У нас вы можете посмотреть бесплатно በርባን ይቅር በለኝ እንዳትቀየመኝ или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
የአይሁድ ህዝብ ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲሰቅልላቸውና በርሱ ምትክ በርባን የተባለ ነፍሰ ገዳይ እንዲፈታላቸው ለመኑት። በርባን ሁላችንንም የወከለ ወንበዴ ሲሆን እኛ ኃጢአተኞቹ የሰው ልጀች በክርስቶስ ሆነን የእግዚአብሔር ልጆች እንድንሆን ክርስቶስ የኛን እርግማን ተሸኽሞ በመስቀል ላይ የመሞቱን ሚስጢር ያመለክታል። ታሪኩን ከዚህ ቀጥሎ ያንብቡ። የማርቆስ ወንጌል 15 1 ወዲያውም ማለዳ የካህናት አለቆች ከሽማግሌዎችና ከጻፎች ከሸንጎውም ሁሉ ጋር ከተማከሩ በኋላ፥ ኢየሱስን አሳስረው ወሰዱትና ለጲላጦስ አሳልፈው ሰጡት። 2 ጲላጦስም፦ አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን? ብሎ ጠየቀው። እርሱም፦ አንተ አልህ ብሎ መለሰለት። 3 የካህናት አለቆችም ብዙ ያሳጡት ነበር፤ እርሱ ግን ምንም አልመለሰም። 4 ጲላጦስም ደግሞ፦ አንዳች አትመልስምን? እነሆ፥ በስንት ነገር ያሳጡሃል ብሎ ጠየቀው። 5 ኢየሱስም ከዚያ በኋላ ጲላጦስ እስኪደነቅ ድረስ ምንም አልመለሰም። 6 በዚያም በዓል የለመኑትን አንድ እስረኛ ይፈታላቸው ነበር። 7 በዓመፅም ነፍስ ከገደሉት ከዓመፀኞች ጋር የታሰረ በርባን የተባለ ነበረ። 8 ሕዝቡም ወጥተው እንደ ልማዱ ያደርግላቸው ዘንድ እየጮኹ ይለምኑት ጀመር። 9 ጲላጦስም፦ የአይሁድን ንጉሥ እፈታላችሁ ዘንድ ትወዳላችሁን? ብሎ መለሰላቸው፤ 10 የካህናት አለቆች በቅንዓት አሳልፈው እንደ ሰጡት ያውቅ ነበርና። 11 የካህናት አለቆች ግን በርባንን በእርሱ ፈንታ ይፈታላቸው ዘንድ ሕዝቡን አወኩአቸው።