У нас вы можете посмотреть бесплатно Message from Ambassador Ervin Massinga или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
ጤና ይስጥልኝ፦ ስሜ ኤርቪን ማሲንጋ ይባላል። በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የአሜሪካ አምባሳደር ሆኜ ሳገለግል ክብር ይሰማኛል። አሜሪካና ኢትዮጵያ የ120 ዓመታት የጋራ መከባበርና ትብብርላይ የተመሠረተ የረጅም ጊዜ አጋርነት አላቸው። ዛሬ እዚህ የተገኘሁት ስለ አሜሪካ ቪዛ ለማብራራት ነው። ሴክረተሪ ሩቢዮ እንደገለጹት ቪዛ መብት ሳይሆን ልዪ ጥቅም ነው። ይህ ልዩ ጥቅም የሚሰጠውም ለተወሰነ ዓላማ ብቻ ነው። ቪዛው የተሰጠበትን የጉዞ ዓላማ አለማክበር ከባድ መዘዞችን ያስከትላል። ለማንኛውም ወደ አሜሪካ ለሚጓዝ መንገደኛ በጣም አስፈላጊ ከሆኑት እና ብዙ ጊዜ በተሳሳተ ትርጉም ከሚረዱት መስፈርቶች አንዱ የአሜሪካ ቪዛ ሕግጋትን ማክበር ነው። የአሜሪካ ጉምሩክና ድንበር ጥበቃ ማንኛውም የውጭ አገር ዜጋ በአሜሪካ ውስጥ እንዲቆይ የሚፈቀ ድለትን የጊዜ ገደብ ይወስናል። ከተፈቀደው የጊዜ ገደብ በላይ መቆየት በይቅርታ አይታለፍም። ከተፈቀደልዎ የቆይታ ጊዜ በላይ በአሜሪካ ውስጥ መቆየት የሚያስከትላቸው መዘዞች የቪዛ መሠረዝን፣ ከአገር መባረርን እና ለወደፊት የቪዛ ጥያቄ ብቁ አለመሆንን ያካትታሉ። በተጨማሪም የተሰጠዎን ቪዛ በአግባቡ አለመጠቀምዎ ወደፊት ለኢትዮጵያውያን ተጓዦች ቪዛ ለማግኘት አስቸጋሪ ያደርግባቸዋል። የአሜሪካ ዜጎች የኢትዮጵያን የቪዛ ሕግጋቶች እንዲያከብሩና የቆይታ ጊዜያቸውንም እንዳያሳልፉ አጥብቄ እንዳሳሰብኩት ሁሉ በአሜሪካ ቪዛ ከቆይታ ጊዜያችሁ በላይ ባለመቆየት ኢትዮጵያዊ ወገኖቻቹን አግዙ! በአሜሪካ ውስጥ ያልተፈቀደሎትን የሕዝብ ጥቅም ተጋሪ አይሁኑ። ይህ ምን ማለት ነው? ፕሬዝዳንት ትራምፕ ወደ አሜሪካ የሚጓዙ ማናቸውንም መንገደኞች ለነዋሪነትም ሆነ ለንግድ ወይም ለቱሪዝም ለአጭር ጊዜ የሚቆዩ ሰዎች በገንዘብ ራሳቸውን የቻሉ መሆን እንዳለባቸው በግልጽ አስታውቀዋል። ይህም የአሜሪካ ዜጎች የሚያገኟቸውን የሕዝብ ጥቅማጥቅሞች ለመጠበቅ ይረዳል። ወደ አሜሪካ ለአጭር ጊዜ በቱሪስትነት ወይም የሕጋዊ ቋሚ ነዋሪ ወይም የአሜሪካ ዜጋ የቤተሰብ አባል በመሆን ለሚያደርጉት ጉዞ የሕክምና ወጪዎችን ጨምሮ ሁሉንም ሊከሰቱ የሚችሉ ወጪዎችን ለመሸፈን የሚያስችል በቂ የገንዘብ አቅም እንዳለዎት ያረጋግጡ። ይህም ለአሜሪካ ዜጎች የተዘጋጁ የሕዝብ ጥቅማጥቅሞችን ለመጠበቅ ይረዳል። የአሜሪካ የሕዝብ ጥቅማጥቅሞችን አላግባብ መጠቀም ፕሬዝዳንቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለ75 አገራት ይሰጥ የነበረው የነዋሪነት ቪዛ እንዲቆም በቅርቡ ላሳለፉት ውሳኔ አንዱ ምክንያት ነበር። ሕጋዊ ጉዞን ለማመቻት ያለን ቁርጠኝነት የፀና ቢሆንም ሕግጋትን አለማክበር ግን ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይአይደለም። ስለተረዳችሁኝ አመሰግናለሁ። መልካም ጉዞ ይሁንላችሁ!