У нас вы можете посмотреть бесплатно ጋብቻ በግል ንብረት ላይ የሚያስከትለው ውጤት или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
#ጋብቻ በንብረት በኩል ምን ዓይነት ውጤት አለው? ============= ጋብቻ በ #ባልና #ሚስት መካከል ራሱን የቻለ ግንኙነት የሚፈጥር ከመሆኑ አንፃር በመካከላቸው ያለውን ግላዊ ግንኙነትም ሆነ በንብረት ረገድ የሚኖራቸውን ግንኙነት በጋብቻ ውል መስማማት የሚችሉ ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ ይደነግጋል(አንቀፅ 42)፡፡ የጋብቻ ውል ማለት ባልና ሚስት ጋብቻቸው ንብረታቸውን በተመለከተ ስለሚያስትለው ውጤት እንዲሁም ግላዊ ግንኙነታቸውን በተመለከተ ስለሚኖራቸው መብቶችና ግዴታዎች ጋብቻቸውን ከመፈፀማቸው በፊት ወይም እጅግ ቢዘገይ ጋብቻቸውን በሚፈፅሙበት ዕለት የሚያደርጉት ስምምነት ነው፡፡ ይሁንና ባልና ሚሰት ይህንን ግንኙነታቸውን ለመወሰን ያደረጉት ውል የሌለ እንደሆነ ይህ አይነቱ ግንኙነት በህጉ በተቀመጡ ድንጋጌዎች የሚገዛ ይሆናል፡፡ በጋብቻ ውስጥ ያለ #ንብረት የግል ሀብት አሊያም የጋራ ሀብት ሊሆን ይችላል፡፡ በመርህ ደረጃ አንደኛው ተጋቢ የግል ሀብቱ መሆኑን ካላስረዳ በስተቀር ንብረቱ በባል ወይም በሚስት ስም ብቻ የተመዘገበ ቢሆንም እንኳን ንብረቱ የጋራ ሀብት እንደሆነ ህጉ ግምት /#Legal Presumption/ ይወስዳል፡፡ (አንቀፅ 63(1))፡፡ ምንም እንኳን የህጉ ግምት በትዳር ውስጥ ያለ ማንኛውም ንብረት የጋራ ንብረት ነው የሚል ቢሆንም ተገቢዎች ንብረቱ የግላቸው መሆኑን ማስረዳት እሰከቻሉ ጊዜ ድረስ ጋብቻው ፀንቶ ባለበት ሁኔታም ባልና ሚስት የየራሳቸው የግል ንብረት ሊኖራቸው የሚችል ስለመሆኑ ከህጉ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ጋብቻ ከመመስረቱ አስቀድሞ ተጋቢዎች በየግላቸው የነበራቸው ንብረት እንደ ጋራ ንብረት ይቆጠራል ወይስ አይቆጠርም የሚል ጥያቄ ብዙ ጊዜ ይስተዋላል፡፡ባልና ሚሰት ከጋብቻ በፊት የነበራቸውን የግል ንብረት የጋራ ሀብት እንዲሆን መደንገጉ ምን አይነት አንድምታ ሊኖረው እንደሚችል ከግምት ውስጥ በማስገባት የኢፌድሪ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ ሀተታ ዘ-ምክንያት እንዲህ ይገልፀዋል… “ተጋቢዎች ከጋብቻ በፊት የነበራቸውን የግል ንብረት የጋራ ሀብት እንዲሆን መደንገጉ ጋብቻን ከንብረት ጋር የማየት ሁኔታና አስተሳሰብ የሚፈጥር ሲሆን በውጤቱም ጋብቻ ሀብት ለመካፈል የመፈፀምበትና የሚፈርስበት ዕድል ይከፍታል፡፡ምንም ያልነበረው ተጋቢ ንብረት ያለውን ሰው ብቻ በማግባት ጋብቻው ሲፈርስ የሚካፈልበትን ሁኔታ በሕጋዊ አስተዳዳር ስር ማስቀመጡ በሕሊናም ሆነ በፍትህ ረገድ ተቀባይነት የሚኖረው አይደለም፡፡” ይህንን ሀሳብ መነሻ በማድረግም የቤተሰብ ህግ በአንቀፅ 57 እና 58 የባልና ሚስት ሀብትን ያለግብይት የተገኙ የግል ንብረቶችና በግብይት የተገኙ የግል ንብረቶች በሚል ከፋፍሎ አስቀምጧል። ከቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 42 እና 58 የጣምራ ንባብ መረዳት እንደሚቻለው ባልና ሚስት በጋብቻ ውላቸው ያደረጉት ሌላ ተቃራኒ ስምምነት ከሌላቸው በስተቀር ከጋብቻ በፊት በየግል የነበራቸው ንብረት እንዲሁም ከጋብቻ በኃላ በውርስ አሊያም በስጦታ በየግል ያገኟቸው ንብረቶች የግላቸው ሆነው የሚቀሩ ናቸው። ይሁን እንጂ ባልና ሚስት ጋብቻ ከመሰረቱ በኋላ አንዱ በግሉ የነበረውን የግል ሀብት ቢለውጥ ወይም ይህንን ንብረት ሸጦ ሌላ ቢገዛ ወይም ይህንን ንብረት ሸጦ ገንዘቡን ቢይዝ የግል ይባልልኝ ብሎ ለፍርድ ቤት ጥያቄ አቅርቦ ካላፀደቀው በቀር ይህ ንብረት የጋራ የሚሆን ስለመሆኑ ህጉ በግልፅ ይደነግጋል። ይህም ማለት ለምሳሌ ጋብቻ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ባል መኪና ቢኖረው እና ይህንን መኪና ትዳር ውስጥ ከገባ በኋላ ቢሸጠው ወይም ከሌላ ሰው ጋር በሌላ ንብረት ቢለዋወጥ አሊያም መኪናውን ሸጦ ገንዘቡን በእጁ ቢይዝ ይህንን መሰረት አድርጎ በግብይት የተገኘው ንብረት የግል ይባልልኝ ብሎ ፍርድቤት ቀርቦ ጥያቄ እስካላቀረበና ፍርድቤቱ እስካላፀደቀው ጊዜ ድረስ ንብረቱ የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ይሆናል(አንቀፅ 58)። በሌላ በኩል በህጉ የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ተደርጎ የሚውሰደው ባልና ሚስት ከግል ጥረታቸው የሚያገኙት እና ከግል እና ከጋራ ንብረት የሚያገኟቸው ንብረቶች ናቸው።ይኸውም ከቅጥር የሚገኝ ደመወዝ፣ከባልና ሚስት የግል ንብረት የሚገኝ ገቢ(ለአብነትም ከላይ በቀረበው ምሳሌ ባል የግል በሆነው መኪና ገቢ የሚያስገኝ ስራ ላይ ቢሰማራ ወይም የግል ቤት ቢኖረው ቤቱን ከማከራየት የሚያገኘው ገቢ)፣ በትዳራቸው ካፈሩት የጋራ ንብረት የሚገኘው ገቢ እንዲሁም ከላይ በተገለፀው አግባብ በግብይት የተገኘው ንብረት የግል ስለመሆኑ ፍርድቤት ካላፀደቀው የባልና ሚስት የጋራ ሀብት ነው(አንቀፅ 62)። --------------------------------------- የገጠማችሁ እና የህግ ምክር የምትፈልጉበት ማንኛውም ጉዳይ ካለ በኮመንት መስጫው ስር የሚገኘውን የመወያያ ግሩፓችንን በመቀላቀል ጥያቄ ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡👇🏽👇🏽 ለበለጠ፡ contact us ☎️0925122319 tiktok.com/@lawyer_kidist_elias telegram @kidistelias