У нас вы можете посмотреть бесплатно በወላይታ ሶዶ ከተማ የሁሉ ቁጠባና ብድር መሠረታዊ ሕብረት ስራ ማህበር የመስቀል በዓል// 2018 или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
የሁሉ ቁጠባና ብድር መሠረታዊ ሕብረት ስራ ማህበር በዛሬው ዕለት 'ጊፋታ' ን በወላይታ ሶዶ ከተማ በመገኘት በህግ ስር ያሉ ታራሚዎችን በመጠየቅና የመጽሀፍ እንዲሁም የተለያዩ የንፅህና መጠበቅያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ በማድረግ አሳልፏል፡፡ በመርሃግብሩ ላይ የተገኙት የሕብረት ስራ ማህበሩ ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ አብርሃም ቃሬሶ እንዳሉት የሁሉ ቁጠባና ብድር መሠረታዊ ሕብረት ስራ ማህበር እንደስሙ ለሁሉም ሰው የፋይናንስ ተደራሽነት ላይ እየሰራ እንደሚገኝና በወላይታ ሶዶ ከተማ የ'ጊፋታ' ን በዓል ስናከብር በእርምት ላይ ያሉ ወገኖቻችንን ለመጎብኘት እንዲሁም በቅርቡ ሕብረት ስራ ማህበሩ ቅርንጫፉን በሚከፍትበት ጊዜ ከማረሚያ ቤቱ ጋር በጋራ ለመስራት በማሰብ መሆኑን ገልጸዋል። የቦርዱ ጸሃፊ አቶ አበዙ አስፋው በበኩላቸው በመታረም ላይ ያሉ ግለሰቦች በማረሚያ ቤቱ ውስጥ እየሰሩ ያሉትን የተለያዩ ስራዎች ካሉበት ሆነው ሳይቸገሩ እንዲሰሩና ከራሳቸው አልፈው ለቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ለሀገር የገቢ ምንጭ በመፍጠር የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ከፍ ያለ እንዲሆን ከማሰብ አንጻር የሁሉ ቁጠባና ብድር መሠረታዊ ሕብረት ስራ ማህበር ማረሚያ ቤቶች ላይ በስፋት እየሰራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ የሶዶ ማረሚያ ተቋም ማረምና ማነጽ ስራ ሂደት አስተባባሪ ኮማንደር ዳንኤል ዶላ እንዳሉት ታራሚዎችን መጎብኘት እንዲሁም ለስራ እንዲነሳሱ ማድረግ የሁሉም ሰው ሃላፊነት ነው ያሉ ሲሆን በቀጣይነት ከሕብረት ስራ ማህበሩ ጋር መስራት በመቻላችን ደስተኞች ነን ብለዋል።