У нас вы можете посмотреть бесплатно የቅድም አያቶቹነ ቅርስ ለቢላሉል ሐበሺ ሙዝየም በስጦታ ያበረከተው ወጣት или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
ኑ ወደ ደግነት ! 6833 ላይ ok ብለው ከተመዘገቡ በኋላ ፣መልእክት ሲደርስዎ ብቻ በሚያዋጡት 1 ብር ፣ዘርፈብዙ የበጎሥራ ተግባራትን እያከናወነ የሚገኘውን "ቢላሉል ሐበሺ "ን ይደግፉ። ቢላሉል ሐበሺ ላለፉት 20 ዓመታት ምንጩ ሙሉ ለሙሉ ከኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን ብቻ በሆነ በጀት ዋነኛ ትኩረቱን በትምህርት ፣ ጤና እና ከተረጅነት አላቆ ራስን ማስቻል ላይ በማድረግ ከ9300 በላይ ወላጅ የሌላቸውን ወጣቶች እና ህፃናት ጎዳና እዳይወጡ ከነቤተሰቦቻቸው የኑሮ እና የትምህት ድጋፍ በመስጠት፤ ከ 1100 በላይ አረጋውያን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ፤ ከ 300 በላይ ወጣቶች፣ በተለይ ሴቶችን የስራ ማቋቋሚያ ድጋፍ በመስጠት፤ ከ 3600 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች በራሱ መኪናዎች ነፃ የቀብር አገልግሎት በመስጠት በአዲስ አበባ እና የተለያዩ ክልሎች ኮሮናን ጨምሮ የተፈጥሮ ሰው ሰራሽ ችግር ለደረሰባቸው ወገኖቻችን የእለት ደራሽ እርዳታዎችን በመለገስ፤ ለብዙ ሺ ወገኖቻችን ችግር መቃለል እና ህይወት መስተካከል ምክንያት መሆን ችሏል። ከእነዚህ ቀጥተኛ ድጋፎች በተጨማሪ ቢላሉል ሐበሺ መካኒሳ አካባቢ ባስገነባው ህንፃ ውስጥ ሙዚየም ፣ ቤተ መጽሐፍት ፣ ሁለገብ አዳራሽ፣ የጥናት እና ምርምር ማዕከል አቋቁሞ አገልግሎት በመስጠት ታሪካዊ እና ማኀበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል ። ቢላሉል ሐበሺ በቀጣይም፣ ይህንኑ የበጎ ተግባራት እንቅስቃሴውን አጠናክሮ በመቀጠል ህብረተሰቡን በቀጥታ የሚጠቅሙ የጤና እና የትምህርት ኘሮጀክቶችን ነድፎ ለተግባራዊነታቸው እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ። ፕሮጀክቶቹም 1) የሱስ ማገገሚያ ማዕከል 2) የእናቶችና ህፃናት ክሊኒክ 3) ትምህርት ቤት ሲሆኑ እነዚህን ህብረተሰቡን በቀጥታ ተጠቃሚ የሚያደርጉ እቅዶች በፍጥነት እውን ለማድረግ ይረዳው ዘንድ እርስዎ በሞባይሎ 6833 ላይ ok ብለው ከተመዘገቡ በኋላ ፣ መልእክት ሲደርስዎ ብቻ በሚያዋጡት 1 ብር ፣ላለፉት 20 ዓመታት ዘርፈ ብዙ የበጎ ሥራ ተግባራትን እያከናወነ የሚገኘው የቢላሉል ሐበሺ ቤተሰብ ይሁኑ ። ኑ ወደ ደግነት !