У нас вы можете посмотреть бесплатно ራስ መኮንን ወልደ ሚካኤል/Ras Makonnen Wolde Mikael የአፄ ኃይለ ሥላሴ አባት или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
መኮንን ወልደ ሚካኤል የተወለዱት በ1844 በጊዜው በመንዝ ክፍለ ሀገር ለአንኮበር ቅርብ በነበረችው በደፈሮ ማርያም ከእናታቸው ከወይዘሮ ተናኜ ወርቅ ሳህለ ሥላሴና የመንዝ እና ዶባ ክፍለ ሀገራት ገዥ ከነበሩት ከአባታቸው ደጅ አዝማች ወልደ ሚካኤል ወልደ መለኮት ነበረ። እናታቸው ሰሎሞናዊ የዘር ግንድ የነበራቸው የሸዋው ንጉስ የሳህለ ሥላሴ ልጅ ነበሩ። በ1858 በ14 ዓመት ዕድሜያቸው መኮንን አባታቸው ወደ ሸዋው መሪ ወደ ንጉስ ምኒልክ ዘንድ ወስደዋቸው የውትድርና ሥልጠና እና የግዛት መሪነት ችሎታን ቀሰሙ። በ1865ም መኮንን የደጅ አዝማች አሊን እና የወይዘሮ ወለተ ጊዮርጊስን ሴት ልጅ የሺ እመቤት አሊን አገቡ። በ1867ም ከመኮንን እና የሺ እመቤት ካልሆነች ከሌላ ሴት ይልማ መኮንን ተወለደ። በ1884 የመኮንን እና የየሺ እመቤት ልጅ ተፈሪ መኮንን ተወለደ። በ1893 ከየሺ እመቤት አሊ ሞት በኋላ መኮንን የእቴጌ ጣይቱ ብጡል የወንድም ልጅ ወይዘሮ ምንትዋብ ወሌን አገቡ፤ ጋብቻው ግን ተራክቦው አልተከናወነም ነበር፤ በ1894 ጋብቻው ተሻረ። የአጎታቸው ልጅ የነበሩት አፄ ምኒልክ ሀረርን በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ከጠቀለሉ በኋላ በ1879 መኮንን የሀረር ገዥነት ተሰጣቸው። ጁልስ ቦሬሌ እንዳለው ከሆነ የተበዘበዙት ሀረሪዎች ለመኮንን ወዳጃዊ እይታ ቢኖራቸውም ሀረር ግን በአቢሲንያ ወታደሮች ወታደራዊ ዝርፍያ ተከናወነባት፤ ግማሹ ህዝብም ሸሸ። ሀረሪዎች በሚገልጹት መሰረት የሀረሪ ህዝብ ጭቆና የጀመረው ሀረር በራስ መኮንን መወረሯን ተከትሎ መስጊዶች ወደ ቤተ ክርስትያን መቀየራቸው እና የአቢሲንያ ክርስትያኖች ከሰሜን ተነስተው በመምጣት በከተማዋ በመስፈራቸው ነው። መኮንንም የሀረር ዋና መስጊድ ወደ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን እንዲቀየር አዘዙ። ፈረንሳያዊው ተጓዥ የነበረው ቻርልስ ማይክል እንደገለጸው ከሆነ አቢሲንያውያን የያዙባቸው የመጀመርያዎቹ ዓመታት ከመበልጸግ የራቁ ነበሩ፤ ምክንያቱም ዋጋ ያለውን ነገር ሁሉ ይወስዱ ነበርና፤ በጊዜውም በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች ሀረሪዎችን ከቤታቸው እያስወጡ እነሱ በቦታቸው ይቀመጡ ነበረ፤ በዙርያቸው ያለውንም ነገር ሁሉ ያወድሙ ነበር። ንግድ እና ነጋዴዎችም ከከተማው ተባረሩና ገበያዎች በገጠራማው ክፍል ይከናወኑ ጀመረ። በጊዜያትም መኮንን የሀረር መሬቶችን በመውረስና ለወታደሮቻቸው በመስጠት የሀረሪዎችን ሀብት አዳከሙ። በሀረርም መኮንን ከውጪ ከመጡ ሰዎች ጋር ጥሩ ግንኙነት አግኝተዋል፤ እነዚህም የካፑችን ሰባኪዎችን እና የተጓዥ ቁጥራቸው የጨመረውን ወደ ዋናዋ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ሲሄዱ በመንገድ ያገኙዋቸውን አውሮፓውያንን ያካትት ነበረ። በዛም መኮንን ስለ ውጪው ዓለም የተቻላቸውን ያህል እውቀት ቀሰሙ። በተለይም ደግሞ ለራሽያ ሰዎች ጥሩ ስሜት ነበራቸው፤ የዚህም ምክንያት በሚጋሩት የኦርቶዶክስ እምነት እና ራሽያዎች እንደ ምዕራብ አውሮፓውያን ኢትዮጵያን ቀኝ የመግዛት አላማ ስለሌላቸው ነበረ። መኮንን ለመሳርያዎች ፍቅር ነበራቸው እናም በአካባቢው በሚደረገው የመሳርያ ሽያጭ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ተሳትፎ ያደርጉ ነበረ፤ መሳርያዎችንም ከውጪ በማስመጣት ግማሹን ወደ ሸዋ ልከው ሌላውን ደግሞ በቅርብ የሚገኙትን የሶማሌ ሰዎች ለማስገዛትና ግብር ለመቀበል ይጠቀሙባቸው ነበረ። መኮንንም የኢትዮጵያ ግዛት ከሀረር ወደ ምስራቅ እና ወደ ደቡብ እንዲስፋፋ አደረጉ። በሂደትም የኢሳን እና የገዳቡርሲን አካባቢ ተቆጣጠሩ። በ1882 ከአዲስ አበባ የተላኩላቸው ተጨማሪ ወታደሮች በ1883 ሙሉ ኦጋዴንን እንዲቆጣጠሩ አስቻላቸው። በ1888 ራስ መኮንን አብዱላህ ታሂርን የጂግጂጋ ገዥ አድርገው ሾሙት። በ1898 የጣልያኗ ኤርትራ ገዥ የነበረው ፈርዲናንዶ ማርቲኒ በኢትዮጵያ ውስጥ ህጋዊ ጉብኝት እያካሄደ ነበረ። ዳግማዊ ምኒልክም ራስ መኮንን ወደ አዲስ አበባ ይመጡ ዘንድ ጠሯቸው። ራስ መኮንንም ከሀረር ተነስተው ወደ አዲስ አበባ በሚመጡበት ወቅት በታይፈስ በሽታ ታመሙ። ወታደሮቻቸውም ወደ ቁልቢ ወሰዷቸው፤ በዛም ሳሉ ለልጃቸው ተፈሪ በሹክሹክታ ቡራኬ ከሰጡ በኋላ ሞቱ። ምኒልክም የአክስታቸው ልጅ እንደሞቱ በሰሙ ጊዜ እጅግ እንደተጨነቁና ለሦስት ቀን ያህል በበረታ ሐዘን ውስጥ እንደነበሩ ይነገራል። ማጣቀሻ(Reference) https://en.m.wikipedia.org/wiki/Makon...