У нас вы можете посмотреть бесплатно አፄ ቴዎድሮስ ዳግማዊ/Emperor Tewodros II የዘመናዊት ኢትዮጵያ መስራች или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
ከኢትዮጵያ ታዋቂ መሪዎች መካከል አንዱና ከዘመናዊት ኢትዮጵያ መስራቾች መካከል አንዱ ናቸው፤ አፄ ቴዎድሮስ ዳግማዊ። በዚህ ቪድዮም የአፄ ቴዎድሮስን ሕይወት ከውልደት እስከ ሞት በአጭሩ እንቃኛለን፤ አብራችሁኝ ቆዩ። አፄ ቴዎድሮስ የተወለዱት ካሳ ኃይሉ በሚባል ስም በቋራ ከአባቱ አቶ ኃይሉ እና ከእናቱ እመት አትጠገብ በ1810 ነበር። አባቱም የሞቱት ገና ልጅ እያለ ስለነበር እናቱ በድህነት ውስጥ ኮሶ በመሸጥ በሚያገኙት ገንዘብ አሳደጉት፤ ኋላ ላይ ግን አጎቱ ደጃች ክንፉ ካሳን ወደ ወደ ማኅበረ ሥላሴ ገዳም ከመነኩሴዎች እግር ሥር ይማር ዘንድ ወሰዱት። በማኅበረ ሥላሴም ካሳ በባህላዊ ትምህርት በሥርዓት ተማረ። መዝሙረ ዳዊትንም ተምሮ ጨረሰ፤ ነገር ግን ንጉስ ለመሆን የተመኘው ደጃች ማሩ ከካሳ ጋር ይማሩ የነበሩትን ተማሪዎች ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ጨፈጨፋቸው። በዚህ ታሪክ ዙርያ የተለያየ ትርክት ቢነገርም ደጃች ማሩ የማኅበረ ሥላሴን ልጆች የጨፈጨፈው በመሳፍንቱ ጭቆና ለደረሰበት ለአባቱ ለመበቀል ሲል ነው። ካሳም ከጭፍጨፋው አምልጦ ወደተወለደበት በመሄድ ሽፍቶችን በመቀላቀል የጦርነት ዘዴዎችን እና ሥልቶችን ተማረ። ተክለ ፃድቅ መኩርይል እንዳለውም ካሳ እንደ አመፀኞች መሪ ተቀባይነት አግኝቶ ነበር፤ ነገር ግን ሽፍታነቱን ትቶ በደጃች ጎሹ እና ራስ አሊ ቤት ተቀመጠ፤ በዛም የንጉሳዊ ሥነ ምግባር፣ ወታደራዊ ውግያ እና የስራ ባህል ተማረ። ወጣቱ ካሳም ከግብፆች ጋር በነበረው የሰናር ጦርነት ጀግንነትና ጀብድን ካሳየ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ታዋቂ ሆነ ክብር ያለውም ልጅ የሚለው ማዕረግ ተሰጠው። የራስ አሊ እናት እቴጌ መነንም ሴት ልጃቸውን ወይዘሮ ተዋበችን ለካሳ ሊድሩለት ወሰነ፤ በ1839ም ልጅ ካሳና ወይዘሮ ተዋበች በቤተ ክርስትያን ተጋቡ። የጋብቻውም አላማ ካሳን ለማጥመድና ካሳ ለእቴጌ መነን እና ለራስ አሊ ታማኝ እንዲሆን ለማድረግ ነበር፤ ነገር ግን ካሳ ከጎንደር አልፎ የመሄድና ሙሉ ኢትዮጵያን አንድ አድርጎ የመግዛት ምኞት ነበረው። በአጠቃላይ ዘመነ መሳፍንትን ማቆምና በአንድ አገዛዝ የምትመራ ዘመናዊ ኢትዮጵያን መመስረት ይፈልግ ነበር። መኳንንቱም ካሳን ባገኙት ቁጥር ከየት እንደተነሳ እያስታወሱ ያናንቁት ነበር፤ በትዳሩ ውስጥም የበታች በመሆኑ ይሳለቁበት ነበር። በዚህም ምክንያት ካሳ በድጋሚ የአመፀኛ ሕይወትን ለመምራት ወሰነ። ሚስቱን ተዋበችም ከዝቅተኛ ቦታ የመጣ ሰው አግብተሻል ብለው ስለሚሳለቁባት እርሷም ባሏን ደግፋ ከእርሱ ጋር አምፃ ሄደች። ራስ አሊም ካሳና ተዋበች እንዳመፁ ሲሰሙ እጅግ ተናደዱ፤ ከመቶ አለቃዎቻቸው መካከል አንዱ የሆነውንም ደጃች ወንድ ይራድን ጠርተው በካሳ ላይ ከፍተኛ የጦር ዘመቻ እንዲያካሂድ ነገሩት። ደጃች ወንድ ይራድም በእቴጌ መነን ፊት ጎረረና የኮሶ ሻጯን ልጅ በሕይወት እንዳለ ይዞ ለፍትህ እንደሚያቀርበው ነገራቸው። በሜጮም ጦርነት በ300 ሠራዊት የተዋቀረው የካሳ ጦር ሺህ ሠራዊት ያለውን የደጃች ወንድ ይራድን ጦር አሸነፈ። ካሳን ማርኬ አመጣዋለሁ ብሎ የፎከረው ደጃች ወንድ ይራድ ራሱ ቆስሎ ተማረከ፤ ካሳም ወንድ ይራድ የኮሶ ሻጭ ልጅ ብሎ አናንቆ እንደሰደበው ሰምቶ ነበር፤ የካሳ ሠራዊትም ድል ስላደረጉ ለድሉ ድግስ ጠጅና ጠላ እየጠጡ ሳለ በካሳ ትዕዛዝ ታዛዦቹ ደጃች ወንድ ይራድን በተደጋጋሚ መራራውን ኮሶ በግድ አስጋቱት። ከደጃች ወንድ ይራድ ሽንፈት በኋላ እቴጌ መነን ልጃቸውን ራስ አሊን በወገራ እንዲቀመጥ አዘዙት፤ እሳቸው ራሳቸውም 20000 ሠራዊት እየመሩ ካሳ ላይ መጡበት። በደምቢያም ጦርነት ተካሄደ፤ የካሳ ሠራዊት ከመነን ሠራዊት ጋር ምንም አይመጣጠንም። መነንም በጦርነቱ ለድል ቀርበው ሳለ አንድ ጥቃት ደርሶባቸው ቆሰሉ፤ ከፈረሳቸውም ወደቁ፤ ምርኮም ተማረኩ፤ በካሳም ፊት ቀረቡ። ከወንድ ይራድ ተቃራኒ በሆነ ሁኔታ መነንን የተቀበላቸው በጥሩ ሁኔታ ነበር። ራስ አሊም የእናቱ መማረክ በሰማ ጊዜ በካሳ ላይ ዘመተ፤ ነገር ግን ያለው አማራጭ እርቅ እና ድርድር ብቻ እንደሆነ ሲያውቅ፤ ከካሳ ጋር ተደራደረ፤ እርሱም እናቱን ከለቀቀለት ደምቢያና ቋራን ይገዛ ዘንድ እንደሚሰጠው ነገረው፤ ካሳም ተስማማ እቴጌ መነንንም ለቀቀ። ብዙ ሰውም ደጃች የሚለውን ማዕረግ ለካሳ ሰጠው። በዚህም ጊዜ የካሳ ስም በሙሉ ኢትዮጵያ ገነነ። እናቱን ካስመለሰም በኋላ ራስ አሊ ከደጃች ካሳ ጋር እርቅ ለመፈጸም ስለፈለገ በጎጃሙ ገዥ በደጃች ጎሹ ትብብር ሁለቱም በደምቢያ ተገኝተው ያላቸውን ሠራዊት አሳዩ። አሁን ካሣ የአሊን እና የጎሹን ጥምር ጦር ቢዋጋ እንደማያሸንፋቸው አውቋል፤ ስለዚህም ለየብቻ ሊያጠቃቸው ፈለገ። ካሳም የጦር ስልት አዘጋጀ ለተከታዮቹም ደምቢያን ለቅቆ እንደሚሄድ ነገራቸው፤ ደግሞም አደረገው። ከደምቢያም ለቀቀ፤ ወደ ሠራዊቱንም በትውልድ ቦታው በቋራ አጠናከረ። ራስ አሊም የካሳን እንቅስቃሴ ባወቀ ጊዜ ደምቢያ የደጃች ጎሹ ክፍለ ሀገር እንደሆነች አወጀ። ደጃች ጎሹም በራስ አሊ ተግባር ደስ ተሰኘ። ደጃች ጎሹም በግልጽ የጎጃምና የደምቢያ መሪ ሆነ፤ ግን ይህ ለካሳ በደንብ ጠቅሞት ነበር። ካሳም ሠራዊቱን ወደ ደምቢያ አንቀሳቀሰ፤ በጉራ አምባም ብዙ ቁጥር ካለው የደጃች ጎሹ ጦር ጋር ፊት ለፊት ተጋፈጠ። የደጃች ጎሹም ጦር በጦርነቱ እየመሩ ነበር፤ ነገር ግን ደጃች ጎሹ ራሳቸው ሠራዊቱን ከፊት እየመሩ ሲዋጉ ነበርና በጥይት ተመቱ፤ ከፈረሳቸውም ወድቀው ወድያውኑ ሞቱ። በዚህም ካሳ ሁለት አይነት የተቀላቀለ ስሜት ተሰማው፦ ይህም ድል በማድረጉ ደስተኛ ነበር፤ ነገር ግን የደጃች ጎሹን የሞተ አካል ባየ ጊዜ በቤቱ በቆየ ጊዜ የተደረገለትን አቀባበል አስታውሶ አዘነ። ራስ አሊም ደጃች ጎሹ እንደተሸነፈ ሲሰማ የደጃች ያዘው፣ የደጃች ባለው፣ የደጃች አበን እና የላስታውን ብሩ አሊን ጦር ሳይቀር እንዲሁም የትግራይና የሰሜኑን የደጃች ውቤን ጥምር ጦር ይዋጉት ዘንድ ላከበት፤ እነዚህ ሁሉ ግን ተሸነፉ። አሁን ራስ አሊ መቶ ሺህ ተዋጊ አዋቀረ በ1844ም ለጣና ሐይቅ ቅርብ በሆነው በጎርጎራ ከካሳ ጦር ጋር ተገናኘ። በጎርጎራም በቁጥር ትልቅ የነበረው የራስ አሊ ጦር በካሳ ጀግና ተዋጊዎች ፊት መዳከም ጀመረ። ራስ አሊም ተሸነፈ፤ ተክለ ፃድቅ መኩርያም እንዳለው ከሆነ ራስ አሊ በተሸነፈ ጊዜ "ይሄ የካሳ በትር ሳይሆን የእግዚአብሔር በትር ነው" ብሏል። ከዚህ በኋላ የደጃች ካሳ ተከታታይ ድሎቹ ማንም የማቋቋመው ጦር እንዲገነባ አደረገው፤ ወደ ጎንደርም በመሄድ የንግስናውን በዓል ማዘጋጀት ጀመረ፤ ነገር ግን ንግስናውን ያለ ፓትርያርክ አቡነ ሰላማ ቡራኬ ማድረግ አልቻለም፤ ፓትርያርኩ ደግሞ የተቀመጡት በደጃች ውቤ ቤት ነበር። በእውነታው ካሳ ወደ ደጃች ውቤ መልዕክተኛን በመላክ ፓትርያርኩ ወደ ጎንደር ይመጡ ዘንድ እንዲፈቅድላቸው ነገረው፤ ነገር ግን ውቤ ራሱ የኢትዮጵያ ንጉስ መሆን ስለሚፈልግ ጥያቄውን አልተቀበለም ነበር። ካሳም አማራጭ ስላልነበረው ውቤ ላይ ዘመተበት፤ የደራስጌ ጦርነትም ተካሄደ፤ በዛም ከሁለቱም በኩል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው ሞተ። በመጨረሻም ከፍተኛ ፉክክር ባለበት ጦርነት መካከል ልጁ እሸቴ ሞቶበትና ሠራዊቱ ተዳክሞ ውቤ ለካሳ እጁን ሰጠ። ደጃች ካሳም ድል ካደረገ በኋላ ወደ ደራስጌ ማርያም ቤተ ክርስትያን ገሰገሰ፤ ህዝቡም በእልልታና በጭብጨባ ተቀበላቸው። ከደራስጌ ድል 3 ቀን በኋላ አቡነ ሰላማ ደጃች ካሳን ቴዎድሮስ ዳግማዊ ንጉሰ ነገስት ዘ ኢትዮጵያ ብለው በየካቲት 5፣ 1847 ዓ.ም ሾሙት። ከሹመታቸው በፊት ቴዎድሮስ ከጎጃሙ ብሩ ጎሹ ጋር ተጋጥመው ነበር። ከደጃች ውቤና ከራስ አሊ ጋር ሲነፃፀር ትንሽና ደካማ ታዳኝ ነበር፤ ነገር ግን ቴዎድሮስ ገና አንፃራዊ በሆነ ሁኔታ ጠንካራ በሆኑት በሸዋ ንጉስ በኃይለ መለኮት ላይ መዝመት ነበረባቸው። በ1849ም ብዙ እግረኛ ፈረሰኞችን ይዘው መንዝ ድረስ መጡ፤ በዛም ለህዝቡ "ሀገርና አባት ካላችሁ ወደ ሀገራችሁና ወደ አባታችሁ ሂዱ፤ ከሌላችሁም አባት እሆናችኋለሁ" አሏቸው። ከኃይለ መለኮት መሸነፍ በኋላ የሳህለ ማርያም(የኃይለ መለኮት ተተኪ እና የኋላው ዳግማዊ ምኒልክ) አጃቢዎች የነበሩት የሸዋ መሳፍንት መልሶ ጥቃት በማካሄድ ቴዎድሮስን ሊያጠቁ አቀዱ። ሳህለ ማርያምም ገና የ12 ዓመት ልጅ ስለነበር ሥልጣኑን መጠቀም የሚችለው በስም ብቻ ነበር እናም የሸዋን ሠራዊት በምናብ ካጠፋው በቴዎድሮስ ሸዋን ያስተዳድር ዘንድ ከተሾመው ከራስ እንግዳ ጋር የሳህለ ማርያም ጦር አይመጣጠንም ነበር። በዚህም ምክንያት ሳህለ ማርያም ተማርኮ የጦር እስረኛ ሆነ፤ ግን ከፍራቻው ተቃራኒ በሆነ ሁኔታ ቴዎድሮስ ፍቅር አሳዩት፣ በሥርዓትም ተንከባከቡት፣ ይዘውትም ሄዱ፤ ነገር ግን ሸዋን ለቅቀው ከመሄዳቸው በፊት ቴዎድሮስ የኃይለ መለኮትን ወንድም መርድ አዝማች ኃይለ ሚካኤልን በሸዋ ወኪላቸው አድርገው፤ አቶ አንዳርጋቸውን ደግሞ መቶ አለቃቸው አድርገው ሾመው ሄዱ። ማጣቀሻ(Reference) https://www.africanidea.org/emperor_t...