У нас вы можете посмотреть бесплатно የአምራች ስነ_ልቦና (ክፍል አራት) - ጋዛ_ጌጣጌጥ или скачать в максимальном доступном качестве, видео которое было загружено на ютуб. Для загрузки выберите вариант из формы ниже:
Если кнопки скачивания не
загрузились
НАЖМИТЕ ЗДЕСЬ или обновите страницу
Если возникают проблемы со скачиванием видео, пожалуйста напишите в поддержку по адресу внизу
страницы.
Спасибо за использование сервиса ClipSaver.ru
ጋዛ ጌጣጌጥ :- ቱባ ባህላችንን ወደ ኢኮኖሚ ምንጭነት መለወጥ የቻለ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ EED: ጥቅምት 5/2018 ዓ.ም (ወራቤ) በኢትዮጵያ የቡና አፈላል ስነ-ሥርዓት እንደ ማህበራዊ ትስስር እና የእንግዳ ተቀባይነት ምልክት ሆኖ ለብዙ ትውልዶች የቆየ ባህላችን ነው። ጀበናው ከውብ ረከቦት ጋር ተደርድሮ፣ ቡናው ተቆልቶ እየተሸተተ፣ ተወቅጦ ሲፈላ፣ እስኪሰክን ተጠብቆ – አቦል፣ ቶና፣ በረካ ተብሎ በርጋታ ቁጭ ተብሎ ይጠጣል። ይህን ባህል ለማክበር የምንጠቀምባቸውን እንደ ረከቦት ያሉ ቁሳቁሶች ከውጭ እያስገቡ መጠቀሙ ያልተዋጠላቸው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወራቤ ከተማ የሚገኙት አቶ አብዱልቃድር አለማር አህመድ ጋዛ ጌጣጌጥን መሠረቱ። ጋዛ ጌጣጌጥ የሚያመርታቸው ምርቶች ከውጭ ከሚገቡት በጥራትም ሆነ በዋጋ የተሻሉ ናቸው። በተጨማሪም ድርጅቱ ከዚህ በፊት ከውጭ እያስገባ ይጠቀምባቸው የነበሩ ጥሬ ዕቃዎችን በአካባቢያዊ ተረፈ ምርቶች በመተካት የውጭ ምንዛሪ ፍሰትን በሀገር ውስጥ ማቆየት ችሏል። በኢትዮጵያ ከቡና አፈላል ባህላችን በተጨማሪ የማኑፋክቸሪንግ ውጤቶችን የሚጠቀሙ ብዙ ቱባ ባህሎች አሉን። እነዚህ ባህሎቻችንን ለመከወን የምንጠቀምባቸውን ቁሳቁሶች በሀገር ውስጥ አቅም መመረት የሚችሉ ናቸው። ዜጎች የስራ ባህላቸውን በማሻሻል፣ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ማምረት ከቻሉ፤ ከውጭ ሀገር ሸቀጥ ጥገኛነትን በመቀነስ የኢኮኖሚ ነፃነትን በአጭር ግዜ መጎናፀፍ እንደሚቻል ጋዛ ጌጣጌጥ ህያው ማሳያ ነው። ጋዛ ጌጣጌጥ ከትርፍ ባሻገር እንደ ማህበረሰብም ትልቅ ለውጥ ፈጥሯል። የአካባቢ ብክለትን በመቀነስ (ተረፈ ምርቶችን በመጠቀም) እና ለብዙ ዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር በዙሪያው ያሉ ማህበረሰቦች ህይወት መለወጥ ችሏል። ጋዛ ጌጣጌጥ ከገበያ እጥረት ጀምሮ እስከ ቴክኖሎጂ ጉድለት ብዙ ችግሮች ቢገጥሙትም አሁን ላይ የተለያዩ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በራሳቸው አቅም በመፍጠር ምርታማነታቸውን ማሳደግ ችሏል። በተጨማሪም ምርቶቻቸውን ወደ ውጭ ሀገር ለመላክ ዕቅድ አላቸው። ጋዛ ጌጣጌጥ ቱባ ባህላችንን ወደ ኢኮኖሚ ምንጭነት መለወጥ የቻለ ስኬታማ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ ነው። በእርሶ ዙሪያ ያሉ ባህላዊና ሀይማኖታዊ ዕሴቶች ምን ይፈልጋሉ? የማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ ማህበረሰብን ይቀላቀሉ! ዛሬውኑ ይጀምሩ! #ኢትዮጵያ_ታምርት_እኛም_እንሸምት ለተጨማሪ መረጃ ፡- #ድረ_ገጽ: https://www.manuf-sme.gov.et #ፌስቡክ፡ / ethiopianenterprisedevelopment #ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopianenterprisedevel... #ዩትዩብ፡ / @ethiopiaenterprise #ኢሜል: ethiopianenterprise@gmail.com