У нас вы можете посмотреть бесплатно ጥቅም እና ህይወት | Benefit and Life или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
የሚከተለውን ሊንክ በመጫን የቻናላችን አባል ይሁኑ https://www.youtube.com/@truthByWill?... Facebook: / truthbywill Telegram: https://t.me/truthByWill_yt ጥቅም እና ህይወት | Benefit and Life ______________________________________ ሰዎች በእንቅስቃሴያቸው ውስጥና በዕለት ተዕለት የኑሮ መስተጋብራቸው ውስጥ የሚፈልጉት ጥቅም የሚባለውን ነገር ነው እንጂ ሕይወት አይደለም። ጥቅም ማለት አንድ ሰው ለሌላ ሰው ሊያደርገው የሚችል ነገር ነው። ሰው ለሌላ ለኑሮው ይጠቅመዋል የሚለውን እንጂ ለሕይወቱ የሚያስፈልገውን ነገር መስጠትም ማድረግም አይችልም። ሰዎች በጣም በብርቱና አጥብቀው የፈለጓቸው እስከ መጨረሻ የሚገላግል መልስ ሳይሆን ጊዜያዊ ለውጦችና መሻሻሎች ናቸው።ጥቅም ለሰው ድምድም ያለና አጥጋቢ ምላሽ አይሰጥም። በሌላ በኩል ሕይወት የሰውን ረጅሙን ማንነቱን የሚወስድና ከጥቅም ጋር የሚያያዝ አይደለም። ሕይወት ከጥቅም የሚለየው ሰው ካገኘው መቼም የማይጠፋና ጥቅሙም በጊዜ የማይለካ ዘላለማዊ መሆኑ ነው። ሰዎች ጥቅም የሚፈልጉት ከሰው ብቻ ሳይሆን ከፈጣሪ መሆኑን የሕይወት ኪሳራ ውስጥ ከቷቸዋል። ሰዎች ከፈጣሪ የሚፈልጉት ዘላለማዊ የሆነ ነገር ሳይሆን ሰሞንኛ ምላሾች ወይም ወቅታዊ የስሜት ምላሾችን ነው። ጥያቄዎቹ ሰውን ጠያቂ እንጂ የመጨረሻ ተጠቃሚ አያደርጉትም። በሰውና በፈጣሪ መካከል ያለው ንግግር ተጠቅልሎ ጥቅም ሆኗል። ሰው የሚፈልገውን ነገር ከፈጣሪ መጠየቅ የለበትም ፍላጎቱ የዓመታት የኑሮ ጥቅሞች ናቸው፤ ዘለቄታዊ አይደሉም። ፈጣሪ ሳይጠየቅ የሚሰጠው ሕይወት ደግሞ ማብቂያ የለውም። ሰው ፈጣሪን ሕይወትን ስጠኝ ብሎ ሊጠይቅ አይችልም ምክንያቱም ሕይወትን ለሰው የሚያውቅለት ፈጣሪው ነው እንጂ ሰው ሊያውቅ አይችልም። ፈጣሪ ጋር ሕይወት እንጂ ጥቅም የለም። ሌላው ደግሞ ለሰው ፈጣሪ እራሱ ሕይወት ካልሰጠው ሌላ ማንም ሊሰጠው አይችልም። ፈጣሪ ለሰው ምንድነው የፈለገው የሚለውን በመንገዱ ሄዶ ነገሩን በራሱ መጨበጥ ይችላል። አድራሻ፡ ከሐያት ሆስፒታል ወደ ቦሌ ብራስ መንገድ ላይ፣ ትጌላ ህንጻ 4ኛ ፎቅ --› ሁሌ እሑድ ጥዋት ከ4፡00 ሰዓት ጀምሮ የአንድ ሰዓት የትምህርት ክፍለ ጊዜ ስላለን ሁላችሁም ተጋብዛችኋል። --› ለበለጠ መረጃ በ0911753088 ወይም በ0703938111 መደወል ትችላላችሁ።