У нас вы можете посмотреть бесплатно ትንቢተ ኤርምያስ //ፍርድ፣ ተሓድሶ፣ አዲስ ኪዳን //እንዳሻው ነጋሽ//Jeremiah// New Covenant //Endashaw Negash или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
ነቢዩ ኤርምያስ በቅድመ ምርኮ ለደቡቡ የይሁዳ መንግሥት ከተላኩ ነቢያት መካከል አንዱ ነው። ይህ ነቢይ በአገልግሎቱ የመጀመሪያዎቹ ጊዜያት በሕዝቡ ላይ እየመጣ ያለውን ፍርድ በማስታወቅ በንስሓ እንዲመለሱ ቢጣራም ሕዝቡ መልእክቱን ለመስማት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ፍርድ አይቀሬ መሆኑን እና ከፍርድ በኋላ ያለውን ተሓድሶ አመልክቷል። ሃይማኖተኛ የነበረው የይሁዳ ሕዝብ ቤተ መቅደስ በመካከላቸው መኖሩን፣ እግዚአብሔር ከዳዊትና ከዘሩ ጋር ያደረገውን ኪዳን፣ እና የመሳሰሉትን ምክንያቶች በመዘርዘር ከኤርምያስ ይልቅ ሐሰተኛ ነቢያትን ይሰማና ይከተል ነበር። ነቢዩ ኤርምያስ ግን በድፍረት ከእግዚአብሔር የተቀበለውን መልእክት በማስተላለፍ ልዩ ልዩ መከራዎችን ተቀብሏል። የተናገረው የፍርድ መልእክት ሲፈጸም ተመልክቷል። የትንቢተ ኤርምያስ ማእከላዊ ሓሳብ ፍርድ፣ ተሓድሶ እና እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር አዲስ ኪዳን ያደርጋል የሚል ሊሆን ይችላል። ይህን አጭር ቪድዮ በመመልከት የመጽሐፉን ማእከላዊ ጉዳይ መረዳት ይቻላል።