У нас вы можете посмотреть бесплатно Logic freshman course chapter 1 የ አዲስ ተማሪወችዩኒቨርሲቲ common course logic или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
#Logic 📚 Logic and Critical Thinking. 📚 Chapter One - Introducing Philosophy. 📚 ዛሬ የምንማረው የ Logic and Critical Thinking ኮርስን ነው። ስለ ኮርሱ አንዳንድ ነገር ልበላችሁ። 📚 ምናልባትም ከመጀመሪያ ሴሚስተር ከባድ ኮርስ ከሚባሉት Logic and Critical Thinking ነው። በዚህ ኮርስ 5 ቻፕተሮችን እንማራለን። ከ 5 ቱ ቻፕተሮች በዋናነት Chapter 2, Chapter 3 እና Chapter 5 ን ለዬት ያለ ትኩረት ሰጥተን እንማማራለን። 📚 ምክንያቱም Mid exam ፈተናችሁ ላይ Chapter 2 ብዙ ጥያቄ ይወጣበታል። ሰፋ ያለ ማሰላሰል እና ተመስጥኦን የሚጠይቅ የ ፅንሰ ሀሳብ ቻፕተር ነው። Final exam ፈተናችሁ ላይ ደግሞ chapter 5 ላይ ብዙ ጥያቄ ይወጣበታል። ይህ ቻፕተር ደግሞ ፅንሰ ሀሳብንም ሽምደዳንም የሚጠይቅ ወሰብሰብ ያለ ነው። ስለዚህ ሁለቱ ቻፕተሮች ላይ ለየት ያለ ትኩረት ሰጥቼ ለፈተና የሚጠቅማችሁን ነገር እሰጣችሗለሁ። 📚 ዛሬ Chapter one ንን እንደ መግቢያ መማር እንጀምራለን። ይህ Chapter የ concept ትምህርት እምብዛም አይታይበትም። ፈተና ላይ የምትፈተኑትም በሽምደዳ መልክ ስለሆነ በ MoSHE የተዘጋጀውን PDF ፈተና ሲደርስ ብቻ ሸምድዱት😁 ማለቴ ቃል በቃል አንብቡት ምንም የዞረ ጥያቄ አይወጣበትም። እሺ አሁን ወደ ትምህርቱ። Philosophy ምን አንደሆነ እንመልከት። Philosophy በአማርኛ 'ፍልስፍና' ማለት ነው። ፍልስፍና ማለት ምን ማለት ነው🤔? 📌 የጥበብ መጀመሪያ ፈጣሪን መፍራት ነው። 📌 ፍልስፍና ደግሞ ጥበብን መሻት ነው። ስለዚህ ፍልስፍና ከፈጣሪ ህልውና እና ከተፈጥሮ ጋ የሚጋጭ ሳይሆን ስለ ፈጣሪ ና ስለ ተፈጥሮ ምክንያታዊ ዳሰሳ የማድረግ ሳይንሳዊ ሒደት ነው። 😁ስለዚህ ፍልስፍና ሲባል ፈጣሪ ን መቃወም የሚመስለን ልጆች ከዚህ በሗላ ይህንን አስተሳሰባችንን ልንቀይር ይገባል። ለማንኛውም እንደ መግቢያ ያህል እንማረው። 🌹 Because of its universal nature, it is difficult to define philosophy in terms of a specific subject matter. However, we can define it etymologically as 'love of wisdom‘. 📚 Philosophy ን ወይንም ፍልስፍናን እንዲሁ በቀላሉ define ማድረግ ወይም ብያኔ መስጠት ይከብዳል። ለምንድን ነው ፍልስፍንናን እንዲህ ነው ብለን መግለፅ ያቃተን🤔? 📚 ምክንያቱም ፍልስፍና ወይንም Philosophy ሁሉንአቀፍ ወይንም ሁሉንምነገሮች የመዳሰስ ተፈጥሯዊ ባህሪ(universal nature) ስላለው ነው። ይህ ማለት ደግሞ ፍልስፍና specifically አንድ ነገር ለይቶ ማጥናት አይችልም ወይም ስለ አንድ ነገር ብቻ አያጠናም። በዚህም ምክንያት ፍልስፍና(philosophy) ን define ማድረግ ያስቸግራል። 📚 ነገር ግን አንዱን የ ናቹራል ተማሪ what is chemistry ብዬ ብጠይቀው chemistry is a branch of natural science that studies about the nature and composition of matter ብሎ define ማድረግ ይችላል ምክንያቱም chemistry የሚያጠናው ስለ አንድ ነገር ስለሆነ እርሱም ስለ matter እና ከ matter ጋር ስለተያያዙ ነገሮች ብቻ ነው የሚያጠናው። አንዱን የ ሶሻል ተማሪ what is Geography ብዬ ብጠይቀው define ማድርግ ይችላል ምክንያቱም ስለ አንድ ነገር ስለሚያጠና። 📚 ነገር ግን ፍልስፍና(Philosophy) ን በዚህ መልክ define ማድረግ ይከብዳል። ስለዚህ በምን መልኩ እናብራራው🤔? 🌹philosophy(ፍልስፍና) 'philo' እና 'sophia' ከተባሉ ሁለት የግሪክ ቃላት የተመሰረተ ነው። 👉 Philo ማለት Love ነው። 👉 sophia ማለት wisdom ነው። 📚 ስለዚህ የ philosophy ቃል በቃል ትርጉሙ love of wisdom ማለት ነው። Love of wisdom ማለት ደግሞ በአማርኛ "ጥበብን መሻት መፈለግ" ማለት ነው። 🌹ስለዚህ ከ love of wisdom(ጥበብን መሻት) ተነስተን philosophy ን በተወሰነ መልኩ ማብራራት እንችላለን👇። 📚 Thus, as a pursuit of wisdom, philosophy refers to the development of critical habits, the continuous search for truth, and the questioning of the apparent. 🌹 ስለዚህ philosophy(ፍልስፍና) ማለት በተለያዩ ነገሮች ላይ ጭፍን አመለካከት ከመያዝ ይልቅ ነቂሳዊ(ምክንያታዊ) አመለካከትን የማዳበር ባህል ÷ እውነትን ያለማቋረጥ የመፈለግ ሒደት ÷ በሰዎች ዘንድ ግልፅ መስለው የሚታዩ ነገሮች ላይ ጥያቄ ማንሳት መመራመር እና በተለያዩ dimensions መመልከት ማለት ነው። 📚 ነገር ግን እንደ ፋላስፎች እይታ መነፅር ከሆነ love of wisdom የሚለው በቂ አይደለም philosiphy ን ለማብራራት። ለምን🤔? 📚ምክንያቱም wisdom specific መሆን ስለሚችል። ለምሳሌ አንድ ሐኪም(ዶክተር) ስለ ህክምና በቂ ዕውቀት(wisdom) አለው። ነገር ግን ከህክምና ውጭ ስላሉ ነጠሮች በበቂ ሁኔታ ላያውቅ ላይረዳ ላይመራመር ይችላል። ስለዚህ philosophy ደግሞ ሁሉን አቀፍ ነው ስላልን love of wisdom ብቻውን በቂ definition ሊሆን አይችልም። ስለዚህ ከ love of wisdom በተጨማሪ philosophy ሌሎች ብያኔዎች(definitions) ይኖሩታል። እነሱን እናያለን ስለዚህ Basic features of Philosophy ን እንመልከት። #Logic 📚 Basic Features of philosophy የ Philosophy መሰረታዊ መገለጫዎችን ( Basic features ) ወይንም philosophy ን ከሌሎች የትምህርት አይነቶች የሚለዩትን ባህሪያቱን እንመለከታለን ። 🌹1) Philosophy is a set of views or beliefs about life and the universe, which are often held uncritically. Philosophy ማለት ስለ ህይወት ስለ አለም በሰው ልጆች አዕምሮ ውስጥ ጥያቄ የሚያስነሱ ተጨባጭ የሆነ ማስረጃ ያልተገኘላቸው ጉዳዮች ላይ ያለን አመለካከት ወይም ነፀብራቅ ማለት ነው። 👉ለምሳሌ ስለ ህይወት ብናነሳ ከሞት በሗላ ህይወት አለ ወይስ የለም😮💨? 👉ገነት ና ሲኦል የሚባሉ ነገሮች አሉ😿? 👉ፈጣሪ አለ? ይህ የሚታየው ገሀዱ አለም ከየት ነው የመጣው? ወዘተ 📚 ስለዚህ ስለእነዚህ ነገሮች ያለን ምልከታ philosophy ይባላል። ታዲያ ስለእነዚህ ነገሮች እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነ የግል ምልከታ ይኖረዋል።(ሰምታችሁ እንደሆነ አንዳንድ ሰዎች "የኔ ፍልስፍና" ይላሉ። አንድ ሰው ወጣ ያለ ሀሳብ ካለው ደግሞ ኸረ እሱ ኮ ፈላስፋ ነው ይባላል ኣ😁።) እንዲሁም ደግሞ ስለ እነዚህ ነገሮች በተቻለ መጠን ምክንያታዊ ሀሳብን ተንተርሶ የሚሰጠት ምልከታ አለ። ስለዚህ 😎 ሁለት ነገሮች አሉ ማለት ነው። 1ኛ) Having philosophy ( informal sense of philosophy ) - በሰው ልጆች አዕምሮ ውስጥ ጥያቄ የሚያስነሱ ተጨባጭ የሆነ ማስረጃ ያልተገኘላቸውን ጉዳዮች ወይም ነገሮች ላይ የ እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነ የግል አመለካከት ወይም እይታ Having philosophy ይባላል። "ሀይማኖት የግል ነው ሀገር የጋራ ነው ይባላል😁" 📚 Having Philosophy ማለት ለነገሮች ያለንን የግል አመለካት ወይንም ፍልስፍና እኔ የማስበው ፣ የኔ እይታ ፣ እኔ የሚመስለኝ ብለን የምንገልፃቸውን ያመለክትልናል ። 2ኛ) Doing philosophy - በሰው ልጆች አዕምሮ ውስጥ ጥያቄ የሚያስነሱ ተጨባጭ የሆነ ማስረጃ ያልተገኘላቸውን ጉዳዮች ላይ በተቻለ መጠን ምክንያታዊ ሀሳብን ተንተርሶ የሚገኝ ምልከታ doing philosophy ይባላል ። 📚 ባለን ፍልስፍና ነገሮችን Critical Thinking በሆነ መንገድ Analyze Evaluate Judge እና Understand ማድረግ ስንችል ነው Doing philosophy የሚባለው። ✌️Having Philosophy ማለት ማንኛውም ግለሰብ ስለ ነገሮች ያለው የራሱ አመለካከት ና አቋም ነው። ✌️ Doing Philosophy ግን ሳይንሳዊ ፍልስፍና ማለት ነው። ሳይንሳዊ ሒደትን ተከትሎ ነገሮችን የማጥናት ሒደት ነው። Therefore , critical thinking,critical,basic features of philosophy,nature of philosophy,reflecting,entwrprenarship,freshman course,critizm,fresh course,logic,having,english,philosophy,maths,university