Русские видео

Сейчас в тренде

Иностранные видео


Скачать с ютуб የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኮሪደር ልማትን በተመለከተ ለተነሱ ጥያቄዎች የሰጡት ምላሽ | Ethiopia | corridor development в хорошем качестве

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኮሪደር ልማትን በተመለከተ ለተነሱ ጥያቄዎች የሰጡት ምላሽ | Ethiopia | corridor development 4 месяца назад


Если кнопки скачивания не загрузились НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru



የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኮሪደር ልማትን በተመለከተ ለተነሱ ጥያቄዎች የሰጡት ምላሽ | Ethiopia | corridor development

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በ1997 ዓ.ም ተመዝግበው ሲቆጥቡ ለቆዩ ነዋሪዎች የኮንዶሚኒየም ቤቶች በእጣ መከፋፈላቸውን ገለጹ። በአሁኑ ሰዓት “97 የሚባል [ኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢ] የለም” ሲሉም ተናግረዋል። ከንቲባዋ ይህንን የተናገሩት በከተማይቱ እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማትን አስመልክቶ ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ ጥቅምት 9፣ 2017 ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ ከከተማይቱ ነዋሪዎች፣ ከልማት ተነሺ ተወካዮች፣ ከታዋቂ ሰዎች እና ከሃይማኖት አባቶች ጋር በተደረገው ውይይት ላይ ነው። የውይይት መድረኩን ከከተማይቱ ከንቲባ በተጨማሪ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ እና የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ መርተውታል። በዚህ ውይይት ለከተማይቱ ኃላፊዎች ከተሳታፊዎች ከቀረቡላቸው ጥያቄዎች መካከል፤ በኮሪደር ልማቱ ምክንያት “ሰዎች በድንገት እየሞቱ ነው” የሚለው ይገኝበታል። ለጥያቄው ምላሽ የሰጡት ከንቲባዋ በልማቱ ምክንያት የሞቱ ሰዎች አሉ ተብሎ የሚቀርበው መረጃ “ውሸት ነው” ሲሉ አጣጥለዋል። በኮሪደር ልማቱ ምክንያት ሞቱ በተባሉ ሰዎች ላይ በተደረገው ማጣራት ግለሰቦቹ ሞተው የተገኙት የኮሪደር ልማቱ በማይለማባቸው አከባቢዎች ላይ እንደሆነ “ማረጋገጥ” መቻሉን ገልጸዋል። በቅዳሜው ውይይት፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሪደር ልማቱን የሚገነቡ ኮንትራክተሮችን ሲመርጥ “በጨረታ አይደለም የሚመርጠው። ለፈለገው ነው የሚሰጠው” የሚል ቅሬታ መኖሩም ተነስቷል። ከንቲባ አዳነች የኮሪደር ልማቱን እንዲያለሙ በዋናነት ኮንትራት እየተሰጠ ያለው “ለአዳዲስ ማህበራት” መሆኑን ተናግረዋል። በማልማት ሂደቱ የሚያጋጥሙ ውስብስብ ስራዎችን ለማሰራት “በልዩ የግዢ ስርዓት” እንዲያልፉ ተደርገው ስራዎችን የሚሰሩ የተመረጡ ኮንትራክተሮች መኖራቸውንም ገልጸዋል። የከተማ አስተዳደሩ በቅርቡ ያጸደቀው በመንገድ ዳር የሚገነቡ ህንጻዎች ከመንገድ ምን ያህል መራቅ እንዳለባቸው የሚያዘው የ“ሴት ባክ” ርቀት “ወጥ በሆነ መንገድ ለምን አይተገበርም?” የሚል ጥያቄም ቀርቧል። ከንቲባዋም በምላሻቸው ህጉ በዋንኛነት አዲስ በሚገነቡ ህንጻዎች ላይ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ ምላሽ ሰጥተዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር) ------------------------------------------------------------------------------------------------------------------- የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ትኩስ ዜናዎችን እና ወቅታዊ ዘገባዎችን ለመከታተል፦ ድረ ገጽ ፦ http://ethiopiainsider.com​ ፌስቡክ ፦   / ethiopiainsider   ትዊተር (ኤክስ) ፦   / ethiopiainsider   ቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopiaInsiderNews ቲክቶክ፦   / ethiopiainsider  

Comments