У нас вы можете посмотреть бесплатно ethiopia🌸ግራዋ ጥቅም🍂የግራዋ ቅጠል ጥቅም🍂benefits of bitter leaf или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
#ግራዋ ጥቅም#ethiopia#የግራዋ ጥቅም#የግራዋ ቅጠል ጥቅም የግራዋ አስደናቂ የጤና ጥቅሞች /incredible healt benefit of bitter leaf (vernonia amygdalina) ethiopia በተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት እንደጎመን ከሾርባ ጋር ተሰርቶ ወይም ከገንፎ፣ ከሾርባ ከገንፎና እንደወጥ ተሰርቶ ይበላል / @lavender1626 የግራዋ ቅጠል ግንዱና አበባው መድሃኒት ናቸው. የግራዋ ቅጠል በቫይታሚን ኤ ሲ ኢ ቢ1 እና ቢ2 ካልሲየም ዚንክ ብረት ፕሮቲንና ሚነራሎች ኮፐር አሰር ማንጋኒዝ ፖታሲየም ፎስፈረስ ሴሌኒየም የበለፀገ ነው. #የግራዋ ቅጠል ጥቅም ፀረ ባክቴርያ የግራዋ ጭማቂ ለብዙ በባክቴርያ ምክንያት ለሚከሰቱ ኢንፌክሽኖችና በሽታዎች በጣም መፍትሄ ይሰጣል ለምሳሌ እንደ የሳንባ ምችና የጥርስ መበላሸት የሆድ ድርቀትንም ያስታግሳል ለቆዳ ኢንፌክሽኖች ለምሳሌ ሽፍታ፣ ጭርት፣ችፌን ያጠፋል ቆዳ ያለሰልሳል የፊት ማስክ ማድረግ ወይም በውሃው በመታጠብ ይቻላል #የግራዋ ጥቅም ፀረ ካንሰር ካንሰር አንዳንድ ህዋሶች በሰውነት ውስጥ ያልተለመደ እድገትና መባዛት ሲከሰት የሚፈጠር በሽታ ነው የካንሰር ህዋሶች በፍጥነት ያድጉና ወደሌሎቹ ጤናማ የሰውነት ክፍሎች ይዛመታሉ. ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የግራዋ ጭማቂ ያልተለመደ የህዋሶች እድገትን ያዘገያል ወይም ይገታል በዚህም ካንሰር እንዳይከሰት ይረዳል. የጨጓራ የአንጀትና የፕሮስቴት የግራዋ ጁስ ለማዘጋጀት እድገቱን የጨረሰ የግራዋ ቅጠል ደጋግሞ ማጠብና መፍጫ ውስጥ ጨምሮ ከትንሽ ውሃ ጋር መፍጨት ከዛም አጥልሎ መጠጣት (ስኳር ወይም ማር መጨመር) ይቻላል. ትኩሳትን ለማስታገስ (ፀረ ወባ ግራዋ በውስጡ ኩዊኒን የተባለ ንጥረነገርን በመያዙ የተነሳ በወባ ምክንያት የሚከሰተውን ከፍተኛ ትኩሳት ያስታግሳል. ኤክስፐርቶች እንደሚመክሩት አዘውትሮ ግራዋን በመጠቀም የወባ በሽታ ከመከሰቱ በፊት በመውሰድ ችግሩን መከላከል ይቻላል ነገር ግን በሽታው ከተከሰተ በኃላ መውሰዱ በሽታውን አያድነውም. ወባ የያዘው ሰው ግን በሃኪም የታዘዘለትን መድሃኒት መውሰድ አለበት የአንጀት ኢንፌክሽንን ለማዳን የአንጀት ኢንፌክሽን በፓራሳይት ምክንያት የሚከሰት ሲሆን የሆድ ህመም ማቅለሽለሽና ማስመለስ፣ ከባድና ደምና ዝልግልግ ፈሳሽ የያዘ ተቅማጥ የሚያስከትል. አንጀትን ብሎም ጉበትንም በጣም የሚያጠቃ ሞትም ሊያስከትል የሚችል በሽታ ነው የሚተላለፈው በዚህ ፓራሳይት የተበከለ ምግብ ወይም ውሃና በመሳሰሉት ነው. ፀረኦክሲዳንት ግራዋ በውስጡ በያዛቸው ፍላቮኖይዶች ምክንያት ፀረኦክሲዳንትና መርዛማን የማፅዳት ችሎታ አለው. ተፈጥሯዊ ፀረኦክሲዳንት ባህሪው ከቫይታሚን ሲ ጋር ተመሳሳይነት አለው. የግራዋ ቅጠል በደም ውስጥ የሚገኘውን የስኳር መጠን በማመጣጠን የስኳር በሽታ እንዳይዘን ይረዳናል የስኳር በሽታ ክትትል ካልተደረገበት ኩላሊትንና ሌሎች የሰውነት አካላትን ያበላሻል የስኳር ህመምተኞች ግራዋን አዘውትረው ቢጠቀሙት ጥሩ ለውጥ ያገኙበታል ከሰውና ከከብቶች ጥገኛ ትሎችን በተሳካ ሁኔታ ለማስወገድ. ኮሶ የመንጠቆ ትል ወስፋት የመሳሰሉት የአንጀት ትሎችን ያጠፋል እነዚህ ፓራሳይቶች አንጀት፣ ሳንባ፣ ጉበት፣ ፊኛና አንጎል ውስጥ በብዛት ተሰራጭተው ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳሉ የግራዋ ጭማቂ ጥገኛ ተውሳኮችን ሽባና መመገብ እንዳይችሉ አድርጎ ይገድላቸዋል. አንዳንድ የግራዋ ዝርያዎች ከሌሎቹ የበለጠ ይመርራሉ ምሬቱን ለመቀነስ ቅጠሉን ደጋግሞ ማጠብ ካስፈለገም በውሃና በጨው ዘፍዝፎ ማጠብ ይቻላል አለዚያም ቅጠሎቹን ከማጠባችን በፊት ትንሽ መቀቀልና ከዛ ማጠብ ወይም አጥቦ በደንብ መጭመቅ የግራዋ ጁስ ጉበት ኩላሊት ሳንባንና አጠቃላይ የውስጥ አካላትን ያፀዳል በዚህም የኩላሊት ጠጠር እንዳይፈጠር ያግዛል #የግራዋ ቅጠል ጁስ ደም ግፊትን ለመቀነስ ይረዳል. ግራዋ ከፍተኛ የፖታሲየም ይዘት ስላለው በደም ውስጥ ተከማችቶ የሚገኘውን የጨው መጠን እንዲወገድ በማድረግ ከፍተኛ የደም ግፊትን ለመቀነስ ይረዳል የእንቅልፍ ችግር ያለባቸው ሰዎች የግራዋ ጁስን ቢጠጡ ሰውነታቸው ዘና እንዲል በማድረግ ጥሩ እንቅልፍ እንዲተኙ ይረዳቸዋል. እንዲሁም ለጨጓራ ህመምን ቀነስ እንዲል ያደርጋል፣ ለወር አበባ ህመምን ለማስታገስ. የግራዋ ቅጠል ጁስ ለአለመውለድ ችግር መፍትሄ ይሰጣል. መውለድ የሚፈልጉ ሴቶች ነገር ግን ቶሎ ማርገዝ ያልቻሉ ቢወስዱት የማርገዝ እድላቸውን ከፍ ያደርገዋል ለሚያሳክክ የግራዋ ቅጠልና ዝንጅብል ፈጭቶ በቀን ከ2-3 ጊዜ መጠጣት ጥሩ ውጤት ያስገኛል It decreases negative effects of medicine. pills and antibiotics) ጉበትን ይጎዳሉ ነገርግን ግራዋ ይሄን ጉዳት ይከላከላል አዘውትሮ ግራዋን በሾርባ መልክ መውሰድ በእርግዝና ጊዜ ለፅንሱ ጥሩ እድገት ጥንካሬና ለማህፀን ጡንቻዎች መጠንከርና ህመም፣ መድማትና ውርጃ እንዳይከሰት ይረዳል. ለተቅማጥ ለጨጓራ መቆጣትና ለመሳሰሉት ችግሮች በቀን 2 ብርጭቆ የግራዋ ጁስ መጠጣት ችግሩን ያስወግደዋል. 4. የግራዋ ጥቅም ለጥርስና ለአጥንት Vitamin C እና ኬ ስላለው ለጤናማ አጥንትና ጥርስ ይረዳል ከአጥንት መሳሳትም ይከላከላል. 11. የግራዋ ጥቅም ክብደት ለመቀነስ የግራዋ ቅጠልን በምግብ ውስጥ አካትቶ አዘውትሮ መመገብ ወይም ጁሱን መጠጣት ክብደት ለመቀነስ ይረዳል ምክንያቱም በዛ ያለ የአሰር ይዘት ስላለው ኮሌስትሮልንም ይቀንሳል ክብደት ለመቀነስ አንዱ አማራጭ ነው ግራዋ የቆዳ ቁስለትንና ኢንፌክሽንን የአፍ እብጠትን የጥርስ ህመምን ታይፎይድን ቲቢንና ሌሎች የመተንፈሻ አካላት ህመምን ለማከም ይጠቅማል Safety እድገቱን የጨረሰ የግራዋ ቅጠል በጥሬው ተዘጋጅቶም ሆነ ተቀቅሎ ሰው ቢመገበው ጉዳት አያስከትልም. ነገር ግን ለጋ የግራዋ ቅጠሎች በከፍተኛ መጠን ሳያናይድና ሌሎች ንጥረ ነገሮች በሰውነት በተገቢው ሁኔታ ተመጥጠው ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ያግዳል. ስለዚህ ይህን ለመከላከል ለጋ ቅጠሎች በደንብ ታጥበው ከተጨመቁ በኃላ በጥንቃቄ መብሰል ይኖርባቸዋል. የበለጠ ጥሩ የሚሆነው እድገቱን የጨረሰውን ቅጠል ብቻ መጠቀም ይመከራል. የግራዋን ቅጠል ፍሪጅ ውስጥ ማስቀመጥ ወይም አድርቀን ማስቀመጥና መጠቀም ይቻላል ግን ጥቅሙን በተወሰነ መጠን ያጣል. ህፃናትና የግራዋ አለርጂ ያለባቸው እና የኩላሊት ህመምተኞች እንዲጠቀሙት አይመከርም