У нас вы можете посмотреть бесплатно በ50 ሺብር ደረቅ ሳሙና ማምረትና መሸጥ፣ የደረቅ የልብስ ሳሙና አሰራር ሂደቶች " или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
በቀላሉ በቤት ውስጥ ደረቅ የልብስ ሳሙና አመራረት ሂደቶች፣ደረቅ የልብስ ሳሙና አመራረት ስልጠና፣በትንሽ ገንዘብ ካፒታል ደረቅ የልብስ ሳሙና በቤት ውስጥ አምርቶ መሸጥ፣በቤት ውስጥ ደረቅ የልብስ ሳሙና አመራረት ቴክኒኮች፣የሳሙና ሳፕ እሴት ወይም ሳፕ ቫልዩ አሰራር፣የሳሙና ኬሚስትሪ፣የሳሙና ሳፖኒፊኬሽን ሂደቶች በዝርዝር፣Home made bar soap production process in easy ways,bar or laundery soap production tranning,home made small bussiness bar soap production and saling,home made bar soap production process in details,saponefication value or sap value calculation,soap chemistry,saponefication process #የደደረቅ ሳመና አዘገጃጃት(Recipe) የተጠቀምከኩት"የሳሙና ግብአቶች መጠን አሰላል እነሆ:- ሀ/የሳሙና ኬሚስትሪና የሳሙና መስሪያ ግብእአቶችን ስሌት መሰረታዊ የኪሚስትሪ ሳይንሳዊ ቀመር በመጠቀም Triglyceride (Fat/Oil) + Sodium Hydroxide (Lye) → Soap (Fatty Acid Salt) + Glycerol 1ኛ/አጠቃላይ የሚያስፈልገንን ዘይት መጠን መወሰን በመጀመርያ የኬሚስትሪ ቀመርን ተጠቅመን 10 ፍሬ ሳሙና እያንዳንዳቸዉ 250 ግራም የሚመዝን ባጠቃላይ 2500 ግራም የሳሙና ግብአቶችን ለክተን እናዘጋጃልን ፡፡ አንድ ሳሙና ከሞላ ጎደል ሙሉ በሙሉ ከዘይት የተሰራ ስለሆነ፣ የምንፈልገው አጠቃላይ የሳሙና ክብደት (2500 ግራም) የሚያክል ዘይት ያስፈልገናል። አጠቃላይ የዘይት መጠን: 2500 ግራም 2ኛ/ የዘይቶቹን አይነት እና በምን ያህል መጠን እንደምንጠቀም አሁን እኔ ምሰራላችሁ ሳሙና በፋብሪካ ስታንዳርድ ብዙ ሳሙና አምራቾች የሚጠቀሙበት ፎርሙላ በመጠቀም የኮኮናት ዘይት: 40% ማለትም ጥሩ አረፋ እና የማፅዳት አቅም እንዲኖረዉ ፣የፓልም ዘይት 30% ማለትም ጥሩ ሳሙናው ጠንካራ እንዲሆን የሱፍ አበባ ዘይት: 30% ይሀም ለስላሳ እንዲሆን እና እርጥበት እንዲሰጥ ያደርግልናል፡፡ በዚህም መሰረት በግራም የኮኮናት ዘይት: 2500 ግራም (አጠቃላይ ዘይት) x 0.40 (40%) = 1000 ግራም የፓልም ዘይት: 2500 ግራም (አጠቃላይ ዘይት) x 0.30 (30%) = 750 ግራም የሱፍ አበባ ዘይት: 2500 ግራም (አጠቃላይ ዘይት) x 0.30 (30%) = 750 ግራም ጠቅላላ ዘይት: 1000 + 750 + 750 = 2500 ግራም (ይህ ትክክል መሆኑን ያረጋግጥልናል)፡ 3ኛ/ለእንዳንዱ ዘይት አየነት የሚስፈልገንን የዘይት መጠን እና የሶዲየም ሃይድሮክሳይድ (NaOH) መጠን ማስላት ይህንን የምናውቀው እያንዳንዱ የዘይት አይነት የራሱ የሆነ "SAP value" ወይም (Saponification Value) በመጠቀም ነዉ፡፡በየተለያዩ ዘይቶች የተለያዩ ባህሪያት ስላሏቸው (አረፋ፣ ጥንካሬ፣ ማለስለስ)፣ በአንድነት መጠቀም የተሻለ ነው። SAP value: ማለት 1 ግራም ዘይትን ሙሉ በሙሉ ወደ ሳሙና ለመቀየር ስንት ግራም NaOH እንደሚያስፈልግ የሚያሳይ ቁጥር ነው። ከዚህም በተጨማሪ የምንሰራዉ ሳሙና አልካላይን ቤዙ በዝቶ ልብስ ሲናጥብ ቆዳችን እንዳይደርቅ ከምናሰላዉ የቤዝ አልካሊን ዉሀድ 5% "superfat" እንቀንስለታለን፡፡ በዚህም መሰረት የሚፈለገው የሶዲየም ሃይድሮክሳይድ (NaOH) መጠን ከላይ ባገኘነዉ የዘይት መጠን ስናሰላዉ ሀ/ለእንዳንዱ ዘይት አየነት የሚስፈልገንን የዘይት መጠን የኮኮናት ዘይት SAP value: 0.190 (በአማካይ) • የሚፈለገው NaOH ለኮኮናት ዘይት: 1000 ግራም x 0.190 = 190 ግራም የፓልም ዘይት SAP value: 0.141 (በአማካይ) • የሚፈለገው NaOH ለፓልም ዘይት: 750 ግራም x 0.141 = 105.75 ግራም ሲጠጋጋ 105.8 ግራም ይሆናል፡፡ የሱፍ አበባ ዘይት SAP value: 0.134 (በአማካይ) የሚፈለገው NaOH ለሱፍ አበባ ዘይት: 750 ግራም x 0.134 = 100.5 ግራም ይሆናል፡፡ ለ /የሶዲየም ሃይድሮክሳይድ (NaOH) መጠን ስለዚህ ከላይ እንዳየነው አጠቃላይ የ NaOH መጠን (ያለ superfat): 190 + 105.8 + 100.5 = 396.5 ግራም ይሆናል፡ የ5% Superfat ስንቀንሰዉ ማለትም ቤዙ በዝቶ ልብስ ሲናጥብ ቆዳችን እንዳይደርቅ 396.25 ግራም x 0.05 (ለ 5%) = 19.81 ግራም ይሆናል፡፡ ስለዚህ ከአጠቃላይ NaOH ላይ 19.81 ግራም እንቀንሳለን። የመጨረሻ የ NaOH መጠን: 396.3 - 19.81 = 376.44 ግራም ወደ 376.5 ግራም እናጠጋጋዋለን፡፡ 4/የሚፈለገው የውሃ መጠን ማሰላት ለሳሙና አሰራር የውሃ መጠን ብዙውን ጊዜ ከጠቅላላው የዘይት ክብደት 33% ያህል ይመከራል። በዚህም መሰረት10 ፍሬ ሳሙና እያንዳንዳቸዉ 250 ግራም የሚመዝን ባጠቃላይ 2500 ግራም የሚመዝን ሳሙና ለመስራት የሚያስፈልገን የውሃ መጠን: 2500 ግራም (አጠቃላይ ዘይት) x 0.33 = 825 ሚሊ ሊትር ያስፈልገናል፡፡ 5/ሌሎች ተጨማሪ ግብአቶች ማስላት 1ኛ.ግሊሰሪን (Glycerin): ለቆዳ እርጥበት 25-50 ሚሊ ሊትር ወይም ከአጠቃላይ የዘይት መጠን 1-2% መጠቀም ይቻላል፡፡በአማከይ 1.5 መጠቀም እችላለሁ፡፡ በዚሀም መሰረት በአማካይ 35 ሚሊ ሊትር እንጨምራለን፡፡ 2ኛ.የሽቶ ዘይት ለጥሩ ማዛና ለጥሩ ሽታ የላቬንደር ወይም የሎሚ ሽቶ ዘይት 25-50 ሚሊ ሊትር ወይም ከአጠቃላይ የዘይት መጠን 1-2% እንጨምራለን፡፡በአማከይ 1.5 መጠቀም እችላለሁ፡፡ በዚሀም መሰረት በአማካይ 35 ሚሊ ሊትር እንጨምራለን፡፡ 3ኛ.የልብስ ማቅለሚያ (Dye): ሳይበዛ ሳያንስ ሳሙናዉ እንዲያምር ለውበት የምንፈልገዉን ቀለም አይነት እንደ ምርጫችን ጥቂት ጠብታዎች እንጨምራለን፡፡ 4ኛ.ቤኪንግ ሶዳ (Baking Soda): ለማፅዳት አቅም እንዲጨምር ከ50-75 ግራም ወይም ከ2-3 የሾርባ ማንኪያ እንጨምራለን፡፡ በዚሀም መሰረት በአማካይ 2 የሾርባ ማንኪያ እንጨምራለን፡፡ አጠቃላይ ለ10 ፍሬ እያንዳንዳቸው 250 ግራም የሚመዝን የልብስ ሳሙና ባጠቅላይ 2.5 ኪሎ ግራም ሳሙና ለማምረት የሚያስፈልጉ ግብአቶች ሶዲየም ሃይድሮክሳይድ (Sodium Hydroxide - NaOH): 376.5 ግራም የተጣራ ውሃ (Distilled Water): 825 ሚሊ ሊትር የኮኮናት ዘይት (Coconut Oil): 190 ግራም የፓልም ዘይት (Palm Oil): 105.8 ግራም የሱፍ አበባ ዘይት (Sunflower Oil): 100.5 ግራም ግሊሰሪን (Glycerin): 35 ሚሊ ሊትር ሽቶ ዘይት ወይም የላቬንደር ወይም የሎሚ ሽቶ ዘይት: 35 ሚሊ ሊትር .የልብስ ማቅለሚያ (Dye): ጥቂት ጠብታዎች ቤኪንግ ሶዳ (Baking Soda): 2 የሾርባ ማንኪያ ዉድ የዚሀ ቻናለ ቤተሰቦች በዚሀ መሰረት ደረቅ የልብስ ሳሙና ቤታችሁ አምርታችሁ መጠቀም ትችላላችሁ፡፡