У нас вы можете посмотреть бесплатно ሙስሊሞች ማወቅ ያለባቸው የረመዷን ፈታዋዎች | ክፍል 7 | ኡስታዝ አህመድ ሸይኽ አደም или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
በዚህ ዳርስ ኡስታዝ አህመድ ሸይኽ አደም ስለ ረመዷን ጋር የተያያዙ ወቅታዊ ፈታዋዎች በግልፅ እና በጥልቀት ያብራራሉ። በዚህ ትምህርት ውስጥ፦ የረመዷን ፈታዋዎች የጾም ህጎች ሙስሊሞች ማወቅ ያለባቸው አስፈላጊ ጉዳዮች #ረመዷን #ፈታዋ #ኡስታዝ_አህመድ_ሸይኽ_ኣደም #ጾም #ኢስላማዊ_ትምህርት #ፉርቃን_ሚዲያ #Ramadan2026 #EthiopianMuslims #FurqanMedia ጥያቄዎቹ እንደሚከተለው ቀርበዉላችኋል 1/ከፉጡር በኃላ በጣም ስራ ስለሚበዛብኝ የግድ ስራውን መጨረስ ኩንትራትም ስለሆንኩኝ የዒሻና የተራዊህ ሶላትን እንደ ኢትዮጵያዊ አቆጣጠር እስከምሽቱ አራት ሰዓት ባዘገየው እችላለሁኝ? 2/ዐረብ ቤት የምንሰራ ሰዎች በቂ ጊዜ ስለማናገኝ የተራዊህን ሶላትን ስንሰግድ ባገኘነው ስኣት እያቆራረጥን መስገድ እንችላለን ወይ? 3/በረመዷን በቀኑ ክፍለ ጊዜ ባልና ሚስት ስሜታቸውን በሚቀሰቀስ ሁኔታ ቢያወሩ መድይ ቢወጣቸው ወንጀለኛ ይሆናሉ? ? የመዲይ መውጣቱስ የሚፈጥረው ችግር አለን? ወንጀለኛ ያደርጋል ወይ? 4/ነስር ፆምን ያፈርሳልን? 5/በረመዷን በቀኑ ክፍለ ጊዜ ብኹር ወይም እጣን ማጨስ ፆምን ያበላሻልን? 6/የምኖረው በአውሮፓ ነው ከቸርች በካርድ ወይም በኩፖን ወይም በካርድ ገንዘብ አድርገው ይሰጡንና በካርዱ ሄደን ከሱቅ ምግብ ወይም ልብስ እንገዛለን ይህን ገንዘብ ተጠቅመን በገዛነው ምግብ ማፍጠር እንችላለን ወይ? በሌላም ጊዜ ቢሆን ይህን መጠቀሙ እንዴት ይታያል? 7/የ6ወር እርጉዝ ነኝ አንድ ቀን በጣም ፆሙ አድክሞኝ ባፈጥር ወንጀል ይሆንብኛል ወይ? 8/ከባለቤቴ ጋር በረመዷን ፈጅር ከመድረሱ በፊት ግንኙነት እያደርግን እያለ አዛን አለ ምን ማድረግ ያለብን? 9/ጓደኛየ በጣም ያማታል መፆም አትችልም ሰላሳ ሚስኪን በየቀኑ ለማብላት አይመቻትም ስለሚያማትም ሚስኪን ያለበት ቦታ ሄዳ መፈለግ አልቻለምና ለ30ሚስኪን የሚሰጠውን ለአንድ ሚስኪን ብቻ መስጠት ይቻላል ወይ? 10/ሀገር ቤት ቤተሰቦቻችን በየአመቱ ረመዷን 15ኛው ቀን ላይ የረመዷን ሰደቃ ብለው የአካባቢ ሰብስበው አርፈው ይከፋፈላሉ ይህ ነገር እንዴት ይታያል? 11/የምሰራበት ቤት ጎረቤቴ አንዲት ጓደኛ አለችኝ አስሪዋ ምግብ በጣም ሰለትምቆጥብባት እየደበቅኩን ከእኛ ቤት እየወሰድኩ እሰጣታለሁ ረመዷን ላይ እኔ ያለሁበት ቤት ምግብ በጣም ይተርፋል ፣ይደፋሉ ከሚደፋ ብየ ነው የምሰጣት ሰዎቹ ሳያውቁ በመስጠቴ ሀራም ይሆንብኛልን? 12/አንድ ሰው እንቅልፍ የሚያስቸግረው ከሆነ ረመዷን ውስጥ ከዒብዳ እንዛይዘናጋ ብሎ እንቅልፍ የሚከለክል መድኃኒት(ክኒን)መውሰድ ይቻላልን? 13/ወንድሜ ያለፈው ኣመት ረመዷን ሙስሊም የሌለበት ሀገር ሄዶ 15ቀን አልፆመም አሁን በምን መልኩ ነው ቀዷ ማውጣት ያለበት? 14/ በባህር የመጡ እዳ ያለባቸው ስራም የላቸውም ከጀመዓው እየዞሩ ነው ምግብም የሚያገኙት ለእነዚህ ሰዎች ዘካተል ፊጥርን መስጠት ይቻላልን? 15/ያለሁት መካ ነው ከአጎቴ ልጅ ጋር ኡምራ ለማድረግ ፈልገን ነበር ኢህራም የምናደርገው ከየት ነው?ከመስጂደል ዓኢሻ ነው ወይስ ከቤት ነው ኢህራም የምናደርገው? 16/ለእናትና ለአባቴ በአንድ ጊዜ ኡምራ ማድረግ እችላለሁ ወይ? 16/ለእናቴ ኡምራ ላደርግላት ፈልጌ ነበረ በህይወት አለች ጤነኛ ናት ለመምጣት ገንዘብ የላትም እኔ ላደርግላት እችላልሁን?ከቻልኩስ ለእሷ ማሳወቅ አለብኝን?