У нас вы можете посмотреть бесплатно Sheger Liyu Were - እናትና ልጅ ከ42 ዓመታት በኋላ ሲገናኙ - ሸገር ልዩ ወሬ - Wondimu Hailu или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
Sheger Liyu Were - እናትና ልጅ ከ42 ዓመታት በኋላ ሲገናኙ - ሸገር ልዩ ወሬ - Wondimu Hailu #ShegerFM #WondimuHailu #LiyuWere በምስሉ ላይ የሚታዩት ወ/ሮ ሐሊማ ኑኑ ያሉትን መሀል ላይ የሚታየውን ልጃቸውን የወለዱት የዛሬ 42 ዓመት ነው፡፡ ያኔ ፊናንስ ፖሊስ የነበሩት የኑኑ አባት ከሥራቸው ተሰናበቱ፡፡ ጥቂት ቆይቶ ደግሞ አባት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡ ኑሮ የከፋችባቸው ወ/ሮ ሐሊማ ኑኑን ስዊዲን ኤምባሲ ለምትሰራ ስዊዲናዊት ሴት በጉዲፈቻነት ሰጧት፡፡ ከዚያን በኋላ ላሉት ዓመታት ልጅቸው ሲታወሳቸው ማንባት ሆነ፡፡ “የልጄን ነገር ሳስታውስ ኡኡ ብዬ እቃ እሰብራለሁ - ጎረቤቶቼ ያውቃሉ” ይላሉ ወ/ሮ ሐሊማ፡፡ “የውጭ ሐገር ኳስ ማየት እወዳለሁ” የሚሉት ወ/ሮ ሐሊማ፣ “ፀጉሩ ያመረ ሰው ሳይ ልጄ ይሆን እንዴ እላለሁ” ይላሉ፤ “42 ዓመት ሙሉ በእሱ ጥበብ ነው እንጂ ያለሁት እንደኔ ማልቀስ ወዲያው ልቤ የሚቆም ነበረ…” ስፍር ቁጥር ለሌላቸው ጊዜያት ስዊዲን ኤምባሲ እየተመላለሱ ስለልጃቸው ጠየቁ፡፡ መልስ የለም፡፡ ትዳር መስርተው 4 ልጆች አፈሩ፡፡ የእናቱ በልጃቸው እንዲህ መብከንከን አላስችል ያለው በምስሉ ላይ በሰተቀኝ በኩል የሚታየው ሐሰን የተባለው ልጃቸው ኑኑን በኢንተርኔት ማፈላለግ ጀመረ፡፡ እናም ተሳክቶለት እነሆ እናትና ልጅ ከ42 ዓመታት በኋላ ለመተያየት በቁ፡፡ የወ/ሮ ሐሊማን ደስታ ቃላት አይገልፀውም፡፡ አሁን ላይ ስዊዲን ውስጥ ታዋቂ ተዋናይ የሆነው የ42 ዓመቱ የድሮው ኑኑ የአሁኑ ማርስ እናቱ ሞተዋል ብሎ ነበር የሚያስበው፡፡