У нас вы можете посмотреть бесплатно ራስ ምታት መንስኤ,ምልክቶች እና መፍትሄ| What is Headache? или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
#youtube #headache #ራስ_ምታት ➥ ራስ ምታት ማለት በየትኛውም የራስ ክፍል ላይ የሚሰማ ህመም ነው፡፡ ህመሙ ሙሉ የራስ ቅልን፣ ከፍሎ ወይም አንድ ቦታ ላይ ብቻ ሊሰማ ይችላል፡፡ ተያይዞም ከአንዱ ወደ ሌላ ሊሄድም ይችላል፡፡ራስ ምታት የሚወጋ፣ የሚጠዘጥዝ ወይም የሚከብድ አይነት አሉት፡፡ ይህም ለሰዓታት ወይም ለቀናት አልፎም እድሜ ልክ ሊቀጥል ይችላል፡፡ ✍️ ራስ ምታት በምን ምክንያት ይመጣል? ➥ ያላችሁ ምልክቶች የራስ ምታቱን ምክንያት ለማወቅ ይረዳል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ግን አስጊ አይሆንም አንዳንዴ ግን በጣም ከባድ የሆኑ ምክንያቶች ይኖሩታል፡፡ የመጀሪያው የራስ ቅል ችግር ጋር የተያያዘ ሲሆን ሁለተኛው አይነት ደግሞ ከሌሎች በሽታዎች ምልክት ሆኖ ይከሰታል፡፡ ✍️ ሃኪሞትን መቼ ማማከር አለባችሁ? ➥ ራስ ምታት ለህይወት አስጊ የሆኑ ሁኔታዎች ምልክት ሊሆን ስለሚችል ቸል ሊባል አይገባም፡፡ ከራስ ምታት ጋር፦ 📌 ትኩሳት (37.5 በላይ ከሆነ) 📌 ህመም ማስታገሻ ብትወስዱም ካልተሻላችሁ ወይም ከባሰ 📌 የሰውነት አለመታዘዝ እና መደንዘዝ 📌 የአንገት ህመም 📌 ለማየት፣ ለመናገር መቸገር 📌 ለመራመድ መቸገር 📌 ማቅለሽለሽ ወይም ማስመለስ 📌 ከበፊቱ የበዛ ወይም የጠነከረ ከሆነ 📌 ራስን መሳት ተያይዞ ከገጠማችሁ ህክምና ማድረግ አለባችሁ። ✍️ ራስ ሜታትን እንዴት መከላከል እንችላለን? 📌 በቂ እንቅልፍ ማግኘት 📌 ጤናማ አመጋገብ መከተል 📌 በቂ እና እለታዊ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ 📌 ጭንቀትን መቀነስ 📌 የሚመች ትራስ መምረጥ 📌 ፈሳሽ ነገሮችን አብዝቶ መውሰድ 📌 የአልኮል መጠጥ ማስወገድ 📌 ጥሩ እንቅልፍ ማግኘት 📌 ካፊን ያላቸውን መጠጦች ማስወገድ 📌 የዮጋ ስፖርት መስራት ራስ ምታትን ለመከላከል ይረዳል። እንኳን ወደ ቻናሌ በሰላም መጣችሁ ዶክተር ዮሀንስ እባላለሁ ሰብስክራይብ በማድረግ ጠቃሚ የጤና መረጃን ያግኙ! ሌሎች የሶሻል ማድያ ገፆቼን ከታች ተጭነው ይከታተሉ! ✅ ዶ/ር ዮሀንስ/Dr. Yohanes 👉 ለተጨማሪ የጤና መረጃ የቴሌግራም ቻናሌን ይቀላቀሉ! https://t.me/HealtheducationDoctoryoh... 👉 የፌስቡክ ገፄን ይቀላቀሉ / doctoryohanes