ ኢንጆሪ ቫይታሚን ሲን በውስጡ ይይዛል።ይህም ቫይታሚን ለፀጉር እድገት እጅግ ጠቃሚ ንጥረ ነገር ነው። ከዚህም ሌላ ቫይታሚን ሲ አንቲ ኦክሲደንት ባህሪ አለው። ይህም ማለት በፀጉር ስር ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ሞለኪዩሎችን ይከላከላል።እነዚህ ሞለኪዩሎች በሰውነታችን ውስጥ እና በአካባቢያችን ላይ ይገኛሉ። በቀን ቢያንስ አስከ 144 ግራም እንጆሪ መመገብ ለፀጉር እድገት አስፈላጊ ነው። ከዚህ ሌላም ሰውነታችን collagen ለማምረት ቫይታሚን ሲ ይጠቀማል። collagen ፀጉር እንዳይሰባበር የሚያግዝ ፕሮቲን ነው። 3. ጎመን ጎመን እንደ ፎሌት፣ ብረት ፣ ቫይታሚን ኤ እና ሲ ባሉ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች የበለፀገ ጤናማ አረንጓዴ አትክልት ነው። እነዚህ ንጥረ ነገሮች ለፀጉር እድገት እጅግ ጠቃሚ ናቸው። ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ቫይታሚን ኤ ለፀጉር እድገት አስፈላጊ ነው። ነገር ግን ከመጠን በላይ ቫይታሚን ኤ መውሰድ የፀጉር መርገፍ ሊያስከትል ይችላል። ጎመን ለፀጉር እድገት አስፈላጊ የሆነ ከዕፅዋት የሚገኝ ትልቅ የብረት ምንጭ ነው። ብረት ቀይ የደም ሴሎች ኦክስጅንን እንዲያጓጉዙ ይረዳል። እነዚህ ኦክስጅን ደግሞ ሰውነታችን ውስጥ ለሚደረገው ለሜታቦሊዝም ስርዓት እጅግ አስፈላጊው እና ዋነኛው ንጥረነገር ነው። 4. ስኳር ድንች ስኳር ድንች ትልቅ የቤታ ካሮቲን ምንጭ ነው። ሰውነታችን ይህን ውህድ ወደ ቫይታሚን ኤ ይለውጠዋል ይህም ከፀጉር ጤና ጋር የተያያዘ ነው.። የቫይታሚን ኤ እጥረት የፀጉር መርገፍን ያስከትላል ። እንደ ስኳር ድንች ያሉ በቫይታሚን-ኤ የበለጸጉ ምግቦችን መጠኑ በመመገብ የፀጉር ዕድገትን ማምጣት ይቻላል። 5. አቮካዶ አቮካዶ ጣፋጭ፣ ገንቢ እና ጥሩ የስብ ምንጭ ነው። በተጨማሪም የፀጉር እድገትን የሚደግፍ የቫይታሚን E ትልቁ ምንጭ ነው። በቀን ቢያንስጰእስከ 200ግራም አቮካዶ መመገብ ለፀጉር እድገት እጅግ ጠቃሚ ነው። ቫይታሚን E ልክ እንደ ቫይታሚን ሲ አንቲ ኦክሲደንት ነው። በአንድ የቆየ ጥናት ውስጥ፣ የፀጉር መርገፍ ያለባቸው ሰዎች ለ8 ወራት የቫይታሚን ኢ ተጨማሪ ምግብ ከወሰዱ በኋላ 34.5% የበለጠ የፀጉር እድገት አግኝተዋል። 6. ለውዝ ለውዝ ጣፋጭ፣ ምቹ እና ለፀጉር እድገት ጠቃሚ የሆኑ የተለያዩ ንጥረ ነገሮችን የያዘ ነው። ከዚህም በላይ ብዙ ዓይነት ቪታሚኖችን፣ ዚንክ እና አስፈላጊ ስቦችን ይይዛል። የእነዚህ ንጥረ ነገሮች እጥረት የፀጉር መርገፍን ያስከትላል። ለውዝ ከፀጉር እድገት በተጨማሪ እብጠትን መቀነስ እና ለልብ በሽታ የመጋለጥ እድላቸው ዝቅተኛ ያደርግልናል። 7. ባቄላ ባቄላ ለጸጉር እድገት አስፈላጊ ከጥራጥሬ የሚመደብ ትልቁ የፕሮቲን ምንጭ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ባቄላ የዚንክ ጥሩ ምንጭ ሲሆን ይህም የፀጉር እድገትን እና የተጎዳ ፀጉርን ለመጠገን ያገለግላል። 8. አኩሪ አተር ጥናቶች እንደሚያሳዩት በአኩሪ አተር ውስጥ ያሉ ውህዶች የፀጉር እድገትን ሊያበረታቱ ይችላሉ። አኩሪ አተር የ spermidine ምርጥ ምንጮች ውስጥ አንዱ ነው የፀጉር እድገትን ያፋጥናል። 9. ስጋ ስጋ በብዙ ሰዎች አመጋገብ ውስጥ ዋና አካል ሲሆን ለፀጉር እድገት በሚረዱ ንጥረ ነገሮች የበለፀገ ነው። በስጋ ውስጥ ያለው ፕሮቲን እድገትን ይረዳል እና የፀጉር ሀረጎችን ለመጠገን እና ለማጠናከር ይረዳል.። በተለይም ቀይ ስጋ በከፍተኛ መጠን በአይረን የበለፀገ ነው።ይህ ማዕድን ቀይ የደም ሴሎች ኦክስጅንን ወደ ሁሉም የሰውነት ሴሎች ለማድረስ ይረዳል። ይሁን እንጂ ቀይ ስጋን ከመጠን በላይ መመገብ የልብና የደም ቧንቧ በሽታዎች,፣ የስኳር በሽታ የመጋለጥ ዕድልን ይጨምራል። 10 የሳልሞን አሳ ሳልሞን በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች ያሉት የኦሜጋ -3 ፋቲ አሲድ ምንጭ ነው። ኦሜጋ 3 የፀጉር መርገፍን ይከላከላል። ኦሜጋ -3 ለጤንነት እና ከበሽታ ነፃ እንድንሆን ከመርዳት በተጨማሪ ለፀጉር ዕድገት እንዲሁም ፀጉር አንፀባራቂ እንዲሆን ያደርጋል። ሳልሞን ሰውነታችን ኢንሱሊንን በብቃት እንዲሰራ የሚረዳ አንዱ ምግብ ነው። በተጨማሪም ሳልሞን የ ቫይታሚን ዲ ምንጭ ነው። ቫይታሚን ዲ የፀጉር ቀረጢቶች ለማነቃቃት ሊረዳ ይችላል። በሌላ አነጋገር፣ ንጥረ ነገሩ የፀጉር መሳሳትን አልፎ ተርፎም ራሰ በራነትን በከፍተኛ መጠን ይከላከላል። #youtube #hair #health