У нас вы можете посмотреть бесплатно DW Amharic የመጋቢት 20 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
የመጋቢት 20 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና በአማራ ክልል የተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች በሥራ ላይ የሚገኙ የአማራ የክልል ገቢዎች ቢሮ ሠራተኞች የተፈቀደላቸውን የደመወዝ ጭማሪ እንዲከፈላቸው ጠየቁ። በአማራ ክልል የተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች በሥራ ላይ የሚገኙ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ሠራተኞች አሁን የሚከፈላቸው ደመወዝ ኑሮአቸውን በአግባቡ እንዲመሩ ባለማስቻሉ የደመውዝ ማሻሻያ እንዲደረግላቸውና ጥቅማጥቅሞች እንዲከበርላቸው ለበርካታ ጊዜ ሲጠይቁ እንደነበር ይገልፃሉ። በትላንትናው ዕለት በምያንማር ባጋጠመ ርዕደ መሬት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ1,600 መብለጡን የሃገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቁ። በአደጋው ከ 3,400 በላይ ሰዎችም ቆስለዋል። ትላንት በማዕከላዊ የሐገሪቱ ግዛት ያጋጠመው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 7 ነጥብ 7 የተለካ ሲሆን በርካታ ሕንጻዎችን ጨምሮ የተለያዩ መሰረተ ልማቶችንም አፈራርሷል። የመሬት መንቀጥቀጡ ዛሬም ተከስቶ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። ሩስያ ለሊቱን ለዛሬ አጥቢያ በማዕከላዊ የዩክሬይን ግዛት ዴኒፕሮ በፈጸመችው የሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት በትንሹ 4 ሰዎች መገደላቸውና 21 መቁሰላቸውን የዩክሬይን ባለስልጣናት አስታወቁ። የግዛቷ አስተዳዳሪ ሰርሂ ሊሳክ «በከተማዋ ከባድ ፍንዳታዎች ተደምጠዋል ብዙ ጉዳትም ደርሷል» ብለዋል። አሜሪካ በሶሪያ የሚገኙ ዜጎቿ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክት አስተላለፈች። በሶሪያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ከሮመዳን ፆም ፍቺ በኋላ በተለያዩ ተቋሞች ላይ የአሸባሪዎች ጥቃት ሊፈጸም እንደሚችል አመላክቷል።