У нас вы можете посмотреть бесплатно #DR или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
የኢትዮጵያ-ፖለቲካ#ኦሮሚያ #ነፃነት #EthiopiaNews#ጃዋር#የኦሮሞትግል #የኢትዮጵያፖለቲካ #ኦሮሚያ #ነፃነት #EthiopiaNewsመንግስት የሚከተለው የኢኮኖሚ ፓሊሲ እያሳደረ ያለው የኑሮ ውድነትና የኢኮኖሚ ተጽእኖ የሁላችንም ደጃፍ እያንኳኳ መሆኑን መረጃ ማቅረብ የማያስፈልግበት ደረጃ ላይ መድረሱ አሌ ሊባል ባይችልም በተቃራኒው መንግስት ከሚከተለው ፓሊሲ በመነጨ ያዋጣኛል የሚለውን የግብርና የአገልግሎት ዋጋ መጨመር የሚከለክለው ሕግ የለም። ነገር ግን የተሸከምነው ጫና ሳያንስን ተጓዳኝ፣ ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ ተዘዋዋሪ ግብርና የአገልግሎት ጭማሪዎችን ከመተግበራቸው በፊት ውሳኔዎቹ በሀቅ ላይ ተመስርተው፣ በመረጃ ተደግፈው በተገቢው መገናኛ ብዙሃን አለመቅረባቸው ለኢኮኖሚያዊ ምስቅል በመዳረግ በኑሯችን ላይ ተጨማሪና ውድ ዋጋ እያስከፈሉን ነው ። መንግስት ከዛሬ ሶስት ወር በፊት ድጎማን አጠናቆ መጨረሱንና ነዳጅ በዓለም አቀፍ ዋጋ እየተሸጠ መሆኑን መግለጫ ሲሰጥ ነበር። ዛሬ ደግሞ ቀጥተኛ ካልሆኑ መገናኛ ብዙሃን እንደ ተከታተልነው ከሆነ ድጎማን ለመጨረሻ ጊዜ ለማቆም በድምሩ 30% የኤክሳይዝና የተእታ ግብር የተጣለ መሆኑን እየሰማን ነው። በተቃራኒው በዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ግምገማ መሰረት የነዳጅ ዋጋ ከኦክቶበር 2025 ጀምሮ የ6% ቅናሽ እንዳሳየን ቅናሹም የሚቀጥል ስለሆነ የአፍሪካ መንግስታት ይህንን አጋጣሚ እንደ እፎይታ ጊዜ በመውሰድ በሕዝባቸው ላይ የተከሰተውን የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነት ለማረምና ጫናውን ለማርገብ እንዲጠቀሙበት መግለጻቸው ይታወሳል። ዛሬ ምን ገጠመኝ። ነዳጅ ስላለቀብኝ ለመግዛት ያደረጉት ተደጋጋሚ ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል። ነዳጅ አልቆና ጠፍቶ ነው እርግጠኛ መሆን አልችልም። የንግድ ስርዓቱ ዛሬ እንደተበጠበጠና እንደተተራመሰ ውሏል። ዋጋ እየጨመረ ነው። ግልጽና አስተማማኝ መረጃ እስከሌለ ድረስ መታመሱና መተራመሱ እንደሚቀጥል በቂ ምልክት እየታየ ነው። መንግስት መረጃ መስጠቱ ግዴታ ቢሆንም መረጃም ሆነ ፍንጭ የለም የነዳጅ ዋጋ አልጨመረም። እንዲያውም በተቃራኒው እየቀነሰ እንደሆነና ቅናሹም እንደሚቀጥል ይጠበቃል። ከሶስት ወራት በፊት ድጎማ ሙሉ ለሙሉ እንደተጠናቀቀና ነዳጅ በዓለም አቀፍ ዋጋ እየተሸጠ እንደሆነ መግለጫ ተሰጥቷል። የ30% የተእታና የኤክሳይዝ ታክሰም ቀጥተኛ ያልሆነ ግብር እንጂ የድጎማ ማረሚያ እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ውሳኔው ተግባራዊ ይሆናል እስከተባለበት "አንድ ወር ደረስ" ከመንግሰት በኩል ሀቀኛና አሳማኝ ዝርዝር መረጃ እስካልቀረበ ድረስ የግብይትና የዋጋ ትርምሱን ተደራራቢ ዋጋ እያስከፈለ ተጠናክሮ መቀጠሉ የተለመደና የሚጠበቅ ነው። ሸማቾች የዋጋ ንረት፣ የብር መግዛት አቅም መውደቅና የአቅርቦት እጥረት የሚያሳድርባቸው የዋለ ያደረ ተጽእኖ ሳያንሳቸው በስጋትና በስሚ ስሚ (Speculation) የማያባራ የዋጋ ንረት መቀጣታቸው ይቀጥላል። በተደጋጋሚ እንደገለጽኩት መንግስት ውሳኔዎቹና ፓሊሲዎቹ በሚያስከትሉት ኢኮኖሚያዊ ለውጦች ላይ እምነት፣ ቁርጠኝነትና እርግጠኝነት ካለው መረጃውን በአግባቡ በሚስጥር አቆይቶ በተገቢው ጊዜና በተገቢው መድረክ በሚተገበሩበት ጊዜ በመልቀቅ ቢያንስ ከግምታዊ ኢኮኖሚያዊ ሁከት (Speculation)፣ አለመረጋጋትና ትርምስ ዜጎችን መታደግ ይገባል። በዚህ ጉዳይ ላይ ምልከታዬን ለመረዳት ጥቅምት 8 ላይ የጻፍኩትን ማብራርያ ማስፈንጠርያውን በመጠቀም ያንብቡ።