У нас вы можете посмотреть бесплатно ኢ-መጽሐፍ ቅዱሳዊው или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
ኢ-መጽሐፍ ቅዱሳዊው ውድድር (Unhealthy competition) ውድድር ጤናማ ሲሆን ፦ 👉 ለለውጥ መነሳሳት ያለበትና እውነትና ፍትህን የማይጨፈለቅ ነው። 👉ዓይንን ከሌሎች የመሮጫ ትራክ ላይ አንስቶ በራስ ትራክ ላይ ያተኮረ ነው። 👉ወዳጅን ወደ ተቀናቃኝነት የመለወጥ አጀንዳ ይዞ፣ ሌሎችን ከጨዋታ ውጪ የማደርግ ምኞት የለውም! ውድድር ጤና ያጣ ሲሆን:- – 👉መነሻው ከነ እከሌ በልጬ መገኘት አለብኝ ወደ ሚል ጭንቀት ይወስዳል ። 👉ከክፉ ቅናት እና ተገቢ ካልሆኑ ውስጣዊ ፍላጎቶች የመነጨና በማሸነፍ አባዜ የተወጠረ ነው። 👉እርካታ አልባና ጭንቀታም የሚያደርግ፣ የደስታ ቀማኛ ነው! መጽሀፍ ቅዱስ ጤነኛ ስላልሆነ ፉክክር ምን ይላል? መጽሐፍ ቅዱሳችን በትዕቢት፣ በቅናት፣ ወይም በራስ ወዳድነት የሚመራ ጤናማ ያልሆነ ውድድርን አጥብቆ ይቃወማል። የሌሎችንም ልብ የሚጎዳ ፉክክርን አጥብቆ ያወግዛል:: ምክኒያቱም ፣- 👉.ምንጩ ኩራትና እራስ ወዳድነት ስለሆነ ነው። ፊሊ 2:3 "ሌሎች ከእናንተ እንደሚሻሉ በትህትና ቁጠሩ እንጂ፣ በራስ ወዳድነት ምኞት ወይም ከንቱ ውዳሴ ለማግኘት አንዳች አታድርጉ" 👉ቅናትን የሚለኩስ የጤናማ ህብረት ጠንቅ ስለሆነ ነው። ገላ 5:26 "እርስ በርሳችን እየተጎነታተልንና እየተቀናናን በከንቱ ውዳሴ አንመካ" ቅናት ማለት -የአንዱን፣ ስኬት፣ ችሎታ፣ ኑሮ፣ ትዳር፣ ስራ፣ አገልግሎት … ከራስ ጋራ በማወዳደር የሚነሳ ክፉ የልብ ስሜት ነው 👉ወደ ጥላቻ፣ ሌላውን ለማዋረድ ወደ መፈለግ ይመራል ። አጥንት ያነቅዛል ምንም አይጠቅምም የኋላ ኋላ ጉዳቱ ለእራስ ነው:: 1ኛ ቆሮ 13-4 ፍቅር አይቀናም። ስለዚህ ፦ ራስን ከሌሎች ጋር ማፎካከር ይቁም !! ፍቅርና ህብረትን ያጠፋል- እኛ የተጠራነው አጥፊ ለሆነው ፉክክር ሳይሆን ለፍቅርና ለአንድነት ነው! ሮሜ 12:10 "በወንድማማች መዋደድ እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ፣ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ" ጌታ ይርዳን 🙏