У нас вы можете посмотреть бесплатно የብርቱኳን በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች | Health benefits of Orange или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
የብርቱካንን በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች በብርቱካን ውስጥ ያሉት ንጥረ ነገሮች የተለያዩ የጤና ጥቅሞችን ይሰጣሉ። ●ለካንሰር ህመም ተጋላጭነትን ይቀንሳል ብርቱካን የቫይታሚን ሲ አንቲኦክሲዳንት ምንጭ ስለሆነ ካንሰርን የሚያስከትሉ ነፃ ራዲካሎች መፈጠርን ለመቋቋም ይረዳል። ● የደም ግፊትን ለመቀነስ ይረዳል ብርቱካን ምንም ሶዲየም የለውም። ይህም አንድን ሰው ከዕለታዊ የሶዲየም ገደቡ በታች ለማድረግ ይረዳል። በሌላ በኩል፣ አንድ ኩባያ የብርቱካን ጭማቂ በየቀኑ የፖታስየም የማግኘት ይዘትን በ14 በመቶ ይጨምራል። የሶዲየም አወሳሰድን መገደብ የደም ግፊትን ለመቀነስ አስፈላጊ ነው። በአንፃሩ ደግሞ የፖታስየምን መጠን መጨመር የአንድን ሰው ለከፍተኛ የደም ግፊት ስጋት ለመቀነስ ይረዳል። ምክንያቱም ፖታሲየም የደም ሥሮች እንዲከፈቱ ይረዳል። ከዚህም ሌላ ለስትሮክ ተጋላጭነትን ይቀንሳል። ●የልብ ጤንነትን ለማሻሻል ይረዳል የልብ ሕመም በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ በጣም የተለመደው ያለጊዜው ሞት መንስኤ ነው። ብርቱካን ጥሩ የፋይበር እና የፖታስየም ምንጭ ሲሆን ሁለቱም ለልብ ጤንነት አስፈላጊ ናቸው ። በቂ ፋይበር መመገብ የልብ በሽታን የመጋለጥ እና ገዳይ የመሆን እድልን በእጅጉ ይቀንሳል። ይህም በደም ውስጥ ያለውን የኮሌስትሮል መጠን የመቀነስ ችሎታ ይኖረዋል። በተጨማሪም ብርቱካን እና ብርቱካን ጭማቂ አዘውትሮ መውሰድ የልብ ሕመምን የሚያጋልጡ ሁኔታዎችን ለመቀነስ ይረዳል። ● ለስኳር በሽታ ተጋላጭ እንዳንሆን ያደርጋል አንድ የብርቱካን ፍሬ እስከ 131 ግራም ይመዝናል። በውስጡም እስከ 3.14 ግ ፋይበር ይይዛል። ይህም በቀን ለ የአንድ ሰው የሚያስፈልገውን 10% ፋይበር ይሆናል። ከመጠን በላይ ውፍረት እና ከመጠን በላይ መወፈር type 2 የስኳር በሽታ እድገት አስተዋጽኦ ስለሚያደርጉ ክብደትን መቆጣጠር የስኳር በሽታ ተጋላጭነትን ለመቀነስ አስፈላጊ ነው። ሰውነቱ ፋይበርን ከሌሎች ንጥረ ነገሮች በበለጠ በዝግታ processed ያደርገዋል። ከፍተኛ መጠን ያለው አትክልትና ፍራፍሬ የያዘ አመጋገብን መከተል የደም ስኳር መቆጣጠርን ሊረዳ እና ለtype 2 የስኳር በሽታ ተጋላጭነትን ይቀንሳል። ● ለቆዳ ጤንነት እና ውበት በቂ የሆነ ቫይታሚን ሲ መጠቀም የቆዳ ጤንነትን እና ገጽታውን ውብ እንዲሆን ያደርጋል። ቫይታሚን ሲ ኮላጅን እንዲመረት አስተዋጽኦ ያደርጋል። ኮላጅን ቆዳ እንዲጠነክር በቆዳችን ላይ ለሚፈጠረው ቁስል እንዲፈወስ እና እንዲድን፣ እና ለቆዳችን ድጋፍ በመሆን ያገለግላል። ባጠቃላይ ቫይታሚን ሲ ቆዳ ጤናማ እንዲሆን ፣ ውብ እንዲሆን ፣ እንዳይጨማደድ ፣ እንዲሁም ሻካራ እንዳይሆን እናም የመለጠጥ ባህሪ እንዲኖረው የሚያደርግ አስፈላጊ ንጥረ ነገር ነው። ለቫይታሚን ሲ ደግሞ ትልቁ መገኛው ብርቱኳን ነው። ●የደም ማነስ ለመከላከል በቫይታሚን ሲ የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ የደም ማነስን ለመከላከል ይረዳል። የደም ማነስ ማለት ለሰውነታችን አስፈላጊ የሆነው ንጥረነገር ማለትም አይረን ሲያስ የሚከሰት በሽታ ነው። ምንም እንኳን ብርቱካን ጥሩ የአይረን ምንጭ ባይሆንም እጅግ በጣም ጥሩ የቫይታሚን ሲ ምንጭ ነው፣ይህም ሰውነትታችን አይረን የመሳብ ችሎታውን ይጨምራል ። ● የበሽታ የመከላከል አቅምን ይጨምራል በቪታሚኖች፣ ማዕድናት እና አንቲኦክሲደንትድ ውህዶች የበለፀጉ ፍራፍሬዎችን አዘውትሮ መመገብ በሽታ የመከላከል አቅምን ለማዳበር ይረዳል። ብርቱካን እና ሌሎች የሎሚ ፍራፍሬዎች በጣም ጥሩ የቫይታሚን ሲ ምንጮች ናቸው። ይህ ንጥረ ነገር እንደ ተፈጥሯዊ የበሽታ ተከላካይ ሕዋሳት ተግባር ወሳኝ ነው። እንዲሁም ያረጁ፣ ወይም የሞቱ ህዋሶችን በአዲስ ሴሎች ለመተካት ይረዳል። ከዚህም በተጨማሪ ብርቱካን ኮሊን ይይዛል። ኮሊን ለእንቅልፍ፣ ለጡንቻ እንቅስቃሴ፣ ለመማር እና ለማስታወስ የሚረዳ ጠቃሚ የብርቱካን ንጥረ ነገር ነው። በተጨማሪም ኮሊን የነርቭ መልዕክቶችን ለማስተላለፍ ይረዳል። ከዚህም በተጨማሪ ስብን ለመምጠጥ ይረዳል እና የእብጠትን በሽታን ይቀንሳል። #orange #ጤና #ኢትዮጵያ