У нас вы можете посмотреть бесплатно የንግድ ድርጅት ትመና አነጋጋሪ ነጥቦች - EP 13 или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
የንግድ ድርጅት ትመና አነጋጋሪ ነጥቦች የንብረት ግምት ጽንሰ ሃሳብ ለብዙ ሰዎች አዲስ ነገር አይደለም። በዕለት ተዕለት ኑሯችንም ስንጠቀምበት ይታያል።የንግድ ባንኮች ለግለሰቦችና ለድርጅቶች ብድር ሲያቀርቡ ለብድሩ ተመጣጣኝ ግምት ያላቸውን ንብረቶች እንደመያዣ ሲጠቀሙ እናያለን። ግለሰቦች ቤትና መኪና ከመግዛታቸው በፊት ያውቃሉ የሚሏቸውን ሰዎች ዋጋ ያስገምታሉ። ይህ የሚያሳየን የንብረት ግምት ማስላት የኑሯችን አካል መሆኑን ነው። ከዚህ ለየት የሚለው የንግድ ድርጅት ትመና (ቢዝነስ ቫሉዌሽን) ነው። ኢንቨስትመንት በሁለት መልኩ ይካሄዳል። ብዙ ሰዎች አዲስ ድርጅት መስርተው ድርጅቱ የሚያስፈልገውን የገንዘብና የሰው ሃይል ኢንቨስት በማድረግ ተቋማቸውን ያሳድጋሉ ። ሌሎች ከአመታት በፊት ተመስርቶ ምርትና አገልግሎት በመስጠት ላይ ያለ ድርጅት ላይ ተጨማሪ ኢንቨስት በማድረግ ወይም የድርጅቱን አክሲዮን በመግዛት ድርጅቶች ላይ ኢንቨስት ያደርጋሉ። የንግድ ድርጅት ትመና አስፈላጊነት እዚህ ላይ ይመጣል። እንደሚታወቀው የንግድ ድርጅት ጠቅላላ ግምት በድርጅቱ ስር ያሉ ንብረቶች ድምር አይደለም። በመሆኑም የንግድ ድርጅት ትመና ራሱን የቻለ አለም አቀፍ ተቀባይነት ያላቸው ዘዴዎች ያሉት ሲሆን ባለሙያዎችም እነዚህን ዘዴዎች ተጠቅመው ትመናውን ያሰላሉ ። በዚህ ዝግጅታችን የBDO ኢትዮጲያ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሚሊዮን ክብረት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የንግድ ስራ ትምህርት ቤት የአካውንቲንግና ፋይናንስ መምህር ከሆኑት ከአቶ ታምራት መንገሻ ጋር “የንግድ ድርጅት ትመና አነጋጋሪ ነጥቦች” በሚል ርዕስ ውይይት አድርገዋል ። በውይይቱ የሚከተሉት ነጥቦች ተካተዋል። 1. የንግድ ድርጅት ትመና ምንድን ነው? 2. የንግድ ድርጅት ትመና ከንብረት ትመና በምን ይለያል? 3. ዋና ዋና የንግድ ድርጅት ትመና መንገዶች የትኞቹ ናቸው? 4. ከነዚህ መንገዶች በሃገራችን ነባራዊ ሁኔታ የትኞቹን መጠቀም ይመከራል? 5. በትመናው ስራ አስቸጋሪ የሚባሉ ግብዓቶች የትኞቹ ናቸው? 6. ትመናው ምን ያክል ተዓማኒ ነው? 7. ትመናው ለምን ግብዓት ይውላል? The Concept of Property Valuation The concept of property valuation is not new to most people. In fact, it is something we apply in our daily lives. For example, when commercial banks provide loans to individuals or organizations, we observe that they use properties with fair valuation as collateral for the loan. Likewise, before individuals purchase a house or a car, they try to get estimation or assessment of the value of what they intend to buy. This shows that the practice of property valuation is an integral part of our everyday life. What differs from this, however, is business valuation. Investment generally takes place in two ways. Many people establish new businesses and invest financial and human resources to grow their enterprises. Others invest in existing businesses—those already operating and producing goods or services—by injecting additional capital or purchasing shares. This is where the importance of business valuation arises. As is well known, the total value of a business enterprise is not merely the sum of its assets. Accordingly, business valuation has its own internationally recognized methods, and professionals apply these methods to estimate the true value of a business enterprise. In today’s session, Mr. Million Kibret, Managing Partner of BDO Ethiopia, held a discussion with Mr. Tamrat Mengesha, Lecturer of Accounting and Finance at the School of Commerce, Addis Ababa University, under the theme “Key Points in Business Valuation.” The discussion covered the following points: 1. What is business valuation? 2. How does business valuation differ from property valuation? 3. What are the main methods of business valuation? 4. Considering our country’s current circumstances, which of these methods are most applicable? 5. What are the major challenges faced during the valuation process? 6. How reliable is a valuation result? 7. For what purposes is a valuation conducted?