У нас вы можете посмотреть бесплатно Sebatu Mentola'et/ሰባቱ መንጦላዕት/መዝሙር /Mezmur/ሰአሊተ ምሕረት ማርያም አዲስ አበባ /ኢትዮጵያ/ከሠርክ ጉባኤ የተወሰደ или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
ሰባቱ መንጦላዕት ወዴት ተጋረዱ ሰባቱ መብራቶች ወዴት ተሰናዱ ታናሽ ሙሽራ ነሽ የአሥራ አምስት ዓመት በአንቺ ላይ ሲፈጸም እንግዳ ሥርዓት አዝ......... አንዴ እየታጠቀ አንዴም እየፈታ ገብርኤል ሲያበስርሽ በፍጹም ሰላምታ ይኩነኒ ብለሽ ስትቀበይው መለኮት እንዴት ነው የተዋሐደው ይህን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጣል አዝ........ ሁሉን የሚወስን ባንቺ ተወሰነ ከሦስቱ አካል አንዱ ቃልም ሥጋ ሆነ ስፋት እና ጥበት ሰማይ እና ምድር ባንቺ ተገናኙ ገባሪና ግብር ይህን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጣል አዝ........... እንዴት ቢመርጥሽ ነው እንዴት ቢያከብርሽ ትናንት እና ዛሬን ያገናኘብሽ ምልዐትና ወሰን ግዝፈትና ርቀት ባንቺ ተዋሐዱ ፈጣሪና ፍጥረት ይህን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጣል አዝ........ ምስጢር ሊመረምር ይወጣል ኀሊና ያልፋል ይሻገራል ከሰማይ ደመና ነገር ግን አይችልም ምንም ቢገሠግሥ በመሰወሪያው ሥር ከልጅሽም ሊደርስ ስለዚህ አቅቶት ደክሞት ይመለሳል መልክዐ ውዳሴሽን በአድናቆት ያደርሳል