У нас вы можете посмотреть бесплатно የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ለመምህር ገብረ ወልድ ሽኝት ያቀረቡት ግሩም ምስጋና или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
መጋቢት 23 ቀን 2017 ዓ.ም የመምሬ ገብረ ወልድ ደመቀ አጭር የሕይወት ታሪክ “እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ፍጻሜው ያምራል በሚሞትበትም ቀን ይከብራል” መጽ.ሲራክ 1፡13 መምሬ ገብረ ወልድ ደመቀ ከአባታቸው አቶ ደመቀ ዘሙ እና ከእናታቸው ወ/ሮ አመተ ገ/ሥላሴ በትግራይ ክፍለ ሀገር ውቅሮ አውራጃ ገማድ ወረዳ ልዩ ስሙ ማርያም ጻዕዳ ናዕለ በተባለው ቦታ በ1931 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ እድሜያቸው ለትምህርት እንደደረሰ ከመሪጌታ ተድላ ዘንድ ከፊደል እስከ ንባብ፣ ዳዊት እና የቃል ትምህርት፣ ሰዓታትና ቅዳሴ ተምረው በተወለዱበትና ክርስትና በተነሱበት ማርያም ጻዕዳ ናዕለ በዲቁና ሲያገለግሉ ቆይተው ወደ ላስታ ላሊበላ በመሄድ ትምህርታቸውን በማጠናከር ተምረው በ1954 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በዚሁ በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በደጅ ጥናት ሆነው በገዳም ሰፈር የቄስ ትምህርትን በመጀመር የሰፈሩን ሕፃናት ፊደል በማስቆጠርና ንባብ በማስተማር ብዙዎቹን ለከፍተኛ ትምህርት እንዲበቁ አድርገዋል፡፡ መምሬ ገብረ ወልድ ደመቀ የደጅ ጥናት አገልግሎታቸውን በዚሁ ቤተ ክርስቲያን አጠንክረው በመቀጠል በ1956 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ በዲቁና ተመድበው እያገለገሉ እያለ በ1957 ዓ.ም ከወ/ሮ አበባ ወ/ሐዋርያት ጋር ጋብቻቸውን በዚሁ ቤተ ክርስቲያን በተክሊልና ቅዱስ ቁርባን ፈጽመው ከዲቁና ወደ ቅስና አድገው ከ60 ዓመት በላይ ደብሩን በቅዳሴ፣ በሰዓታት፣ በጊዜያዊ ገንዘብ ያዥነት፣ በተደጋጋሚ በሰበካ ጉባኤ አባልነት እና የልማት ኮሚቴነት፣ የሙዳዬ ምፅዋቶች አጠቃላይ ቁልፍ ያዥ፣ የደብሩ አስታራቂ ኮሚቴ የሰላም አባት በመሆን ያለአንዳች እንከን ሲያገለግሉ የነበሩ አንጋፋ ካህን ነበሩ፡፡ መምሬ ገብረ ወልድ ለትምህርት በነበራቸው ልዩ ፍላጎትና ዝንባሌ በደብሩ አስተዳደር ጽ/ቤት እየተወከሉ፡- 1. በ1971 ዓ.ም በደብሩ አስተዳደር ጽ/ቤት ተወክለው ለመላው የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት ካህናት በዚሁ ደብር ተዘጋጅቶ በነበረው የ3 ወራት የካህናት የሙያ ማሻሻያ ኮርስ ተከትለው ኮርሱን በመጨረስ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ የመጽሐፍ ቅዱስ ሽልማትና የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል፡፡ 2. በ1981 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት አማካኝነት ለአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት በተሰጠው የ3 ወራት ኮርስ ደብሩን ወክለው ተሳትፈዋል፡፡ እንዲሁም ከአብራካቸው የተገኙትን ልጆቻቸውን ጨምሮ በየጊዜው ከሀገር ቤት ይመጡ የነበሩ የዘመድ አዝማድ ልጆችን ከቤታቸው በማኖርና በማስተማር ራሳቸውን እንዲችሉ የረዷቸው በርካታ ናቸው፡፡ መምሬ ገብረ ወልድ ደመቀ ባለፉት 60 ዓመታት ከመደበኛ መንፈሳዊ አገልግሎታቸው በተጨማሪ ለዚህ ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ካበረከቱት አስተዋፅኦ በጥቂቱ ለማስታወስ ከግል ማኅደራቸው የተገኙ፡- @ በሰበካ ጉባኤ አባልነት በተደጋጋሚ ጊዜያት በመመረጥ በታማኝነት አገልግለዋል፤ @ ደብሩ አሁን ለደረሰበት የልማት ውጤትና ምሳሌነት ከ25 ዓመት በፊት በአቡነ ፊሊጶስ የአስተዳደር ዘመን የገንዘብ መዋጮ ከምዕመናን በማሰባሰብ በወቅቱ በተዘጋጁ የቲኬት እና የኮፍያ ሽያጭ ሌሎችም የገንዘብ ማሰባሰቢያ መንገዶችን በመጠቀም ለደብሩ ስብከተ ወንጌል አዳራሽ፣ ሙዚየም የመጀመሪያው ሁለገብ ሕንጻ ግንባታ እና አሁን ድረስ እየተሰሩ ላሉት የልማት ውጤቶች በልማት ኮሚቴነት እስከ ቅርብ ቀን ድረስ ማገልገላቸው አይረሳም፤ @ በማንኛውም ወቅትና ጊዜ የሰላም አባት በመሆን የተጣሉትን በማስታረቅ የተራራቁትን አቀራራቢ አባት ከመሆናቸውም በላይ በረዥሙ የአገልግሎት ዘመናቸው ከማንም ያልተጣሉ ይቅር ለእግዚአብሔር ተባብለው የማያውቁ አባት ነበሩ፡፡ @ የ2000 ዓ.ም የጥምቀት በዓል አስተባባሪ ሆነው በመመረጥ በዓሉ በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር ምዕመናንን በማስተባበር ላደረጉት አስተዋጽኦ ከደብሩ አስተዳደር ጽ/ቤት የምስጋና ደብዳቤ ተቀብለዋል፡፡ @ መምሬ ገብረ ወልድ ደመቀ በሥልጣን ክህነታቸው በፍጹም ትጋት ሲያገለግሉ የኖሩ ናቸው ሲባል በዘፈቀደ ሳይሆን አገልግሎታቸውን ይፈፅሙ የነበሩት ፈጣሪያቸውን በመፍራትና በመታመን ስለነበር አገልግሎታቸው የሰመረ በሁሉም ዘንድ የሚወደድላቸው እና የደብሩ ካህናትና የአጥቢያው ምዕመናን ከሊቅ እስከ ደቂቅ የሚያውቁት መንፈሳዊ ተግባራቸው ነው፡፡ መምሬ ገብረ ወልድ ደመቀ በደብሩ ካህናትና ምዕመናን ከሚታወሱባቸው ተግባራት፡- ü በየዓመቱ በበዓለ ፶ ንስሀ ልጆቻቸውን የትንሳኤ በዓል በማስመልከት በየቤታቸው እየደገሱ ካህናትን እንዲጋብዙ በማድረግ የቆውን የአባቶች ትውፊት እንዳይረሳ ያስቀጠሉ፤ ü በየዓመቱ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን የስደት ወቅት በማስታወስ በጽጌ ወራት እንደዚሁ ንስሀ ልጆቻቸውን እያስተባበሩ ሲያስደግሱና በየዓመቱ ጥቅምት 14 የጻድቁ አቡነ አረጋዊን በዓለ ንግስ ምክንያት በማድረግ ከዋዜማው ጀምሮ እስከ በዓሉ ፍፃሜ ድረስ በማስደገስና እንግዶችን በመቀበል ሲያገለግሉና ሲያስገለግሉ ኖረዋል፡፡ ሁሉም ንስሀ ልጆቻቸው በሐዋርያዊ አገልግሎታቸው አማካይነት በሰበካ አባልነት ተመዝግበው አስራት በኩራታቸውን እንዲያወጡ ንስሀ ገብተው ወደ ቅዱስ ሥጋው እና ክቡር ደሙ እንዲቀርቡ ያደረጉ ታላቅ ካህን ነበሩ፡፡ ü ሐዋርያዊ አገልግሎታቸውን በተግባር ከገለጡባቸው ተግባራት አንዱ በየዓመቱ የመጋቢት መድኃኔዓለም በዓል አስመልክቶ ዝክር በማድረግ በአገልግሎት የዋሉትንና ቀዳስያኑን እንዲሁም ምዕመናኑን በቤታቸው በመጋበዝ አርአያነታቸውን ለመንፈስ ልጆቻቸው በተግባር ያሳዩ መንፈሳዊ አባት ነበሩ፡፡ ü መምሬ ገብረ ወልድ ደመቀ ወደ አዲስ አበባ ከመምጣታቸው በፊት መንፈሳዊ ትምህርታቸውን ሲማሩ ከቆዩበት በወሎ ክፍለ ሀገር ላስታ አውራጃ ለሚገኘው ደብረ ሎዛ እና ማርያም ሰላጢት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በእርጅና ምክንያት ፈርሶ እያለ እድሳት ሲደረግለት በነበረበት ወቅት በግል ገንዘባቸው በየጊዜው ቆርቆሮ እየገዙ በመላክ የቤተ ክርቲያኑን ሙሉ ጣሪያ በቆርቆሮ እንዲለብስ በማድረጋቸው ከቤተ ክርስቲያኑ አስተዳደር ላደረጉት ከፍተኛ እርዳታ የምስጋና ደብዳቤ ተልኮላቸው ነበር፡፡ መምሬ ገብረ ወልድ ደመቀ ከክብርት ባለቤታቸው ወ/ሮ አበባ ወ/ሐዋርያት 1 ወንድ እና 6 ሴት ልጆችን ያፈሩና ከእነዚህ ልጆቻቸው 12 የልጅ ልጆችን ያዩ፣ ፶ ዓመት የጋብቻ በዓላቸው በ2006 ዓ.ም ከባለቤታቸው፣ ከልጆቻቸው፣ ከልጅ ልጆቻቸውና ከዘመድ አዝማድ ጋር አብረው ያከበሩና ከባለቤታቸው እረፍት በኋላም በልጆቻቸው እንክብካቤ እገዛ ሲደረግላቸው ቆይተው፤ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በ2ኛ ጢሞ ምዕራፍ 4 ከቁጥር 7 በላከው መልዕክቱ “መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ ሩጫውን ጨርሻለሁ ሃይማኖትን ጠብቄያለሁ ወደፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም” በሚለው አምላካዊ ቃል መሠረት ከዚህ ዓለም ውጣ ውረድ በተወለዱ በ86 ዓመታቸው መጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ.ም በሞት ተለይተዋል፡፡ ቀብራቸውም በዛሬው ዕለት መጋቢት 23 ቀን 2017 ዓ.ም በወዳጃቸው በሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዕለት በአንቀጸ አባግዕ መካነ መቃብር ተፈፅሟል፡፡ የአባታችን የመምሬ ገብረ ወልድ ደመቀ ዜና እረፍት እንደተሰማም ቤተሰብ ብቻ ሳይሆን ቤተ ክርስቲያናችን በሀዘን ላይ ትገኛለች፤ እንደሳቸው ያለውን ደግ እና መንፈሳዊ አባት ፈጣሪ እንዲተካላት ትማፀናለች፡፡ በመጨረሻም እግዚአብሔር አምላክ የአባታችን “ነፍሰ አቡነ ገብረ ሥላሴ” ነፍስ በወዳጆቹ በእነ አብርሃም፣ ይስሐቅ እና ያዕቆብ ጎን እንዲያሳርፍልን ለልጆቻቸው፣ ለልጅ ልጆቻቸውና ለንስሀ ልጆቻቸው እንዲሁም ለሥራ ባልደረቦቻቸው የደብሩ ካህናት ሁሉ መጽናናትን ያድለን እያልን በዚሁ እንሰናበታለን፡፡ ምስጋና የደብራችን አስተዳዳሪ ክቡር መልአከ ገነት ክብሩ ገ/ጻድቅ እና የሰበካ ጉባኤው አስተዳደር አባታችን መምሬ ገብረ ወልድ ደመቀ በእድሜ መግፋትና በጤና ምክንያት በቤት ከዋሉበት ጊዜ ጀምሮ አገልግሎታቸውን በማሸፈን ሙሉ ደመወዛቸውን በየወሩ እንዲያገኙ ትዕዛዝ በመስጠት ጸሎታቸውንም በቤታቸው ሆነው እንዲጸልዩ በማድረግ ለረጅም ጊዜ አገልግሎታቸውና አባትነታቸውን የሚገባውን ድጋፍ ሲያደርጉላቸው የቆዩ በመሆኑ ከፍ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ከደብሩ ሰበካ ጉባኤ አስተዳር ጽ/ቤት #ጊዮርጊስ #ቀንዲል #ቋንቋየነሽ