У нас вы можете посмотреть бесплатно ይዌድስዋ፤ ወበሳድስ፤ ይቤላ | yiwedisiwa part 20 или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
#ይዌድስዋ_ወበሳድስ_ይቤላ ትምህርተ ሰዓታት ይዌድስዋ፤ ወበሳድስ፤ ይቤላ በመልአከ ኀይል ቆሞስ አባ ዘድንግል 💒💒💒 የመጽሐፍ ሰዓታት ጸሐፊ ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ከ፲፫፻፶፯ - ፲፬፻፲፯ ዓ.ም ድረስ የነበረ ታላቅ ሊቅ ሲኾን ካለው ከፍተኛ መንፈሳዊ ዕውቀት የተነሣ "ዐምደ ሃይማኖት፣ ኢትዮጵያዊ ቄርሎስ" የሚል ሥያሜ ሲሰጠው ከ፳፩ በላይ መንፈሳውያት መጻሕፍትን የጻፈ አባት ነው። ሰዓታት ማለት የበርካታ ሰዓቶች ስብስብ ሲኾን በነጠላ ሰዓት ሊባል ይችላል። የተፈጠሩ ፳፪ቱ ፍጥረታት ኹሉ መነሻ ጊዜ (ሰዓት) ያላቸው ሲኾኑ፤ በተለይ ሰውና መላእክት በየሰዓቱ በየጊዜያቱ የእግዚአብሔርን ስሙን አመስግነው ክብሩን ሊያወርሳቸው ፈጥሯቸዋል። ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም ይኽነን መጽሐፉን "መጽሐፍ ሰዓታት ዘሌሊት እና መጽሐፍ ሰዓታት ዘመዓልት ብሎ በዚኽ ስም ሊሠይምበት የቻለበት ምክንያት፦ ፩, በመዓልትም በሌሊትም በሰዓቱ ኹሉ በአንድነቱ ምንታዌ(ኹለትነት) በሦስትነቱ ርባዔ (አራትነት) የሌለበት ልዑል እግዚአብሔር ምስጉን ስለኾነ ሲኾን ፪, ካህናት፣ ዲያቆናት፣ ምእመናን በደመ ወልደ እግዚአብሔር በተመሠረተችው የልዑል ማደሪያ በኾነችው በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው በእነዚህ የሌሊትና የመዓልት የሰዓት ጊዜያት ልዑል እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑበት ታላቅ የምስጋና መጽሐፍ ስለኾነ ነው። 💒 ይዘቱም • ምስጢረ ሥላሴ • ስለልዑል እግዚአብሔር ቸርነት • ስለ እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ • ሰለ ነገረ ማርያም • ሰለ ነገረ መላእክት • ስለ መስቀልና ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስለ ሰንበተ ክርስቲያን ክብር • ስለ ቀደምት አርዕስተ አበው እና ነቢያት ክብርና አማላጅነት • ስለ፬ቱ ወንጌላውያን ምሳሌ • ሰለ ሰማዕታት ተጋድሎና አማላጅነት • ሰለ ጻድቃን ስለ መነኮሳት ሰለ ደናግል ሕይወትና ቅድስናዊ ኑሮ • ስለ ሥዩማነ ቤተ ክርስቲያን • ስለ ሥነ ዘፍጥረት። በጥልቀት ተብራርቶበታል። 💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒💒 "የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው"። Subscribe for more... / @ztw Follow us on Instagram... / zenawe_tefsehet_wehaset Follow us on Telegram... https://t.me/lediyakonat