У нас вы можете посмотреть бесплатно ለ6 ከደፈሩኝ በኃላ ጫካ ውስጥ ጥለውኝ ሄዱ?EBS ቪዲዮዉን ለምን አወረደው?በስቃይ የተሞላ ሕይወት( или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
ምንም ዘመድ የለኝም! #Ethiopia | እዚህች ሀገር ላይ ብዙ የጭካኔ ታሪኮችን ሰምተናል። የዚህች ልጅ ስቃይ ግን ከቃላትም ሆነ ከአእምሮ በላይ ነው። ብርቱካን ተመስገን ትባላለች። ከልጅነቷ ጀምሮ ዕድል ፊቷን ያዞረችባት ሰው ናት። በልጅነቷ ወላጆቿን አጣች። ለአሳዳጊ ተስጥታ መክራ ማየት ጀመረች።ትምህርቷን በደንብ ተከታትላ 392 ነጥብ አመጣች። ተሰቃይታ ተምራ ዩኒቨርስቲ ገባች። በዩኒቨርስቲም በፋርማሲ ትምህርቷን በትጋት መከታተል ጀመረች።የ2ኛ ዓመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪ እያለች ያልታሰበ ነገር ተፈጠረ። ታጣቂዎች ከምትማርበት ዩኒቨርሲቲ ከሌሎች ተማሪዎች ጋር አንድ ላይ ጠልፈው ወደ ጫካ ወሰዷቸው። 1 ዓመት ከ 6 ወር በላይ ጫካ ውስጥ ከታጣቂዎች ጋር ኖረች። በመጨረሻ 6 በሚሆኑ አረመኔ ታጣቂዎች ተደፈረች። ጫካ ውስጥ ጥለዋት ሄዱ። እርጉዝ መሆኗን አወቀች። አሁን ብርቱካን ውድ ኢትዮጵያውያን ትምህርቴን መከታተል እፍልጋለሁ። ታማሚ ልጅ አለኝ። እኔም የልብ ታማሚ ነኝ። እባካችሁ እርዱኝ። ምንም ዘመድ የለኝም - እያለች ትገኛለች። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000679657112 ብርቱካን ተመስገን እባካችሁ እናንተ ደጋግ ኢትዮጵያውያን ሼር አድርጉት #Ethiopia ከዓመታት በፊት እንደ ሁሉ ዓማን እንደ ሀገር ሰላም ቀዬ መንደራቸውን ለቀው ፣ ሀገር ሕዝባቸውን አምነው ሊማሩ ሊመራመሩ ከቤት የወጡ ጥቂት የማይባሉ ተማሪዎች በወጡበት ቀርተዋል፡፡ እድል ቀንቷቸው መያዛቸው ከተሰማላቸው ተማሪዎች በመለስም ብዙዎቹ የት እና በምን ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ ሳይታወቅ ድምፃቸው ጠፍቷል ….፡፡ በብዙ ልፋት እና መከራ አሳድጎ …ሀገር ሰላም ብሎ ….ልጆቻቸውን ለአስኳላ የላኩ ወላጆች ከመቼው ተመርቀው ከመቼው ስራ ይዘው ብለው የምርቃታቸውን ቀን በጉጉት ሲጠብቁ ..ገሚሳቸው ዩኒቨርስቲ ውስጥ በተቀሰቀሰ ዘርን እና ጎጥን መሰረት ባደረገ ረብሻ ልጆቻቸውን አጥተው መርዶ ሲሰሙ ገሚሳቸው ደግሞ ልጆቻቸው የውሃ ሸታ ሆነው የቀሩባቸውም ብዙ ናቸው፡፡ ትላንት በኢቢኤስ ጣቢያ አዲስ ምዕራፍ በተሰኘ መሰናዶቸው ላይ ከዩኒቨርስቲ ታግታ....አንድ አመት ከስድስት ወር ጫካ በመቆየት፣ እርቃኗን እንድትቆም በመደረግ፣ እንደ እንሰሳ በቡድን በመደፈር እና ...ሌሎች ያልተሰሙ እጅግ በጣም ዘግናኝ ታሪኮች በማስተናገዷ ምክንያት የደረሰባትን የሕይወት ውጣ ውረድ በእንባ በታጀበ ለሆሳስ ድምጽ ስትናገር የተሰማቸው እንስት የደረሰባት በደል እና ስቃ የብዙዎቻችን ልብ ሰብሮታል፡፡ ባለታሪኳም ሆነች አብረዋት የነበሩ ልጆች እንዲያ ባሉ የስቃይ ቀናት እና ወራት ውስጥ ያልነገሩን …ያልሰማናቸው እንዴት ያሉ መራር ገፈቶችን ሲቀምሱ እንደነበር መገመት እጅጉን ቀላል ነገር ነው፡፡ የተሰማው ታሪክ የሰማነው ታሪክ ብቻ ነው።ብዙ ያልሰማናቸው ታሪኮች እንዳሉ እሙን ነው፡፡ ያልተነገረውስ….መከራ እንዴት አይነት ነበር….ሌሎቹስ የእርሷ ብጤ ግፉዓንስ ወዴት ይሆን ያሉት…. ይች ምስሉ ላይ የምትመለከታት ኢቤኤስ ቴሌቪዥን አዲስ ምዕራፍ በተሰኘ መሰናዶው ላይ ይዟት ብቅ ያለው ግለሰብ ብርቱካን ተመስገን ትባላለች ገና በልጅነቷ ነበር ላሳዳጊ ተስጥታ መክራ ማየት የጀመረችው ፡፡ተወልዳ ያደገችው ም/ጎጃም ስናን ወረዳ መሆኑን ስትናገር ተሰምታለች፡፡ ብርቱካን አባቷ መሰደዱን እና እናት በወሊድ ምክንያት ገና በለጋነት ዕድሜዋ ህይወቷ ማለፉን ትናገራለች።ብርቱካን ምንም እንኳን እንደ ሁሉ ልጅ እየተከታተለ ተማርሽ አልተማርሽ ..ምን ጎደለ …ነይ ላያስጠናሽ …ፈተና መቼ ነው …ውጤት ስነት አመጣሽ እያለ የሚከታተላት የሚደግፋት ሰው ባይኖርም እርሷ ግን ብርቱ ታታሪ ተማሪ ሆና ኑሮ ትምህርቷን በደንብ ተከታትላ 392 ነጥብ በማምጣት ለከፍተኛ ትምህርት ወደ ዩኒቨርስቲ አቀናች:: ብርቱካን እስከ 8 አመት አያቷ ጋር ካደገች በኋላ የሰው ቤት ገብታ እየሰራች ነበር ትምህርቷን የተማረችው፡፡እስከ 8ኛ ክፍል የደረጃ ተማሪ በመሆን የተሸለመችው ብርቱካን ቤት ውስጥ ከምትሰራው ከባድ ስራ ጎንለጎን ትምህርቷን እንዲያ ባለ መልኩ ቀጥላ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳ ያን የመሰለ ግሩም ውጤት ካመጣች በኃላ ዩኒቨርሲቲ ስትገባ በፋርማሲ ዲፓርትመንት ውስጥ ነበር ሌላኛውን አዲስ የሕይወት ምዕራፍ የጀመረችው፡፡ መንገዷ አባጣ ጎርባጣ…እሾህ አሜኬላ በዛው እንጂ በዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ አመት ተማሪ ሆና ሳለ ከዕለታት በአንዱ ቀን ምሽት እንደ ወትሮዋ ሁሉ ከላይብረሪ ስትመለስ በግቢ ውስጥ ረብሻ ስለመከሰቱ የምትናገረው ብርቱካን በወቅቱ የሆነውን ስትናገር ከውስጥም ከውጪም ተኩስ ነበር ቶሎ አምልጡ በማለት እዚህ መኪና ግቡ ብለው መኪናው ላይ ከገባን በኃላ ይዘውን ወደ ጫካ ገቡ ብላለች። ጨካ ከደረስንም በኃላ የፈልግናችሁ ለስልጠና ነው አብራችሁን ትሆናላችሁ ብለውን ጫካ አስቀመጡን በጣም የመከራ ጊዜ ነበር የሚበላ የሚጠጣ ማግኘት አስቸጋሪ ነበር ትላለች ብርቱካን የሆነውን ሰታስታውስ፡፡ ተፈጠሮ መቼም የመንጋት የመጨለም ውሏን አትረሳም እና እየነጋ እየመሸ ጊዜው ሄደ ቀናት አልፈው ሰምንታት ሳምንታትም ወራትን ተክተው ወደ ዓመት ዘለቁ ፡፡ በብዙ ባልተነገሩ እና ባልተሰሙ በደሎች ውሰጥ ሆነው አመት ከስድስት ወር ተቆጠረ፡፡ ከዛ በቀናት በአንዱ ትላለች ብርቷን ስትናገር በቀናት በአንዱ «አሁን ስራችንን እንጀምር» በማለት ሁላችንንም ልብስ አስወልቀው አሰለፉን ከዛም እየተፈራረቁ ይደፍሩን ጀመር እኔ ስድስተኛ ተራ ቁጥር ላይ ነበርኩ ከዛ በኋላ የሆነውን አላውቅም እኔ ሰውነቴ ደንዝዟል በፌሮ ብዙ ቦታ ለይ ይወጉኝ ስለ ነበር መዛል መደንዘዝ ጀመሪያለሁ፡፡ ስትል ስቃይ መከራዋን ትናገራለች፡፡ እንዲህ ያለው ለምድር ለሰማይ የከበደ ግፍ ከተፈፀመባት በኃላ ሩኃን ሳተች …የት እንዳለች ሳታውቅ ቀናት ተቆጠሩ፡፡በስድስተኛ ቀኔ ስነቃ ደም እየፈሰሰ ነበር፣ ነገ ህይወቴ ይለወጣል፣ ነገ ጥሩ ቦታ እደርሳለሁ ብዬ ያልኩት ልጅ የሕይወት መስመሬ መጨረሻ እንደዚህ ሲሆን በጣም ከፋኝ፣ ህይወቴን በምን መልኩ ነው የምቀጥለው፣ አይዞሽ የሚለኝ ከሰው ሰው ከዘመድ ዘመድ የለኝም። መጨረሻ ላይ የጎዳና ተዳዳሪ ነው የሆንኩት ስትል የሕይወት ውጣ ውረዷን ታስረዳለች፡፡ ያን ሁሉ በደል እና ስቃይ ያደረሱባቸው ሰዎች ጫካ ውስጥ ጥለዋት ይሄዳሉ፡፡ብርቱካን ቀኗ ሲገፋ እርጉዝ መሆኗን አወቀች፡፡ እንዲህ ያለው ነገር ለብርቱካን በቦዓ ላይ ቆረቆር ነበር የሆነባት፡፡ እንዳለችው ተምሬ ነገ ሰው እሆናለሁ …ለሰው ሕመም መፍትሄ እፈጥራለሁ …ይቺን ሀገር እና ሕዝቧን በሙያዬ አገለግላለሁ ብላ ያለች ልጅ እንዲህ ባሉ የመከራ ትብታቦች ተተብትባ መቀርቷን የሰማን ሀሉ ልባችን በብዙ በብዙ አዝኗል፡፡አሁን ብርቱካን የልጅ እናት ነች፡፡ ባልጠና አከሏ ላይ የደረሰው በደል እና ግፍ ሳይደርቅ ደግሞ እናት ሆናለች …እናትነቷ ላይ ደግሞ እርሷም ልጇም ታማሚ ናቸው! ብርቱካን ዛሬም ተስፋዋ ከዓለት የገዘፈ ነው …ያ በብዙ አበክራ ትልትቀጥለበት የምትሸው ትምህርቷ ዛሬም የቀን ቅዠት የሌት ሕልሟ ነው …ኢትዮጵያውያን አግዙኝ ትምህርቴን መከታተል እፍልጋለሁ ታማሚ ልጅ አለኝ እኔም የልብ ታማሚ ነኝ ትላለች፡፡ መለወጥ መደገፍ ህይወቷ ድጋሚ እንዲለመልም ተስፋ እንዲኖራት ትፈልጋለች። እዚህ ጋር እንደ ሰው ቆም ብለን አንድ ውሎ አድሮ የሚከታለትን ፈተና አዘል ጥያቄ ለማሰብ ወደድን …ሕይወት መቼም እንዲህ እንዳለችበት አትቀጥልም እና ውሎ አድሮ ቀን ሄዶ ቀን ሲመጣ ነገሮች ተለውጠው ልጇም አድጎ ራሱን ያቀ ቀን አባቴ ማን ነው ብሎ ቢጠይቃት እንዴት ያለ መልስ ልትመልስ ይሆን …. ልጇ የሕመሟ ውጤት ነው ….የሰቃዩኣ ትውስት …የመከራዋ ሸታ……ምጡን እርሽው ልጁን አንሺ ው እንዲሉ ምጧንም መከራዋንም እረስታ ….የአብራኳ ክፋይ የሆነ ለጅ ስለመሆኑ ብቻ እያሰበች ካልኖረች እንደ እናት ልጇን ስለወለደችበት መከራ ካሰበች ሕመሟ ምስ አልባ ነው፡፡ ሌላኛው እና ዋነኛው ጥያቄ እንዲህ ያለውን ልብ ዝቅ የሚያድግ መሰናዶ ይዞ የቀረበው ኢቢኤስ ይህን መሰናዶ እንደ ወትሮው የየዕለት ፕሮግራሞቹን ሁሉ ዩቱዮብ ላይ ከጫነው በኃላ ለምን እና እዴት እንደሆነ ባልታወቀ መልኩ ከዩቱዮቡ ላይ መልሶ አውርዶታል፡፡ የአበባ ጉይ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ ሲመላለስ መሰናዶውን ያላዩ ሰዎች መልሰው ሊመለከቱት ሲሹ በማጣታቸው ኢቤኤስ ይህን ለምን አደረገ …ምን ጉዳይ ቢገጥመው ነው …ስለምንስ በዚህ ጉዳይ ላይ መግለጫ አልሰጠም የሚሉ ጠያቄዎች ከብዙ አቅጣጫ ይነሱ ጀመረዋል፡፡ ከነዚህ መካከል ጋዜጠኛ ዳግማዊ ታሪኩ የደምቢዶሎ ዮንቨርስቲ ተማሪ የነበረችውና በወቅቱ ታፍነው ከተወሰዱት መሀከል አንዷ ለመስማት የሚከብድ ሰቆቃዋን EBS ላይ ተናግራለች።ለመስማት የቻልኩት የተወሰነውን ነው ቪዲዮውን EBS ከዩቲዩብ ላይ አንስቶታል።ጥያቄዬ EBS ለምን አነሳው ሲያነሳው ደግሞ ምክንያቱን ለተመልካቾቹ መግለፅ የለበትም ወይ የሚል ነው ይህንን መሰሉ ቪዲዮ ማንሳት ተገቢው ማብራርያ ካልቀረበ ለብዙ ትርጉም የተጋለጠና አደገኛ ነው።በተማሪዋቹ እገታ ዙርያ ምላሽ ሳያገኝ ለአመታት የዘለቀ ጥያቄ አለ ጉዳዩ በሚገባ ተመርምሮ መቋጫ ሊያገኝ ግድ ነው።(@GizeMedia1974)