У нас вы можете посмотреть бесплатно ተሻገር ወዳየልህ || Apostolic_Song || TESHAGER WEDYELH || ሙሉ አልበም || በማስተዋል ዘምሩ || FULL ALBUM или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
#Like_በማድረግ_ይጀምሩ!! #ተሻገር_ወዳየልህ !!! #ቪድዮውን_Like_Shere_ያድርጉ የመማጸኛ ከተማ የሚያነፃ የሚያጥብ የሚቀድስ በዘላለም መንፈስ የፈሰሰ የኢየሱስ ደም የክንፉ መዘርጋት ምድርን ሞልታለች የምህረቱ ልክ ዳርቻን ታልፋለች የእንደገና አምላክ እድልን ሰጥቶ በፊቱ ያቆማል በደሙ እጥብ አድርጎ ጸጸት ሲሰማኝ አቅም ሲያሳጣኝ አይኔን ወደ አንተ ማንሳት ሲያቅተኝ ሮጬ መጣለሁ ወደ ምትወደኝ ከነ ድካሜ ማረኝ እያልኩኝ ማረኝ አቤቱ ማረኝ /2 እጠበኝ እነጻለሁ ፈውሰኝ እድናለው እንዳየህ አትፈርድም እንደሰማህ ከሰዎች ልዩ ነህ አንተማ የመማጸኛ ግንብ ከተማዬ የምሸሸግብህ መዳኛዬ በደምህ ውስጥ እየኝ አሻግረህ ከእውነት ትብለጥና ምህረትህ በደሌም ሁል ጊዜ በፊትህ ነው ዋጋዬን በፍቅር ካልቀየርከው ደምህ ያንጻኝ /3 ደምህ በደምህ ብቻ ተመክቼ የመስቀል ፍቅርህን አይቼ በጸጋህ አቅምን አግኝቼ አግዘኝ ልኑር ተጠግቼ Track 02 አሳውቆኛል አሳውቆኛል የልብን ደስታ የነፍስን ሐሴት የህይወት እርካታ በምትጠፋው በዚች ዓለም እንኳ የሱስ ያለበት አየሁኝ ሲሳካ አቤቱ ምን እልሃለሁ የሱስ ሆይ ምን እልሃለሁ ምህረትህን አስባለሁ ስለፍቅርህ አዘምራለሁ በወሰነበት በፈቃዱ ሰዓት አየሁ ለነፍሴ ድንቅን ሲያደርግላት በስሙ ስልጣን በእርሱ እንድታመን ተስፋ ሆኖአታል እስከ ዘለዓለም እግዚአብሔር ሃይሌ ጋሻዬ ሆኖኛል ህይወቴም ደግሞ በእርሱ ደስ ይላታል ልቤ ታመነ እኔም ተረዳሁኝ ለነፍሴ ሰላም እረፍት አገኘሁኝ ቃልኪዳኑንም እርሱ አስታውቆኛል እግሮቼን የሱስ ከወጥመድ አውጥቷል በፍቅሩ ገመድ ወደራሱ ስቦ አሜን አረካኝ በመንፈሱ አጥግቦ Track 03 ኃያል በኃይሉ አይመካ ሃያል በሃይሉ አይመካ ጠቢብ በጥበቡ አይመካ አቅም ጉልበት ሲከዳው ጥሎ የሚሄደው እንደ ጉድፍ በእርሻ ላይ ወድቆ የሚቀረው ዝና ክብሩን እንደያዘ የሚኖርስ ማነው አንዲት ቃል የምትበቃው ሰው ከንቱ ከንቱ ነው ምህረት ፍርድን ፅድቅን በኔ ላይ የሚያደርግ ሆኖ የበላይ የበላይ መንገድ ህይወቴ በእጁ የሆነው እርሱን ነው ማምነው የምታመነው እርሱን ነው ኢየሱስ (2) ነውና የነፍሴ ንጉስ ኢየሱስ (2) የህይወቴ ንጉስ ጥበበኛ ፀሃፊስ የታለ በዘመኑ ሲሠራ የነበረ ብርቱ ሆኖ በስሙ የተለየ ጊዜው አልቆ ዝናው ሁሉ ቀረ ማስተዋሉ የማይመረመር ዘላለም የሚኖር ኢየሱስ ነው የዓለምን ጥበብ ሞኝነት ያደረገው ለዘመኑ ፍፃሜ የሌለው እርሱ አያልቁበትም ከቶ አመቶቹ ጥበበኞችን እያሳፈረ እያሳፈረ ይኖራል ተከብሮ እንደከበረ ለደካማው የሚሰጠው ሃይል ጉልበት ላጣው የሚሆን ብርታት ሁሉን ፍጥረት በየሥም የሚጠራ ሠራዊቱን በቁጥር የሚያወጣ እታመነዋለሁ ይህን ጌታ አያሳጣም ከመልካም ነገር በፅድቁ ቀኝ ደግፎ ያኖራል በክብር አንድ አይታጣው በሃይሉ ብዛት የምድር ዳርቻ ፈጣሪና አምላክ አለኝ አለኝ አምላክ የሚያስመካ አለኝ አለኝ አባት የሚያኮራ አለኝ አለኝ የሚታመን ጌታ ፍፁም የማይደክም የማይረታ Track 04 ኃይልን የሚያስታጥቀኝ ሃይልን የሚያስታጥቀኝ መንገዴን ሁሉ አቅንቶ የጠላቴንም መንገድ ሊያወርሰኝ እርሱ ተዋግቶ ይኼ እግዚአብሔር እውነትም እግዚአብሔር ነው ይኼ አምላክ እውነትም እርሱ አምላክ ነው በከበረው ደሙ እያነፃ ያቀርበኛል ኢየሱስ አርጎኝ ነፃ በአንደበቴ ሞልቷል ምስጋናው አብዝቶልኝ ለእኔ ውለታው ጨለማዬን ሁሉ እያበራ በመንገዴ ሆኗል ከእኔ ጋራ በእውነትም አምላኬ እግዚአብሔር ነው ብቻውን በሰማይ ዙፋን ያለው በበረታው ክንዱ ደግፎኛል ዛሬንም ለክብሩ አቁሞኛል ምን እላለሁ ለዚህ ድንቅ ስራው ብቻ ስለሁሉም ተመስገን ነው ስላደረገኝ የምከፍለው በልቤ ውስጥ ያለ ምስጋና ነው እጅ መንሻዬን ይዤ ልቅረብ ፊቱ ልስገድ ልንበርከክም ለማዳኑ Track 05 ክብርህ ይንካኝ ክብርህ ይንካኝ ኢየሱስ ክብርህ ይንካኝ ክብርህ ይንካኝ ጌታዬ ክብርህ ይንካኝ ክብርህ ሲነካኝ ሁሉ አዲስ ይሆናል ክብርህ ሲነካኝ ያኔ የነፍሴ ውበቷ ይታያል/2× ያላንተ እኔ ምንም ነኝ ከቶ የማያምርብኝ ክብሬ እና ሞገሴ ሆይ ፍጹም ከእኔ አትራቀኝ አይኖችህ ወደ ባሪያህ ይመልከቱ በፍቅር ጠላቴም አይቶ ይፈር አንተ በእኔ ስትከብር ጌታ ያንተን መገኘት ልቤ እጅግ ወዷልና ቤቴን ሙላው ተገልጠህ በክብርህም ደመና የአለም ስበት ሳይዘኝ ልራመድ በከፍታ ዛሬም አሸናፊ አድርገኝ እጆቼን ያዝ አበርታ እልፍ እልፍ እላለሁ ሀይሌን ወደ አንተ አስጠጋለሁ/2× ና ኢየሱስ ና ና ጌታዬ ና ቤቴን ይሙላው የክብርህ ደመና/2× ስምህ በእኔም ይጠራ የኔም አምላክ ተባል መአዛዬም ይለወጥ አንተን አንተን ይበል ሞገስ እስካገኝ ድረስ በፊትህ መድሀኒቴ ክብርህ ይንካኝ እላለሁ እስኪፈጸም መሻቴ Track 06 ልኑር እንዳሳብህ መኖር ማለት ካንተ ጋር መታደም ነው ለክብርህ ዕረፍት ህይወት መቆየት እግርህ ስር መታደል ነው መፈቀር መኖሬ ካልቀረ ልኑር እንዳሳብህ ማምለኬም ካልቀረ ልቤን ላፍስስልህ ጨክኜም ከተውኩት ሁሉን ወደኋላ ከአንተ ጋር ልራመድ በመንፈስ ልመራ በጉዞዬ ሁሉ ሆነህ ከእኔ ጋራ ልቤ ጨካኝ ሆኖ ከመረጥኩህ ከሚታየው ሁሉ ካስበለጥኩህ መሄድ ከጀመርኩኝ ከአንተ ኋላ እንዳልሰናከል እግሬን አፅና በምድረ በዳ ላይ ጥም ባለበት አግዘኝ ጌታ ሆይ ዝዬ እንዳልወድቅ የህይወት ውሃ ወንዝ ከሆዴ አፍልቅ በሰማዩ ራዕይ እንድደነቅ መኖሬ ካልቀረ ለክብርህ አድርገኝ ደስ ይበልህ ልብህ ይረፍብኝ ትዕግስትህን አብዛው ልቤን አጽና እፅዮን አገሬ እስክገባ አላማዬ ኢየሱስ ተስፋዬ አንተ ሌላ ምንም የለኝ ስኖር በአለም የህይወት ውጣ ውረድ እጅግ ቢበዛ ነፍሴንም ስጋዬን አንተው ግዛ Track 07 ስለ እኔ ምን ትላለህ? አሁን ብትመጣ ወዳንተ ልትወስደኝ ከሆንኩኝ በሰማይ የምትቀበለኝ በቃልህ ብርሀን ልቤን ሰትመረምረው እውነተኛ ንፁህ ሆኖ ካገኘኸው አንተን ደስ ካለህ ህይወቴን ስታየው ይሄ ነው መሻቴ ምን እፈልጋለሁ ሰዉ ብቻ ነው ወይስ አንተም የምትለኝ ጻድቅ ፍፁም ሽንገላ ነው ወይስ ህይወት በልቤ ዉስጥ ይኑር እዉነት ኢየሱስ አንተስ ለኔ መልስ አለህ ወይ ጠላቴ ሲከሰኝ ትነግረዋለህ ወይ ቅን ናት ቅን ነው ፍፁም ናት ፍፁም ነው ጻድቅ ናት ጻድቅ ነው ትላለህ ወይ በአንደበቴ ከምናገረው በአደባባይ ላይ ከማሳየው የልቤ ሀሳብ የተሰወረው የጓዳ ኑሮዬ አንተ ምታውቀው ደስ ያሰኝሃል ወይ ስትመዝነው ቃልህ ነው ሚዛኔ የምለካበት አንተን ነዉ የማይህ እንደመስታወት የሚለይ ነገሬን በፀጋህ እየጣልኩት ፈፅሜ ልመስልህ የምተጋው በህይወት የእምነቴ ራስና ፈፃሚ ህይወቴ ኢየሱስ አንተ ነህ ፍለጋህን ዘውትር ልከተል ክብርህ ከራቀኝ ምን አለኝ አይተካውም ምንም ነገር መንፈስህ በውሰጤ ይኑር ብቻህን ፀንተህ ንገስበት ይህ ልቤ ዙፋንህ ይሁን ልቤን እንካ ጌታ ሆይ ልቤን እንካ ልቤን እንካ ኢየሱስ ሆይ ልቤን እንካ ልቤን እንካ ጌታ ሆይ ልቤን ያዘው በዘመኔ ሁሉ ያዘው ከማውቀውም በላይ ጥልቅ ነው አንተ ነህ የምትመረምረው የህይወት መውጫ የሆነውን አባቴ ሰጠሁህ ልቤን ልቤን እንካ .. ካንተ ሌላ እንዳልል በዘመኔ ሁሉ @ApostolicSongs2616 #new_status #new_gospel_massage #massage #bible #biblestudy #biblemessage #apostolic #apostolicchurch #kes_Yohannis #Kesyohannnis #hawassa #Hawasa_annual_youth_conference #apostolicchurchmezmursongs #mezmur #gospelmezmur #apostolic_songs #በማስተዋል_ዘምሩ #Jesus #nameofjesus #onegodbeliever #onegod #isoyisak #iso_yishak #apostolicchurchmezmur #church #churchmezmur #bemastewalzemiru #zemiru #zima #apostolic_songs #2023 #2015 #2024 #2016 #appstolic_church_mezmur_songs #bishop #bishopdegukebede #bishop_degu_kebede #bishop_Alemaw #bishop_Terefe #bishop_getahun #bishop_birhanu #Apostolic_Songs #በማስተዋል_ዘምሩ @Salemspiritualevents @isoyisehak @ApostolicchurchSongwithLyrics7 @asaphchior @ApostolicChurchMezmurSongs