У нас вы можете посмотреть бесплатно በሦስት ትውልድ ዘመን እየደመቀ የሄደ ቀለም - ሠዓሊ ገብረ ክርስቶስ ሰሎሞን በላቸው ይመር или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
መንደርደሪያ፤ ከሠዓሊ ገብረ ክርስቶስ ጋር ከአንድ ዓመት በፊት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ያለቀጥሮ ነበር የተገናኘነው። ባለፈ ትዝታ ሞተር እየተገፋሁ፣ የጠዋቱ አየር ግለቱ ሳይጨምር የቸርችል ጎዳናን አቀበት ወጥቼ፣ የ’ክሪያዚዝን’ ጣፋጭ ኬክ አጣጥሜ ካበቃሁ በኋላ ወደ ፒያሳ ሳመራ ነበር ስቱዲዮውን በድንገት ያየሁት። በሠዓሊው የተሠሩ ይሆናሉ ብዬ የገመትኳቸውን ስዕሎችና አንዲሁም የተለያዩ የእደ ጥበብ ውጤቶኝ በመስኮት አሾልቄ ስላየሁ፣ ባልገዛም ገብቼ ልይ የሚል ጉጉት አደረብኝና ወደ ውስጥ ዘልቄ ከገባሁ በኋላ ከሠዓሊ ገብረ ክርስቶስ ጋር ያደረግነው አጭር ጭውውትም ለዚህ የጉዞ ማስታወሻ መመዝገብ ምክንያት ሆነ። የሰማሁት የሦስት ትውልድ ወግ ነበረና ቀልቤን ሳበው። ያጫወተኝን ታሪክ ላልሰሙ ለማካፈል ፈቃደኛ እንደሆነ ጠይቄው ያለማቅምማት ስለተስማማ፡ በማስግቱ ካሜራዬን ይዤ እንደምመጣ፣ አሱም ተዘጋጅቶ እንደሚጠብቀኝ ተስማማንና ተለያየንን። በቸር አድረን ደግሞ ለመገናኘት በቃን፣ ያሰብነውንም አደረግን። ቀኑ ደረሰና እነሆ የዚያ ያልታሰበ ግንኙነት ውጤት በዚህ መሸኛ ደብዳቤ አጃቢነት ወደርስዎ ተላከ። ሠዓሊ ገብረ ክርስቶስና አኔ ከዚያ በፊት ትውውቅ አልነበረንም፤ ይህ ቪዲዮ ከተቀረጸበት ቀንም ጀምሮ ዛሬ በ’ቀጭኑ ሽቦ’ ክመነጋገራችን በስተቀር በአካል እስካሁን አልተገናኝንም፣ ። የወደፊቱንም እግዚአብሄር ያውቃል። እንደኔ ይህ ዕድል ላልገጠማችሁ ወገኖቼ፣ እኔ ባይኔ ያየሁትን ባይናችሁ እስከምዩታና የሰማሁትን እስከምትሰሙ ድረስ መዳረሻ አንዲሆናችሁ ያለኝን ሳካፍላችሁ ወድጃለሁና ግብዣዬን አንደምትቀበሉ ተስፋ አደርጋለሁ። ምርቃት ነጥቶ አላስከበረኝ፣ ጠቁሮ አላዘነጠኝ የኔውስ ጎፈሬ፣ መላ አጥቶ አስቸገተረኝ። ባመድ የኳሉት ዐይን፣ መስሎ እንኳ ቢታይም፣ አባብሰው መስሎት፣ ይሻላል ባያልም።