У нас вы можете посмотреть бесплатно Ethiopia Sheger FM - Sinksar Documentary - ሁለቱ የግንቦት ፍንዳታዎች или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
#Ethiopia #ShegrFM #SinkisarDocumentary Ethiopia Sheger FM - Sinkisar Documentary 2ቱ የግንቦት ፍንዳታዎች፣ ከ1 500 እስከ 3 000 ያህል ሰዎች ስለሞቱበት ስለ ግንቦት 20፣ 1983ቱ የሸጎሌ የጥይት ፋብሪካ ፍንዳታ ምን ያህል ያውቃሉ ? እሁድ ግንቦት 21 ቀን 2008 ዓ.ም በሸገር የዶክመንተሪ ፕሮግራም (ስንክሳር) ላይ የቀረበው “2ቱ የግንቦት ፍንዳታዎች” የተሰኘው ዶክመንተሪ የዛሬ 29 ዓመት አዲስ አበባን ስላናወጡትና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት ስለቀጠፉት ሁለት ፍንዳታዎች ያልተሰሙ መረጃዎችን አስደምጦናል፡፡ ግንቦት 20፣ 1983 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 እስከ 7፡30 ባለው ጊዜ ውስጥ የተከሰተው የሸጎሌው የጥይት ፋብሪካ ፍንዳታ ከብዙዎች ትውስታ ቢጠፋም የአካባቢው ሰዎች ግን አሁን የሆነ ያህል ያስታውሱታል፡፡ በዚህ ፍንዳታ ከ1 500 እስከ 3 000 ያህል ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ዶክመንተሪው ይነግረናል፡፡ ዶክመንተሪውን ያዘጋጀው ዮሐንስ የኋላወርቅ ያነጋገራቸው የአካባቢው ሰዎች፣ “በሸጎሌው ፍንዳታ በሟቾች ብዛት የተነሳ ሬሳ ማንሻ ጠፍቶ የብዙዎች አስክሬን በጆንያ እንደተጠቀለለ፣ እድሮች ለሟች ቤተሰቦች መክፈል እንደተሳናቸው” ያስረዳሉ፡፡ የዚህ ፍንዳታ መንስዔ አሁን ድረስ በይፋ ባይታወቅም የአካባቢው ሰዎች ግን በሚሳዔል ተመታ ማለታቸውን ዶክመንተሪው ይነግረናል፡፡ አዲስ አበባ ሁለተኛውን ፍንዳታ ያስተናገደችው ደግሞ የሸጎሌው ፍንዳታ በደረሰ በሳምንቱ ግንቦት 27 ቀን 1983 ዓ.ም ነበር፡፡ በበቅሎ ቤቱ የመሳሪያ ማከማቻ ላይ በደረሰው ፍንዳታም እንደሸጎሌውም ባይሆን በርካቶች ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡ ዶክመንተሪውን እንድታዳምጡ ጋብዘናል… #Ethiopia #ShegerFM #Sinkisar #የግንቦት_ፍንዳታዎች Sheger FM 102.1 Radio is The First Private FM Radio Station in Ethiopia youtube channel:https://bit.ly/2ychCUy Website:https://www.shegerfm.com/ Facebook: / sheger102.1 Telegram:https://t.me/EthioshegerFmRadio Twitter:https://twitter.com/shegerfm?lang=en Mobile Application ከApple Store እና play store ያውርዱ https://play.google.com/store/apps/de... https://apps.apple.com/app/id847859021