У нас вы можете посмотреть бесплатно የዜማ ጊዜ | Apostolic Church | እልል በዪ | Apostolic song | Hossana Choir | የሆሳዕና መዘምራን или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
ከጥር 26-28/2015 በሆሳና በተካሄደው 51ኛው የሀድያ ሰበካ ጉባዔ ላይ የቀረበ የዝማሬ አምልኮ። በእዚህ ጉባዔ 73 ሰዎች ወደ መዳን መጥተዋል ፣ 56 ሰዎች ከበሽታ ለመፈወሳቸው መስክረዋል ፣ ከ250 በላይ ሰዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በቅዱስ መንፈስ ተሞልተዋል። ግጥም/Lyrics ነጋ ለሊቱ ነጋ |4x| ክረምት አለፈ የለቅሶ የዋይታ የመከራ ዘመን በኢየሱስ ታለፈ ማቅሽ ተቀደደ እንባሽም ታበሰ የዜማ ጊዜ ይኸው ደረሰ እልል እልል በዪ |3x| ማቅሽን ቀዳድደሽ ተነሺ ዘምሪ እልል እልል በዪ |3x| ትቢያሽን አራግፈሽ ተነሺ ዘምሪ 1. በዓለት ንቃቃት ተሸሽገሽ ያለሽው ውጪ ተገለጪ ዘመን መጣልሽ የናቁሽ በሙሉ ወደ አንቺ ይመጣል ከእግርሽ ስር ወድቀው ገና ይሰግዳሉ ወይንሽም አብቧል ስዕለትሽም ሠምሯል የመከራን ጊዜ በኢየሱስ አልፈሻል ተነሺ ዘምሪ ዘመን መጥቶልሻል የአማልክት አምላክ ድል አጎናጽፎሻል እልል እልል... 2. ኃያላን ነገሥታት ዝናሽን ሰምተው ከሩቅ ይመጣሉ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ያዕቆብ አምላክ እንሂድ ይላሉ ስፍራ ጠብቦናል የምናርፍበት ኑ እንነሳ ለእግዚአብሔር ቤት ሥራ በአንድነት ድንኳንሽን አስፊ ካስማዎችሽን ዘርጊ ዓይኖችሽን አንስተሽ በዙሪያሽ ተመልከቺ ከምስራቅ ከምዕራብ ከሰሜን ከደቡብ ከአራቱም አቅጣጫ ከዳር እስከዳር ኢየሱስ በፉጨት ልጆቹን ይጠራል ጽዮን ደስ ይበልሽ ዘመን መጥቶልሻል ያለፈውን አታስቢ እንደ ክረምት አልፎ ሄዷል አዲስ ነገር አዲስ ታሪክ ኢየሱስ በአንቺ ይሰራል |2x|