У нас вы можете посмотреть бесплатно የአዲስ ኪዳን ዳሰሳ |ወደ ፍልጵስዩስ ሰዎች | ክፍል 1 | አስፋው በቀለ (ፓ/ር) или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
ታሪካዊ ዳራ የፊልጵስዩስ ከተማ የሰሜናዊ ግሪክ ክፍለ አገር የነበረችው መቄዶንያም ዋና ከተማ የነበረች ሲሆን የምትጠራውም በታላቁ እስክንድር አባት በመቄዶንያው ንጉስ በዳግማዊ ፊልጶስ ስም ነበር። የሐዋርያው ጳውሎስ በነበረበት ዘመን ፊልጵስዩስ የሮም ቅኝ ግዛት ስለነበረች የታወቀችና ብዙ የሮም ዜጎችና ወታደሮች በዚያ ይኖሩ ነበር(የሐ16:12) ። የፊልዽስዩስ ቤተ ክርስቲያን የተመሰረተችው በጳውሎስና አብረው ያገለግሉ በነበሩት ሲላስ፣ጢሞቴዎስና ሉቃስ በሚገኙበት ቡድን ሲሆን የሐዋርያው ጳውሎስ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ፊልዽስዩስ የሄደው እግዚአብሔር በጢሮአዳ ለሰጠው ራእይ ምላሽ ለመስጠት ሁለተኛውን የወንጌል ተልዕኮ ባደረገበት ወቅት ነበር ። ራእዩም አንድ የመቄዶንያ ሰው “ወደ መቄዶንያ ተሻገርና እርዳን “ብሎ ሲናገረው መመልከቱ ነበር (የሐዋ 16:9-40) ። በሐዋርያው ዻውሎስና በፊልዽስዩስ ቤተ ክርስቲያን መካከል ጠንካራ ወዳጅነት ተፈጠረ።ብዙ ጊዜ ቤተ ክርስቲያኗ ለዻውሎስ የገንዘብ እርዳታ አድርጋለች፤ በኢየሩሳሌም ያሉትን ችግረኞች ለመርዳት ገንዘብ በሚያሰባስብበትም ጊዜ ይህች ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ልግስና እጅዋን ዘርግታለች (2ቆሮ11:9 ፣ ፊል4:15-16) ። በሦስተኛው ሚሲዮናዊ ጉዞው ወቅት ሐዋርያው ጳውሎስ የፊልጵስዩስን ቤተ ክርስቲያን ሁለት ጊዜ የጎበኘ ይመስላል (ሐዋ 20:1-6) ። የሐዋርያው ጳውሎስ ሦስቱ የወንጌል ተልዕኮ ጉዞዎች በመባል የሚታወቁት የሚከተሉት ናቸው: ❖ የመጀመሪያው /Paul’s 1st Missionary Journey/ ከአንጾኪያ (ሐዋ13:1-4) ❖ ሁለተኛው/ Paul’s 2nd Missionary Journey//ከአንጾኪያ (ሐዋ15:36-18:22) ❖ ሦስተኛው/Paul’s 3rd Missionary Journey/ከአንጾኪያ (ሐዋ18:23-20:38) ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት ይህን መልዕክት ከ 60-61 ዓ. ም ገደማ በመጀመሪያው በሮም እስር ቤት እያለ ለፊልዽስዩስ ሰዎች እንደጻፈ ያምናሉ።እነዚህ ሊቃውንት ጳውሎስ በዚሁ እስር ላይ እያለ ለኤፌሶንና ለቆላስይያስ ሰዎች እንዲሁም ለፊልሞና እንደጻፈ ያምናሉ። ቅኝት ከብዙዎቹ የጳውሎስ መልዕክቶች በተለየ ሁኔታ ወደ ፊልዽስዩስ ሰዎች የተላከው መልዕክት የተጻፈው በቤተ ክርስቲያኗ ችግር ወይም ግጭት ተፈጥሮ አይደለም። የተጻፈበት መሠረታዊ ምክንያት የቤተ ክርስቲያኒቱ ምዕመናን ለወንጌል ስራና ለጳውሎስ ላሳዩት ፍቅር ልባዊ ምስጋናውን ለመግለጽ ፣የክርስቲያን የመኖር ዓላማና የዘላለም ሕይወት ተስፋ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ መሆኑን በመግለጽ እርሱን ማወቅ ደግሞ ከሁሉም የሚበልጥ ጥቅም ያለው መሆኑን አውቀው ይተጉ ዘንድ ለማበረታታት ነው። ለዚህም የክርስቶስን ፈለግ በመከተል በትሕትና ፣ በአንድነትና በሰላም ጌታን እንንዲያገለግሉና የደስታቸውንም መሠረት እርሱን እንዲያደርጉ ለማበረታታትም ነው።በተጨማሪም ዻውሎስ ይህን መልዕክት የጻፈው በእስራቱ ሁሉ የእግዚአብሔር ዐላማ እንዲፈጸም ለቤተ ክርስቲያኒቱ ምዕመናን ለማረጋገጥ ነው (ፊል1:12-30) ። ተጨማሪ የፍልጵስዩስ ዝርዝር 7 ትምህርቶች ቀደም ብለው የተቀረጹ በዚህ ሊንክ ያገኛሉ፡ • Philipians/ፍልጵስዩስ