У нас вы можете посмотреть бесплатно አግዚአብሔር አዲስን ነገር ያደርጋል! или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
ልዩ ምስጋና ለሲኤምሲ ገነት ቤተክርስቲያን(የቀረጻ ስፍራን በማዘጋጀት) የኢትዮጵያ ገነት ቤተክርስቲያን ቅዱሳንን እና ወዳጆች በሙሉ እንኳን ለኢትዮጵያ ገነት ቤተክርስቲያን 74ኛ የምስረታ አመት በሰላም አደረሳችሁ! የዛሬ 74 ዓመት በንጉስ ጃንሆይ ዘመነ መንግስት የወንጌልን እሳት ይዘው ወደ ኢትዮጵያ የመጡቱ የፊንላንድ ሚስዮናዊያን ነበሩ፡፡ ያኔ የተለኮሰው የወንጌል እሳት ብዙዎችን እያንበረከከ ህዝቡን እንደጋለ ነሐስ እያጋመ እና ገለባውን አመድ እያደረገ፤ ከምዕራብ እስከ ምስራቅ፣ ከደቡብ እስከ ሰሜን እያንፀባረቀ 74 ዓመታትን አስቆጥሮ ዛሬም በምድሪቱ ስፋት እንደተንበለበለ አለ፡፡ ዛሬ ላይ የኢትዮጵያ ገነት ቤተክርስቲያን ከ3.1 ሚሊየን በላይ አባላት፣ 1844 በላይ አጥቢያ ቤተክርስቲያናት፣ 632 በላይ የወንጌል ጣቢያዎች አሏት፡፡ ቤተክርስቲያኒቱ ራዕይ 5555፤ ማለትም በሚመጡት አምስት አመታት 5ሚሊየን ሰዎችን በወንጌል ለመድረስ 5 መቶ ሚስዮናዊያንን መላክ እና 5 መቶ የሚብዛዙ ቤተክርስቲያንትን መትከል የሚል የትግበራ ራዕይን ይዛ በመጓዝ ላይ ስትሆን በራዕዩ አፈፃፀም ረገድ በ2016 ዓ.ም 235 በላይ ሚሲዮናዊያንን ያሰማራንበት ሲሆን 362433 ሰዎች ወንጌልን ሰምተው 15960 ሰዎች ጌታ ኢየሱስን እደግል አዳኛቸው እና ጌታቸው አድርገው የተቀበሉበት 6998 ሰዎች ቀጠሮ ሰጥተው 7714 ሰዎች የውሃ ጥምቀት ስርአት የፈፀሙበት ፣ 211 ቤተክርስቲያናትን መትከል የተቻለበት ዓመት ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ገነት ቤተክርስቲያን የህዳር ወርን የኢትዮጵያ ገነት ቤተክርስቲያን ወር በሚል መሰየሟ ይታወቃል። በዚህ ወር ቤተክርስቲያኒቱን አስመልክቶ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተለያዩ ስራዎች የሚሰሩ ሲሆን በወሩ የመጨረሻ እሁድ ማለትም ህዳር 29/2017ዓ.ም በአለም አቀፍ ደረጃ ስጦታ የምንሰጥበት ጊዜ ሲሆን፤ የሚሰበሰበው ስጦታ ወደ ኢትዮጵያ ገነት ቤተክርስቲያን ብሔራዊ ጽ/ቤት በሚከተሉት አካውንት በቀጥታ ገቢ ይሆናል። የንግድ ባንክ :- ኢትዮጵያ ገነት ቤተክርስቲያን 1000228894412 የብርሃን ባንክ:- ኢትዮጵያ ገነት ቤተክርስቲያን 1500050019374 አቢሲኒያ ባንክ:- ኢትዮጵያ ገነት ቤተክርስቲያን 136310461 ከቤተክርስቲያኒቱ ጎን መቆም ለምትፈልጉ እና እግዚአብሔር የተለየ ሸክም የሰጣችሁ ወገኖች ከላይ በተቀመጠው አካውንት ስጦታችሁን ገቢ ማድረግ ትችላላችሁ። እንዲሁም የተለያዩ ስጦታዎችን በአይነት መስጠት የምትፈልጉ የኢገቤ አስተዳደር እና ፋይናንስ የስልክ አድራሻ +251905252627 የኢገቤ ፕረዝዳንት መጋቢ ታምራት ታሪኩ +251 91 782 1847 ላይ በመደወል ስጦታችሁን በማስመዝገብ መስጠት ትችላላችሁ፡፡ በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ! እግዚአብሔር የኢትዮጵያ ገነት ቤተክርስቲያንን እና ቅዱሳንን ሁሉ ይባርክ!