У нас вы можете посмотреть бесплатно ድንቅ ምሽት |ሳያስቡት አሸንፈው የተሸሉሙ አርቲስቶች|ያልታሰበ ደስታ(@Gizemedia1974) или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
"እልል ያለ" ልዩ ሽልማት ዛሬ ይከናወናል ሐበሻ ቢራ አ/ማ የኢትዮጵያን ባህል በልዩነት ያስተዋወቁና እንዲጎለብት ያደረጉ ባለሙያዎች የሚያበረታታ "እልል ያለ" የተሰኘ የመጀመሪያ ልዩ ሽልማት ዛሬ ግንቦት 24 ቀን 2017 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል ይሰጣል። በዛሬው ሽልማት መርሐግብር ከታቀፉት ውስጥ ሙዚቃ፣ ፋሽን፣ ፊልም፣ ሥነ- ፅሁፍ፣ እደ ጥበብ፣ ኪነ ጥበብ፣ ማስታወቂያ የመሳሰሉ ዘርፎች ናቸው ተብሏል። እነዚህ ዘርፎች የኢትዮጵያውያንን የውስጥ ስሜት የሚዳስሱና፣ የሚገልፁ ናቸው። በሙያው የተሠማሩት ባለሙያዎች ከህዝብ ባህል ኑሮና ስሜት ጋር በማገናኘት ያለፈውን ከዘመናዊው ጋር በማዋሃድ በማስተሳሰር፣ በማሠናሠል የወጣቱን አሁናዊ ተሳትፎ ለማጎልበት አቅም ያላቸው ስራዎችም ናቸው። በመጀመሪያ ዙር የዛሬ " እልል ያለ " ሽልማትን የህይወት ዘመን ተሸላሚዎች በሙዚቃ ኢንደስትሪ ፣በመድረክ ስራዎች ጥበብ እና በመገናኛ ስርጭት መስክ የሚገኙ መኾናቸው ከዚህ ቀደም ተገልጷል። እነዚህ ሽልማቶች ባሁኑ ጊዜ በሕይወት ላሉ በሕይወት ዘመን ስራቸው የኢትዮጵያን ማንነት ብቻ ሳይሆን የባህላዊ ታሪኮችንም በአዲስ መንገድ የቀረፁ ናቸው፡፡ ከዚያም አልፎ የሥራቸው ውጤት የወጣቱን ትውልድ የሚያነሳሳ ብሎም አዎንታዊ ተፅዕኖ የሚያሣድሩ ናቸው ተብሏል። ከሳምንታት በፊት ይፋ ከተደረጉት የህይወት ዘመን ተሸላሚዎች መካከል ከ40 ዓመት በላይ ያገለገሉ የሀገር ባለውለታ አቶ ፍቃዱ ዋሬ የአምባሰል ሙዚቃ ቤት ባለቤት አንዱ ኾነዋል። አቶ ፍቃዱ ለበርካታ ድምፃዊያን ለመድረክ መብቃት ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማድረጋቸው ተመርጠዋል። ወ/ሮ የሺ ተክለወርቅ በፊልም ሥራ ጅማሮ ውስጥ ላበረከቱት አስተዋፅኦ፣ ወ/ሮ ብዙ ወንድምአገኝ በገጠሪቷ ኢትዮጵያ በመዞር በቴሌቭዥን ባህልና ታሪክን በማስተዋወቅ ባደረጉት አስተዋፅኦ መመረጣቸው መገለፁ ይታወሳል። እልል ያለ ሽልማት የዛሬውን የመርሐግብሩን ማሳረጊያ ዕለትን በማስመልከት ከዚህ ቀደም እምብዛም ባልተለመደ መልኩ ለዘገባ የሚገኙ በተለያየ ሚድያ የሚሰሩ ጋዜጠኞችን የሀገር ባህል ልብስ በማልበስ ለበዓሉ ድምቀት እንዲሆኑ አድርጓል።(@gizemedia1974)