Русские видео

Сейчас в тренде

Иностранные видео


Скачать с ютуб DW Amharic የሕዳር 14 ቀን 2017 የዓለም ዜና в хорошем качестве

DW Amharic የሕዳር 14 ቀን 2017 የዓለም ዜና 3 недели назад


Если кнопки скачивания не загрузились НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу страницы.
Спасибо за использование сервиса savevideohd.ru



DW Amharic የሕዳር 14 ቀን 2017 የዓለም ዜና

የሕዳር 14 ቀን 2017 የዓለም ዜና • የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የሕግ ኮሚቴ በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመከላከል እና አጥፊዎችን ለመቅጣት የሚያስችል ሥምምነት ለማዘጋጀት የሚያስችል ድርድር እንዲጀመር የውሳኔ ሐሳብ አጸደቀ። • በቀድሞው የደቡብ ሱዳን የስለላ መሥሪያ ቤት ኃላፊ አኮል ኮር የመኖሪያ ቤት ዙሪያ ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ ከተደረገ በኋላ የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር ከጸጥታ ሹማምንቶቻቸው ጋር አስቸኳይ ስብሰባ አካሔዱ። ከሁለት ወራት በፊት መፈንቅለ-መንግሥት ለማካሔድ እያሴሩ ነው በሚል ስሞታ ከኃላፊነታቸው በተባረሩት አኮል ኮር መኖሪያ ቤት አቅራቢያ ሐሙስ ዕለት በተደረገ የተኩስ ልውውጥ አራት ሰዎች ተገድለዋል። • የኒጀር ወታደራዊ መንግሥት በሰብአዊ ርዳታ አመዳደብ ጉዳይ ላይ ካቀረበው ክስ በኋላ የአውሮፓ ኅብረት በሀገሪቱ የተመደቡ አምባሳደሩን ጠራ። የኒጀር ወታደራዊ መንግሥት በሀገሪቱ የሚገኙ የአውሮፓ ኅብረት አምባሳደር የጎርፍ ተጎጂዎችን ለመርዳት የተመደበ 1.3 ሚሊዮን ዩሮ መንግሥትን ሳያማክሩ ግልጽ ባልሆነ መንገድ ለበርካታ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አከፋፍለዋል በማለት ወቅሶ ነበር። • እስራኤል ዛሬ ቅዳሜ ማለዳ በማዕከላዊ ቤይሩት እና ሾምስታር በተባለች ከተማ በፈጸመቻቸው ሁለት ጥቃቶች ቢያንስ 19 ሰዎች መገደላቸውን ሊባኖስ አስታወቀች። • የከባቢ አየር ለውጥ የበረታ ዳፋ የሚያሳድርባቸው ትናንሽ የደሴት ሀገራት እና አፍሪካውያን በአዘርባጃን ዋና ከተማ ባኩ በመካሔድ ላይ ከሚገኘው ድርድር ረግጠው በመውጣት ተቃውሟቸውን አሰሙ። ሊጠናቀቅ ከታቀደለት ጊዜ 24 ሰዓታት የዘገየው ድርድር የመጨናገፍ ሥጋት ተጋርጦበታል። • ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ሩሲያ ኦሬሽኒክ ሐይፐርሶኒክ ሚሳይሎች በውጊያ በውጊያ ውስጥ ጭምር መሞከሯን እንደምትቀጥል አስታወቁ። ፕሬዝደንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ በበኩላቸው ሩሲያ በሰው አልባ አውሮፕላኖች እና በሚሳይሎች ከጎርጎሮሳዊው ሐምሌ 2023 ወዲህ በፈጸመቻቸው ጥቃቶች 321 የዩክሬን የወደብ መሠረተ-ልማቶች መጎዳታቸውን ዛሬ ቅዳሜ ይፋ አድርገዋል።

Comments