У нас вы можете посмотреть бесплатно ፊደል ካስትሮ የ20ኛው ክፍለ ዘመን ድንቅ መሪ ll Fidel Castro, the great leader of the 20th century или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
#ፊደል_ካስትሮ #Fidel_Castro #ታሪክን_የኋሊት በአለም ከተካሄዱ አብዮቶች ትልቅ ለወጥን እንደፈጠረ ተደርጎ የሚቆጠር አቢዮት ነው የኩባ አቢዮት ። አቢዮቱም ክስተት በቻ ሆኖ አልቀረም ። ፊደል ካስትሮ የተባሉ የ20ኛው ክፍለ ዘመን ድንቅ መሪን ለአለም አስተዋውቋል ።ፊደል ካስትሮ እና ጓደኞቹ የወቅቱ መንግስት አምጻችኋል በማለት ለሁለት አመት ካስሯቸው በኋላ በምህረት ለቀቃቸው። ከዛን በኋላ ፊደል ካስትሮ ህዝብ አደራጅቶ ወደ አሜሪካ በመጓዝ ዳግም በተትጥቀ እና በሃይል አደራጅቶ ለትግል ወደ ሳንቲያጎ ተመለሰ። የተጠናክረው ተቃወሞ እና ከግዜ በኋላ እያንሰራራ የመጣው የ ፊደል ካስትሮ ሃይል ወደ ሃቫና ገስግሶ ወደ በመጨረሻም የባቲስትን መንግስት በሃይል መጣል ቻለ ። ከባቲስታ መንግስት በኋላ ፊደል ካስትሮ ወደ ስልጣን ተተትኩ። ካስትሮ ለጥቂይ አመታት ኩባን በጠቅላይ ሚንስተርነት ካገለሉ በኋላ በዛሬው ቀን ከ46 አመት በፊት ዶርቲኮስ ቶራዶን በመተካት የኩባ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ ። ካስትሮ ፕሬዝደንት ሆነው ከተሾሙ በኋላ ኩባ በትምህርት ፣ በጤና ፣ በመሰረተ ትምህርት ግንባታና በወንጀል መከላከል በኩል ኩባ ውጤታማ እንደትሆን አስቸለዋታል ። በተለይ ለትምህርት የሰጠው ትኩረት ሁሌም ያስወደሰዋል ። የአገሪቱ ልጆች ከመዋዕለ ሕጻናት እስከ ዩኒቨርስቲ ለሚማሩት ትምህርት ሁሉንም ወጪ የሚሸፍነው የኩባ መንግስት ነው ። ፊደል በዚህ ምክንያት በኩባ ህዝብ ለዘለዓለም ሲታወሱ ይኖራሉ ። ካስትሮ ለኩባውያን ብቻ የሚያስቡ አልነበሩም ፤ ዘረኝነትን ፣ ቀኝ አገዛዝን በመቃወም ከራሳቸው አልፈው ውቅያኖስና ድንበር ሳይከልላቸው ከጭቁኖች ጋር በመሆን ተዋግተዋል ። ኒካራጋዋ ፣ ኤልሳቫዶር ፣ አልጄሪያ እና ቬትናም የካስትሮ እርዳታ እጅ ተዘርግቶላቸዋል ። በተለይ አፍሪካ የፊደል ካስትሮን እገዛ ባታገኝ ኑሮ ምናልባት አፍሪካ የዛሬዋን አይነት አትሆንም ነበር የሚሉ ምሁራን ጥቂት አይደሉም ። ከባራክ ኦባማ በፊት በነበሩት 10 ፕሬዝዳንቶች ዘመን ኩባን ለማንበርከክ የተከናወኑ ሴርዎች ሁሉ አልተሳኩም ። አንዳንድ ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት የአሜሪካ መንግስት ከቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ አድርጎ ካስትሮን ለመመረዝ ፣ ቦንብ የተቀበረበት ደብዳቤ በመላክ ፣ በሚናገሩበት ማይክራፎን ቦምብ በማጥመድ ፤ በሲጋራው ውስጥ ገዳይ መርዝ በመቀላቀል እንዲሁም ቆንጆ ሴቶችን በመላክ የግድያ ሙከራዎችን ቢያደርጉም አንዱም ሳይሳካላቸው ሁሉም ሊከሽፍ ችሏል ። ካስትሮም እንዲህ ይላላ"ከግድያ ሙከራ መትረፍ የኦሎምፒክ ውድድር ቢሆን ኖሮ የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ እሆን ነበር። ፊደል ካስትሮ ከኢትዮጲያውያንም ጋር በነበረቸው ወዳጅነት ሁሌም ሲታወሱ ይኖራሉ ። በ1970 የሶማሊያው ዚያድባሬ በአሜሪካን እና በግብጽ ድጋፍ በኢትዮጲያውያን ላይ ጦርነት ባወጀበት ወቅት ከኢትዮጲያውያን ጎን በመሆን 17 ሺህ ወታደሮችን ፣ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን እና የህክምና ባለሙያዎችን የላኩልን የኢትዮጲያውያን ባለውለታ ናቸው። “የሶሻሊዝም ጎዳና ባይመችም ፣ ችግር ቢበዛበትም ፊደል ካስትሮ መንገዳችን ብሎ እስከመረጠ ድረስ እንሄዳለን” ይላሉ ዛሬም ድረስ ኩባውያን ። == == == ✔ታሪክን የኋሊት ቲዩብ ቻናል ፡- ታሪክ፤ ዕምነን፤ አስተሳሰብ ፤ባህል፤ ፍልስፍና እና መሰል ነገሮች ላይ ትኩረት ሲያድርግ፤ በሀገራችን እና በአለማችን የተከናወኑትን አንድም ለትውስታ አንድም ለመማሪያ መለስ ብለን የምንቃኝበት ቻናል ነው፡፡ ✔LIKE በማድረግ ተደራሽነቱን ያስፉ፡፡ ✔SHARE በማድረግ ሌሎች እንዲደርሳቸው ያጋሩ፡፡ ✔SUBSCRIBE በማድርገ ቤተሰብ ይሁኑ፡፡ ✔ይህንን እና ሌሎች አስደናቂ ታሪኮችን ለመከታተል ቻናላችንን ያልተቀላቀላ SUBSCRIBE አድርጉ፡፡