У нас вы можете посмотреть бесплатно 1ኛ ጢሞቴዎስ: ሐሰተኞችን መቃወም፤ በእግዚአብሔር ቤት እንደሚገባ መኖር //1 Timothy: living in God's household// Endashaw N или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
1 ጢሞቴዎስ፣ 2ኛ ጢሞቴዎስ እና ቲቶ በተለምዶ “የመጋቢያን ደብዳቤዎች” (Pastoral Epistles) ተብለው ይጠራሉ። የደብዳቤዎቹ ጸሐፊ ላይ የሚነሣ ጥያቄ ቢኖርም በሐዋርያው ጳውሎስ እንደ ተጻፉ መሞገት ይቻላል። የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ የሚጠናቀቀው ጳውሎስ በሮም እስር ቤት ውስጥ ሆኖ ቢሆንም በመልእክታተ ምጋቤ ውስጥ በስተምስራቅ ሲንቀሳቀስ ይታያል። አንዳንዶች በእነዚህ ደብዳቤዎች ውስጥ የተጠቀሱት ሥፍራዎች በሐዋርያት ሥራ ውስጥ አይገኙም። አብዛኛዎቹ ምሁራን እንደሚስማሙት ሐዋርያው ጳውሎስ ከሮም እስር ቤት ተፈትቶ አራተኛ የወንጌል ጉዞ አድርጓል፤ መልእክታተ ምጋቤ ከዚህ ከአራተኛ ጉዞው ጋር የተያያዘ ነው። ጳውሎስ ከእስር ከተፈታ በኋላ ቲቶ እና ጢሞቴዎስን ይዞ በመጀመሪያ ወደ ቀርጤስ ተጓዙ፤ ቲቶን በቀርጤስ ትቶት ከጢሞቴዎስ ጋር ወደ ኤፌሶን ሄዱ፤ ጢሞቴዎስን በኤፌሶን በመተው ወደ መቄዶንያ ተጉዞ ከመቄዶንያ 1ኛ ጢሞቴዎስ እና ቲቶን ጻፈ። የ1ኛ ጢሞቴዎስ ዓላማ የሐሰት መምህራን ልዩ ትምህርት እንዳያስተምሩ ማዘዝ ነው (1÷3)። ጳውሎስ ወደ ኤፌሶን የመሄድ ዕቅድ ነበረው፤ ነገር ግን እስኪሄድ ድረስ አማኞች በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ እንዴት መመላለስ እንዳለባቸው መገንዘብ ይኖርበታል (3÷15)። ጢሞቴዎስ ለሕይወቱ እና ለአገልግሎቱ በመጠንቀቅ መጽናት እና ለራሱና ለሚሰሙት ሁሉ በረከት መሆን ይጠበቅበታል። ይህን ቪድዮ በመመልከት የደብዳቤውን ትኩረት እና ዳሰሳ መረዳት ይቻላል።