У нас вы можете посмотреть бесплатно መልክአ ኤዶም или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
የእመቤታችን ጸሎት አበዊነ ቅዱሳን፡፡ እመቤቴ ማርያም ሆይ፤ ቅዱሳን አባቶቻችን አንቺን መረጡ መድኃኒታቸው የሆንሽ አንቺንም መልካም ፍሬ አፈሩ፡፡ (አስገኙ) ድንግል እመቤቴ ሆይ፤ ለደካማው የመጠጊያ ተራራ ነሽና ጻድቅስ በበጎ ሥራው ይድናል እንደኔ ያለው ኃጥእ ግን መሸሻው መጠጊያው ከአንቺ በቀር ወዴት ነው፡፡ ፳፭፤ ለመልክእኪ፡፡ እመቤቴ ማርያም ሆይ፤ መጻሕፍት እደተናገሩት ወይም እንደሚያስረዱት የእግዚአብሔርን ሥነ ራእይ ለሚመስለው ሥነ መልክእሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ ድንግል እመቤቴ ሆይ፤ የሳሙኤል የሽቱ ሙዳይ አንቺ ነሽ እኮን፤ የሚወዱሽ የሚያከብሩሽም ሁሉ በረከትሽን ያግኙ፤ የሚጠሉሽ የሚመቀኙሽ ግን ፈጥነው ይጥፉ፡፡ ፳፮፤ ስብሐት ለኪ፡፡ የአብ ሙሽራው ማርያም ሆይ ላንቺ ሰላምታ ይገባል፡፡ የወልድ እናቱ ማርያም ሆይ ላንቺ ሰላምታ ይገባሻል፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ንጽሕት አዳራሽ ማርያም ሆይ ሰላምታ ላንቺ ይገባሻል፤ ወርቅና ብር ኃላፊ ጠፊ ነው፤ ስለዚህም ከዚህ ዓለም ብልጽግና ይልቅ አንቺን መውደድ እመርጣለሁና፡፡ ቸርነትሽን አታርቂብኝ፡፡ ፳፯፤ እመቤቴ ማርያም ሆይ፤ አሁንም በመዓልትና በሌሊት ጠብቂኝ፤ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ሠውሪኝ ለዘላለሙ አሜን፡፡