У нас вы можете посмотреть бесплатно የቲቶ መልእክት: ጤናማ ትምህርት ጤናማ ኑሮ //እንዳሻው ነጋሽ// Titus: Healthy Teaching Healthy Conduct// Endashaw Negash или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
የቲቶ መልእክት አጭር ቢሆንም አንድ አማኝ ሊያውቃቸው የሚገቡትን መሠረታዊ ነገሮች በውስጡ የያዘ ደብዳቤ ነው። የመልእክቱን ትኩረት ጤናማ ትምህርት ጤናማ ኑሮ በማለት መስቀመጥ ይቻላል። ሐዋርያው ጳውሎስ ይህንን ደብዳቤ የጻፈበት ምክንያት 1፡5 ላይ በግልጽ ተቀምጧል። ቲቶ የተጀመረውን ጅምር ሥራ እንዲጨርስ እና በየከተማው ሽማግሌዎችን እንዲሾም ታዟል። በምእራፍ 1 መግቢያውን ተከትሎ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች መሥፈርት እና በቀርጤስ የነበሩ የሐሰት መምህራን ባሕርያት ተዳሰዋል። በቀርጤስ የነበሩ ሰዎች እና የሐሰት መምህራን ሁኔታን ከገለጸ በኋላ በምእራፍ 2 ላይ ቲቶ ግን ጤናማ ትምህርት እንዲያስተምር ያሳስበዋል። ምእራፍ 2 አማኞች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዴት መመላለስ እንደሚገባቸው በማሳሰብ ላይ ሲያተኩር ምእራፍ 3 ደግሞ አማኞች በማያምኑት መካከል እንዴት መመላለስ እንዳለባቸው ያስተምራል። ይህ ደብዳቤ ጤናማ ትምህርት ጤናማ ቤተ ክርስቲያን እና ማኅበረ ሰብ እንደሚፈጥር ያመለክታል። ይህቺን አጭር ቪድዮ በመመልከት የደብዳቤውን ትኩረት መገንዘብ ይቻላል።