У нас вы можете посмотреть бесплатно የዓርሹ ባለቤት "الله አላህ" - አዲስ የህብረት ነሺዳ ( или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
#mezamir #liqae #abduselam #nasheed #liqa #neshida #መዛሚር #ethiopia ግጥም - ሀሰን አራጋው ዜማ - ዓብዱሰላም ቅንብር - ኤሉና ስቱድዮ ቪዲዮ - ብራይት ፕሮዳክሽን በሸሃዳ ገመድ ቀልብ ከታሰረ፣ በስምህ ጀምሮ የለም የከሰረ። ቢስሚላሂ ቃሉን ከሁሉ አስቀድሜ፣ ስሙን እጠራለሁ በተሰጠኝ ዕድሜ። ዱኒያን ወደ አኸራ በስልቱ አሻጋሪ፣ አምሳያ የለውም ስልጣኑን ተጋሪ። የአዛኝነት ጋሻህ እንዲያስጥለኝ ከ‘ሳት፣ ጠብቀኝ ሶመዱ ቃልህን ከመርሳት። የጨነቀው ሁሉ ወዳንተ ይጠጋል፣ አላህ አላህ ስንል ይመሻል ይነጋል። ከማንም ከምንም የነበረው ቀድሞ፣ ብቻውንም ሊቀር ፍጥረቱን አክስሞ። ጨለማን ከብርሃን በትንግርት የሰፋ፣ ቢያሻው የሚያበራ ቢያሻው የሚያጠፋ። الله الله الله الله الله الله لاله الا الله محمد رسول الله ሩህን የሸጎጠ በመኹሉቁ ጉያ፣ የአርሹ ባለቤት የሌለው እኩያ። ፍርዱ የሰፈረው በማይነጥፍ ቀለም፣ ነፍሴን በእጁ ይዟል አላህ ረበልዓለም። ቅንጣት የማይተኛ የማያንጎላጀው፣ እሱ እየጠበቀ እረፍቴን ያበጀው። የቀደረው ሁሉ በወንዙ ይፈሳል፣ ተበደልኩኝ ብሎ ማን እሱን ይከሳል? ተቆጥሮ የማያልቅ ፍጥረት በላይ በላይ፣ ለአቅል የራቀ በምድር በሰማይ። ባለቤት ነውና የሰማይ የምድር፣ በፈቃዱ ውየ በፈቃዱ የማድር። እኔ እሱን ፈላጊ በቀንም በማታ፣ እሱ ቻይ ራሱን ሉዓላዊው ጌታ። الله الله الله الله الله الله لاله الا الله محمد رسول الله ከእቀፉኝ ደግፉኝ ለጠራው ዓዚዙ፣ ምህረት ፈላጊዎች ለክብሩ ታዘዙ። ፀሃይ ስንዝር ቀርባ ጭንቀት ሲበረታ፣ ነፍሴን ነፍሴን ብሎ መኽሉቁ ሲረታ። ሸፍዓ ቢፈለግ አማላጅ ወዳጅህ፣ ባንተ ፈቃድ እንጂ አይቆምም ከደጅህ። ጨዋ ሆኜ ስታይ ወንጀሌን ስትሰትር፣ አያያዝህ ሲጠብቅ ባለብዙ በትር። እንኳን የሚያክልህ የሌለህ አምሳያ፣ ከውን አፈጣጠርህ ተዓምርን ማሳያ። የንጉሶች ንጉስ የአለቆች አለቃ፣ የሰፈርከው ሲሳይ ለዓለማት በቃ። የእዝነትህ ፀዓዳ አባሽ የወንጀሌ፣ ኢላሂ እያልኩህ በደረሰ አጀሌ።