У нас вы можете посмотреть бесплатно ዘወረደ፡ የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሳምንት | ጾመ ሕርቃል или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
ዘወረደ የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሳምንት ነው። ዘወረደ ማለት ቃላዊ ትርጉሙ ከሰማየ ሰማያት የወረደው እንደማለት ሲሆን ክብር ይግባውና ወልደ እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ለማዳን ቅድስት ድንግል ከምትሆን እናቱ የሰውን ነፍስና ሥጋ ነሥቶ ሰለመዋሓዱ የሚያሰብበት ነው። በክበበ ትስብዕት ከመገለጠ በፊት መውጣት መውረድ ያለበት አይደለምና መውጣት መውረድ ለመለኮት የሚነገር ባለመሆኑ ከተዋሕዶ በፊት ወረደ የሚለው አገላለጥ ተዋሐደ ለማለት ነው በማለት ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ያስተምራሉ። ----------------------------------------------------------------------------------------------------------- ጾመ ሕርቃል፡ የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሳምንት ጾመ ሕርቃል በመባልም ይታወቃል። ሕርቃል በ614 ዓ.ም. ገደማ የተነሣ የሮማ ንጉሥ ነበረ። ይህ ንጒሥ ለቤተክርስቲያን መልካም ስራዎችን የሰራ ደገኛ መሪ የነበረ ሲሆን በንግሥት እሌኒ አማካይነት ከተቀበረበት ወጥቶ በኢየሩሳሌም በክብር ተቀምጦ የነበተውን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በፋርስ ንጒሥ ኪሪዮስ ተዘርፎ ወደ ፋርስ በሄደ ጊዜ ንጉሥ ሕርቃል ወደ ፋርስ ዘምቶ መስቀሉን አስመልሷል የተማረኩ ካህናትና ምዕመናንንም ወደ ሀገራቸው መልሷል። ወደዚህ ዘመቻ ከማምራቱ በፊት ሕዝቡ ለአንድ ሳምንት ጾመውለት ነበርና ሕዝቡ የዞሙበት ጊዜም በዚህ ጊዜ ውሎ ነበርና ሳምንቱ ጾመ ሕርቃል በማለት እንዲጠራ ሆኗል በቅድስት ቤተክርስቲያን። የንጒሥ ሕርቃልን ታሪክ የተመለከተ መጽሐፍ በዚህ (https://t.me/iyasu_angani) የቴሌግራም ቻነል ያስቀመጥን ስለሆነ አውርዶ ማንበብ ይቻላል። በረከቱ ይደርብንና ኢትዮጵያዊው የዜማ ሊቅና ቅዱስ አባት ማኅሌታይ ያሬድ የዐቢይ ጾምን ሳምንታት ሲሰይም ስድስተኛውን ሳምንት ገብር ኄር ብሏታል፤ ምንባባቱና የሚቀርቡ ትምህርቶች ከዚህ ጋር የተያያዙ ናቸው። በ 2016 ዓ.ም. ዐቢይ ጾም ዘወረደ መጋቢት ፩ ላይ ትውላለች። ------------------------------------------------------------------------------------------------------------------ ዐቢይ ጾም (አብይ ጾም 2016 ወይም አቢይ ጾም 2016 የሚሉም አሉ - "wrong!") ፳፻፲፮ ዓ.ም. መጋቢት ኹለት ቀን የጀመረ ሲሆን እያንዳንዱ ሳምንት የሚቅልበት ዕለት ከመጠሪያ ስሙ ጋር እንደሚከተለው ነው። ዘወረደ - የመጀመሪያው ሳምንት መጋቢት ፩/፳፻፲፮ ዓ.ም. ቅድስት - ሁለተኛው ሳምንት መጋቢት ፰/፳፻፲፮ ዓ.ም. ምኩራብ - ሦስተኛው ሳምንት መጋቢት ፲፭/፳፻፲፮ ዓ.ም. መጻጉዕ - ዐራተኛው ሳምንት መጋቢት ፳፪/፳፻፲፮ ዓ.ም. ደብረ ዘይት - አምስተኛው ሳምንት መጋቢት ፳፱/፳፻፲፮ ዓ.ም. ገብር ኄር - ስድስተኛው ሳምንት ሚያዝያ ፮/፳፻፲፮ ዓ.ም. ኒቆዲሞስ - ሰባተኛው ሳምንት ሚያዝያ ፲፫/፳፻፲፮ ዓ.ም. ሆሣዕና - ስምንተኛው ሳምንት ሚያዝያ ፳/፳፻፲፮ ዓ.ም. ትንሣኤ - ዘጠነኛው ሳምንት ሚያዝያ ፳፯/፳፻፲፮ ዓ.ም. ይህንን በተመለከተ ተጨማሪ ትምህርቶችን ለማግኘት ይሄንን (https://t.me/iyasu_angani) በመከተል የቴሌግራም ቻነላችንን ይቀላቀሉ። ----------------------------------------------------------------------------------------------------------- ዐቢይ ጾም 2016 ዓ.ም. ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስብከት አዲስ በዲ/ን ኢያሱ አንጋኒ (ዶ/ር) - Orthodox Sibket / ኦርቶዶክስ ስብከት / ስብከት ኦርቶዶክስ / መንፈሳዊ ስብከት #ኢያሱአንጋኒ #iyasuangani #driyasuangani ----------------------------------------------------------------------------------------------------------- የቤተክርስቲያን ስብከት፣ ዝማሬ። ዘጋቢ ፊልሞች፣ ወቃታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጡ ትንታኔዎችና መልእክቶች ይተላለፋሉ። ዲ/ን ኢያሱ አንጋኒ ደረጃ Dr. Iyasu Angani Dereja