У нас вы можете посмотреть бесплатно ዘምሪ፣ እልል በይ፣ ጩሂም! ምን ተገኘ? или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
ነቢዩ ኢሳያስ ከክርስቶስ ልደት 700 ዓመታት አስቀድሞ ስለ ክርስቶስ መከራ፣ ከዚያም በኋላ ስለሚመጠው ክብር ይናገራል። ኢሳ. 54 ላይ ከቁጥር አንድ እስከ ሦስት፦ "“አንቺ ያልወለድሽ መካን ሆይ፥ ዘምሪ፤ አንቺ ያላማጥሽ ሆይ፥ እልል በዪ፥ ጩኺም፤ ባል ካላት ይልቅ ፈት የሆነቺቱ ልጆች በዝተዋልና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ የድንኳንሽን ስፍራ አስፊ፥ መጋረጃዎችሽንም ይዘርጉ፤ አትቈጥቢ፤ አውታሮችሽን አስረዝሚ ካስሞችሽንም አጽኚ። በቀኝና በግራ ትሰፋፊያለሽና፥ ዘርሽም አሕዛብን ይወርሳልና፥ የፈረሱትንም ከተሞች መኖሪያ ያደርጋልና።” በማለት የምሥራች ይናገራል። ትልቁ ጥያቄ ምን ተገኘ? የሚለው ነው። የተገኘው ለዘለዓለም ያላማጠችውና ልጆችን ያልወለደችው ሰማያዊት አገር በኢሳ. 53 ላይ በሥጋ ከመጣው፣ በመስቀል ላይ ከተሰዋው፣ ከተቀበረውና ከሙታን ከተነሳው ከክርስቶስ ሥራ የተነሳ አዕላፋትን መውለዷ ነው። ከእርሱ ሥራ የተነሳ እኛ የቁጣ ልጆች የነበርን የሰው ልጆች የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን ዕድል አገኘን። ይህ መልዕክት በኢሳ. 54፥1-3 ባለው ክፍል በወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን ሲልቨር ስፕሪንግ ሜሪላንድ በምትገኘው ፎር ኮርነርስ የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን ቤተክርስቲያን የቀረበ ነው።