У нас вы можете посмотреть бесплатно በባሌ ሮቤ እና አሰላ የ5ጂ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር | 5G Launching Event at Bale Robe & Asella или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
በባሌ ሮቤ እና አሰላ ከተሞች የ5ጂ አገልግሎት የተጀመረ ሲሆን በደቡብ ምስራቅና ደቡብ ደቡብ ምስራቅ ሪጅኖች 114 ከተሞችን የ4ጂ ኤልቲኢ አድቫንስድ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረጉን ስንገልጽ በደስታ ነው! በባሌ ሮቤ ከተማ 5ጂ ኔትወርክ ዋቆ ጉቱ አደባባይ፣ ሮቤ የኢትዮ ቴሌኮም ነባሩ ህንጻ፣ ባሌ ዞን ት/ት ቢሮ፣ ሮቤ ቴክኒክ እና ሙያ ሥልጠና ኮሌጅ እና መደወላቡ ዩንቨርሲቲ ዋና ግቢ አካባቢ ይሸፍናል፡፡ በአሰላ ከተማ ደግሞ 5ጂ ኔትወርክ የአሰላ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት፣ ነባሩ የኢትዮ ቴሌኮም ቢሮ፣ አሰላ ስታዲዮም፣ ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ እና አሰላ ትምህርት ቢሮ አካባቢዎችን የሚሸፍን ነው፡፡ በተጨማሪም ኩባንያችን በሁለቱ ሪጅኖች ሲያከናውን የነበረውን ግዙፍ የ4ጂ ኤልቲኢ አድቫንስድ ኔትወርክ ማሳደጊያ እና ማስፋፊያ ፕሮጀክት በማጠናቀቅ በአሁን ወቅት 114 ከተሞችን የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ ችሏል፡፡ 5ጂ እና 4ጂ ኤል.ቲ.ኢ ኔትወርክ አገልግሎቶችን በመላ ሀገሪቱ ተደራሽ በማድረግ ለዜጎች አካታች የዲጂታል ሶሉሽኖችና ዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች ተጠቃሚ በማድረግ የሀገራችን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ለማፋጠን ጉልህ ሚና ይኖረዋል፡፡ ክቡራን ደንበኞቻችን፣ የ5ጂ እና 4ጂ አገልግሎቶችን ማስተናገድ የሚያስችሉ ቀፎዎች እና ሲም ካርዶችን በአገልግሎት ማእከላችን በማግኘት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንጋብዛለን፡፡ ለተጨማሪ፡- https://bit.ly/3XSgLkD