У нас вы можете посмотреть бесплатно ቀነኒ ነጋ ጠባ ትደበደብ ነበር!መነጋሪያ የሆነው ፎቶ ያወጣቸው ሚስጥሮች|መራር ሕይወቷ(@Gizemedia1974) или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
''ለምን ጥላ አልሄደችም?''ን የምንመልሰው እሷ ጫማ ላይ ስንቆም ብቻ ነው። አንዳንዴ ነገሩ ውስጥ እስካልሆንን ድረስ ሁኔታውን በትክክል መረዳት አንችልም። የምትሄድበት ባይኖራትስ? ሄዳ ባይለቃትስ? ከዛሬ ነገ ይሻላል እያለች ቢሆንስ? በሷ ቦታ ስንሆን ብቻ ሊገቡን የሚችሉ እና እኛ አሁን ላይ judge ማድረግ የማንችላቸው ብዙ ነገሮች ይኖራሉ። ብቻ እኔ ማለት የምፈልገው፤ እንደዚህ አይነት ነገር ውስጥ ያሉ ጓደኞቻችን የሚልኩልንን ቴክስት የሚሰጡንን መልክት ችላ ሳንል፤ ብዙ ነገር ከመፈጠሩ በፊት በቻልነው እንርዳቸው ። ቀነኒ የዛን ጊዜ ያለችበትን የነገረቻቸው ጓደኞቿ ምን እንዳገዟት አላውቅም። ግን ካረፈች በኋላ ተስፋ የቆረጠችበትን ቴክስት መለጠፍ፣ ለእርዳታ ጥሪዋ ትኩረት መንፈጋቸውን ነው የምረዳበት። ጓደኞቻችሁን ቼክ አድርጉ፤ የሆነ ነገር ከመፈጠሩ በፊት ባይሳካላችሁ እንኳን ልታግዟቸው ሞክሩ። አሁን አሁን ከማየውና ከምሰማው ነገር አንፃር ሰዎች የሚገባቸውን ፍትህ ያገኛሉ ብዬ ማሰብ ባቆምም፤ ሚስኪኗ፣ የተማረች እና ወጣቷ ቀነኒ በአጭሩ በእንዲህ አይነት ሁኔታ መቅረቷ ያሳዝነኛል። ሐቋ እንዲወጣላትም እመኛለሁ። እሷም ሰላም ትረፍ። በእንደዚህ አይነት relationship ውስጥ ያላችሁ፣ የሚመታኝ ስለሚወደኝ ነው ስለሚቀና ነው እያላችሁ ራሳችሁን abuse ለመደረግ አመቻችታችሁ የተቀመጣችሁ ሴቶች የሚመታችሁ ደደብ ስለሆነ ነው፣ ቅናት ደግሞ ጥሩ የፍቅር ስሜት አይደለም እና አስቡበት። ዱላውንም ስድቡንም ችላችሁ ከዛሬ ነገ ይሻላል ይለወጣል ብላችሁ አጋሮቻችሁ እስከሚለወጡ በተስፋ የምትጠብቁ ሴቶች ፤ ዛሬ በሰላም ከነጋ ነው ነገን የምታዩት። በዚህ ሁኔታ ካልነጋላቸው ሰዎች መሐል አንዷ ቀነኒ ናት ከሷ ተማሩ። በመጨረሻ Tewodros Tezera ''ኩባያ ውስጥ ያለች እንቆራሪት የሰማዩ ስፋት በኩባያው አፍ ልክ ነው ብላ ትከራከራለች።" የምትል አባባል ነበረችው። እውነቱን ነው። ያላየነው ከኩባያው አፍ ወዲያ ያለው አለም ነፃነት እና ሰላም ሰፊ ነውና፤ ቤት ውስጥ ለሚገጥማችሁ፣ ህይወታችሁን ሁሉ ሊያሳጣችሁ ለሚችል ጭቆና ፊት አትስጡ። የተሻለ ሰላምና ነፃነት ይገባችኋል። ምርጫ ሳይሆን መብታችሁም ነው። አንዳንድ ነገሮች በአጭሩ ቢቀሩ ጥቅማቸው ብዙ ስለሆነ እንዲህ አይነት ሁኔታዎችን በአጭሩ ለመተው አታመንቱ።(@gizemedia1974)