У нас вы можете посмотреть бесплатно እነዚህ 4 ነገሮች ወደ ምንፈልግበት ቦታ ያደርሱናል или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
አሁን ካለንበት ቦታ ወደፊት መሄድ ሁላችንም እንፈልጋለን፡፡የአብዛኞቻችን ህይወት አንድ ቦታ እንደተቀረቀረች መኪና ቀጥ ብሎ ቆሟል፡፡ወይም አንድ አይነት ስሀተት ከአመት አመት እንሰራለን፡፡በዚህ ቪዲዮ አሁን ካለንበት ተነስተን ወደ ወደድንበት ቦታ እንድንደርስ የሚረዱ 4 ሀሳቦችን አንስቻለው፡፡የመጀመርያው ችግራችንን ማወቅ ነው፡፡ችግሩን ያላወቀ ሰው ሊቀርፈው አይችልም፡፡ችግሩን ብቻ ሳይሆን የችግሩን ምክንያትም ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ይህን ለማድረግ ከራሳችን ጋር ያለማቋረጥ መወያጥ አለብን፡፡የሰው ልጆች ራሳችንን ልክ እንደሌላ ሰው አድርግን የመገምገም አቅም አለን፡፡ይህንን አቅም በመጠቀም የራሳችንን ችግር አንድ በአንድ ለቅመን እናውጣው፡፡ሁለተኛው ከችግሩ በላይ ከፍ ያለ አዲስ አላማ መንድፍ ነው፡፡ብዙ ሰው አሁን ውስጥ ባለ ወይም ከትላንት በመጣ የችግር ሳጥን ውስጥ ተግድቧል፡፡ስኬታማ ሰዎች ግን ከችግራቸው በላይ ከፍ ብለው የነገን ተስፋ መመልከት ይችላሉ፡፡አሁን ካሉበት ሳጥን ውስጥ ወጣ ብለው የነገ አለማቸውን በውስጣቸው ይፈጥራሉ፡፡እኛም ይንን ማድረግ አለብን፡፡ምን አይነት መጻኢ ጊዜ እንደምንፈልግ ቁልጭ አድርገን መፍጠር አለብን፡፡ሶስተኛው በፈጠርነው አዲስ አላማ ማመን ነው፡፡በልባችን አላማው ልክ እንደተሳካ አድርገን በማመን በውስጣችን ለአለማው ቅርጽ ምስጠት እንችላለን፡፡እምነት ከማይታያው የፈጣሪ መንፈስ ጋር የማይታየውን አላማችንን በማገናኘት የማይቻለውን ማድረግ ነው፡፡እምነት ከፈጣሪ ጋር በመንፈስ መግባባት ነው፡፡ለሚያምን ሁሉ ይቸላል ይባላልና ከማድረጋችን በፊት አዲሱን አላማ በውስጣችን እንመነው፡፡የመጨረሻው ማድረግ ነው፡፡እምነት ያለድርጊት ኪሳራ ነው፡፡ስራ የሌለበት እምነት ከንቱ ነው፡፡በአዲሱ አላማ በሙሉ ልቡ ያመነ ሰው በሙሉ አእምሮ፣ ሰውነት እና መንፈስ እርምጃ ይወስዳል፡፡የሚያስበውም ይከናወንለታል፡፡ማድረግ ብቻ ሳይሆን በትክክለኛው መንገድ ፈጥኖ ማድረግ አላማችንን ፈጥነን በማሳካት አሁን ካለንበት ወደፊት እንድንሄድ ያደርጋል፡፡ #habesha #ethiopia #motivation #amharic #success #america #usa