У нас вы можете посмотреть бесплатно ድምጻዊ መስፍን አበበ | ለመጀመሪያ ጊዜ በ1974 ዓም ያደረገው ቃለምልልስ | Mesfin Abebe 1st Interview или скачать в максимальном доступном качестве, которое было загружено на ютуб. Для скачивания выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
አርቲስት መስፍን አበበ ! ወይ ሐረር ወይ ሸገር አጫውቺኝ ነይና›› እያለ ከምድር ባቡር ጋር አስተሳስሮ በሚጫወተው ዜማው እንዲሁም ‹‹አይሽ አይሽና ይመጣል እንባዬ››፣ ‹‹እንዲያው ጉም ጉም››፣ ‹‹መልካም ልደት›› ተጠቃሾች ናቸው፡፡ በደሴ ወይዘሮ ስሂን ትምህርት ቤት የሙዚቃ ባንድ ጋር በመሆንና ሙዚቃ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በመጫወት ወደ ጥበቡ የዘለቀው ድምፃዊና ጊታሪስት መስፍን፣ በተለያዩ ሙዚቃ ቤቶች 22 ካሴቶች ማሳተሙ ይነገርለታል፡፡ መስፍን ሕይወቱን ‹‹የመንፈስ አረቄ የነፍስ እህል ውኃ›› እየተባለች ከሚነገርላት ሙዚቃ ጋር ብቻ አላቆራኘም፡፡ የአድማጮችን ኅሊና የሚኮረኩሩ ብሂልን ከባህል ያዛመዱ፣ ነውን ከነበር የሚያጣቅሱ ሥራዎቹን በሙዚቃው ብቻ ማስተላለፍ አልተወሰነም፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ ትውልድን ለማነፅ እንደ አባቶቹ አርዓያነት ያለውን የአስተማሪነት ሙያን በመፍቀድና ከመምህራን ትምህርት ኮሌጅ በመዝለቅ ሙያውን ጨብጧል፡፡ ሲያስተምር፣ ሲያዜም፣ ጊታር ሲጫወት ኖሯል፡፡ አስተማሪነቱ የቀለም ትምህርት ብቻ አልነበረም፡፡ በዘመኑ ወጣት ከነበሩ አሁን አንጋፋ ድምፃውያን ዕውቀቱን አልነፈጋቸውም፡፡ አንዱ ማሳያ የታዋቂው ድምፃዊ ንዋይ ደበበ ምስክርነት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ማኅበር ድረ ገጽ ላይ እንደተመለከተው፣ ‹‹ድምፃዊ ንዋይ ደበበ ዜማዎችን ሲፈጥር በፉጨትና በእንጉርጉሮ ሲሆን፣ ከአንድ ወቅት በኋላ በቦክስ ጊታር እየተጫወተ የሚያቀነቅነውን ዝነኛ ድምፃዊ መስፍን አበበ ለሥራ ወላይታ በመጣ ጊዜ የማግኘት ዕድሉ አጋጥሞት፣ ለዜማ መለማመጃ የቦክስ ጊታር አጨዋወት እንዳስተማረው ይታወቃል፡፡›› ከአባቱ አቶ አበበ ወልደ ማርያምና ከእናቱ ከወ/ሮ ወይንሸት ተሾመ በ1944 ዓ.ም. የተወለደው መስፍን አበበ፣ በአሥራዎቹ ዓመታት በተማረው ሙያ በድምፃዊነትና በሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋችነቱ እንዲሁም በመምህርነቱ ይታወሳል፡፡ ባደረበት ድንገተኛ ሕመም ግንቦት 25 ቀን 2008 ዓ.ም. በ64 ዓመቱ ያረፈው ድምፃዊና መምህር መስፍን አበበ ፣ ሥርዓተ ቀብሩ በማግስቱ በብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን እኩለ ቀን ላይ ተፈጽሟል፡፡ ድምፃዊ፣ ሙዚቀኛና መምህር መስፍን ባለትዳርና የአንዲት ሴት ልጅ አባት ነበር፡፡ መስፍን አበበ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1974 ዓም ከሚያስተምርበት ቦታ ለሙዚቃ ስራ ወደ አዲስአበባ በሔደበት አጋጣሚ ከኢትዮጵያ ሬድዮ ያደረገውን መሳጭ ቃለምልልስ እንድታዳምጡ ጋብዘናል! #ethiopianmusic #habeshamusic #ethiopia #EthiopianOldies #VintageEthiopian #EthiopianClassics #EthiopianGoldenEra #EthiopianRetro #EthiopianHeritage #EthiopianTradition #EthiopianSounds #EthiopianMelodies #Ethiopiannstrument #tigrignamusic #EthiopianLegends #EthiopianHistory #EthiopianCulture #EthiopianSoul #habesha #africa #ethiopian #oromo #addisababa #ethiopianwomen #eritrea #habeshabeauty #ethio #ethiopianfood #habeshawedding #habeshastyle #habeshafashion #eritrean #ethiopians #amharic #ethiopiancoffee #addisabeba #habeshagirl #love #reviewethio ቻናላችንን ሳብስክራይብ ፣ ሼር ፣ ላይክ ፣ ኮመንት በማድረግ እንድታበረታቱን በአክብሮት እንጠይቃለን፣ እናመሰግናለን ! @timelessmuzikaplus