У нас вы можете посмотреть бесплатно ዶክሳ ጥበባት 8 - ህልምሽ / ህልምህ የማን ነው? Is my dream really my dream? или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
ዶክሳ ጥበባት 8 - ህልምሽ / ህልምህ የማን ነው? ለብዙዎቻችን ህልማችንን አጥርተን ማየትና በሙሉ አቅሙ ወደ መገለጥ ማምጣት በጣም ከባድ ፈተና ነው። ስንቶቻችን እንሆን የምንኖርለትን ምክንያት አበክረን የምናውቅና በየዕለቱ ወደዚያው ሙላት እየገሰገስን በዕርካታ የምንኖረው? ይህ የባለቤትነት ጥያቄ ይባላል። Is my dream really my dream? ህልሜ የእውነት የእኔ የራሴ ህልም ነው? በተለያዩ ምክንያቶች የሌሎች ሰዎች ሃሳብ: ስሜት: ምኞትና: ዓላማ ሳናውቀው ሊጋባብን ይችላል። ያን ጊዜ የራሳችንን ህልም የት ጋር እንደጣልነው ሳይገባን በከንቱ እንባክናለን። ብዙዎቻችን በጣም ጥሩ አድርገን መሥራት የምንችለው ነገር ምን እንደሆነ አናውቅም። ጥልቅ ፍላጎታችን ምን እንደሆነም አይባንም። ብዙ ሰዎች በሌሎች ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት ሲሉ በአካባቢያቸው የተሻለ ተመራጭነት ያለው የመሰላቸውን ዓላማ ይዘው ይራመዳሉ። ከዚህ የተነሳ በውስጣቸው ሊቀሰቀስ ይችል ከነበረው እውነተኛ ማንነትና ተፈጥሮአዊ ስብዕና ተለይተው ይወድቃሉ። የእኛ የሆነ እውነተኛ ህልም የወደፊቱን ዘመን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይና ነፍስን በደስታ የሚሞላ ራዕይ ማለት ነው። በነፍሳችን ውስጥ ኩልል ብሎ የሚፈስ እውነተኛ ህልም ሲኖረን በሙሉ ልብ ልናከናውን የምንችለውን ሁሉ እንድናደርግ ታላቅ አቅም ይሰጠናል። ህልማችሁን በሙላት የምትገልጡትና የተፈጠራችሁለትን ህይወት መኖር የምትችሉት የእናንተ መሆኑ በተረጋገጠ ህልም / ጥሪ ውስጥ ነው። ህልማችንን ዕውን ለማድረግ የመጀመሪያው እርምጃ ህልማችን በእርግጥ የእኛ መሆኑን ማረጋገጥ ነው። ህልሜ የእውነት የእኔ ህልም ነው? ለዚህ ጥያቄ የምትሰጠው መልስ "አዎን የእኔ ነው" የሚል ይሆን? (እባኮን ሙሉውን መልዕክት ከኦዲዮው ያድምጡ..) ሻሎም 🌼🌼